ከትንሣኤ እሑድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ በአጭሩ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 24, 2020

ከትንሣኤ እሑድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ በአጭሩ


 

ከትንሣኤ እሑድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ በአጭሩ

ሰኞ - ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
================================ 

ማክሰኞ - ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ 《ዮሐ. 20፡27-29》
በዓለ መላእክት ይባላል፦ ስለ ቅዱሳን መላእክት የምንመሰክርበት ዕለት ነው።
================================ 

ረቡዕ - አልዓዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
================================ 

ሐሙስ - አዳመ ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋና የተገባለት ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ እንደ ተፈጸመና አዳም ከነልጅ ልጆቹ ወደ ገነት በክብር መግባቱን እናስባለን፡፡"የአዳም ሐሙስ”
================================ 

ዓርብ - ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
================================ 

ቅዳሜ - ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
================================ 

እሑድ - ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages