ፍካሬ ኢየሱስ -ክፍል 2 - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ በድምጽ፤ በምስልና በጽሑፍ ዘገባዎችን ያቀርባሉ፡፡

አትሮንስ ዘተዋሕዶ ብሎግ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን ጠብቆ በድምጽ፤ በምስልና በጽሑፍ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ነው።

በመምህር ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ብሎግ ነው፡፡

በመምህር ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ብሎግ ነው፡፡

በቅርብ የተጻፉ

Home Top Ad

Post Top Ad

Saturday, June 27, 2020

ፍካሬ ኢየሱስ -ክፍል 2


Image may contain: text and food
ፍካሬ ኢየሱስ -ክፍል 2
==========::=:===
፨ ትዕዛዜን ጠብቁ ቃሌንም አክብሩ፨
ወንድማቹ ቢበድላችሁ ለብቻው ሄዳችሁ ምከሩት ምክራችሁን ቢቀ ይቅርታ አድርጉለት። ባይሰማ ግን በሁለትና በሶስት ሰዎች ፊት ንገሩት እነርሳቸውንም ባይሰማ ለቤተክርስቲያን ንገሯት ቤተክርስቲያንንም ባይሰማ እንደ አረሚ ቁጠሩት።
እምነታችሁን አታጓድሉ
ምፅዋታችሁን ለራሳችሁ ትታዩና በሰው ፊት ትመሰገኑ ዘንድ እንደ ግብዞች በሰው ፊት እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ እንዲህ ካልሆነ በሰማይ አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም እናንተስ ምፅዋት ያረጋችሁ ጊዜ ቀኝ እጃችሁ የሰጠውን ግራ እጃችሁ አይወቅ። በስውር የሚያይ የሰማዩ አባታችሁ ዋጋችሁን በሰማይ ይሰጣችኋል
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨ትዕዛዜን ጠብቁ ቃሌንም አክብሩ፨
በምትፆሙበት ወቅት እንደግብዞች ጿሚነታችሁን ለመሳወቅ ሰውነታችሁን አታጠውልጉ ግንባራችሁን አትቋጥሩ፤ ፊታችሁን ታጠቡ ገጻችሁ ይብራ ፈገግታም ይኑረው ድካማችሁን በብርታት ሰውሩበሰማይ የሚያይ አባታችሁ ዋጋችሁን በግልፅ ይሰጣችኋልና።
ትዕዛዜን ጠብቁ
ክብርንና ብልፅግና አብዝተው የሚወዱ በፈተና ይወድቃሉ በወጥመድም ይገባናሉ። ለድሃ እና ለችግረኛ እንዳይሰጡ እጃቸው ይታሰራል ልባቸውም እንደ ፈርዖን ይደነድናል የሚድኑትን እንዳያውቁ ዓይናቸው ይሸፈናል ቃሌን እንዳይሰሙ ጆሯቸው ይደነቁራል እንዳይበሉም አፋቸው ይታሰራል ሆዳቸውም ይታወካል ለማያውቁት ሰው ገንዘባቸውን ያከማቻሉ ለልጃቸውም አያልፍም። በኃጢአት እንደ ተሸፈኑ ይሞታሉ ንስሃም አይገቡም ።
፨በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ ፨
ለደጋግ ግን የሚረባ የሚጠቅም መንፈስ ቅዱስ ያሰጣቸዋል ስሜ ሲነሣ ይደሰታሉ የዚህን ዓለም ዋዛ ፈዛዛ አይጫወቱም በሲኦል ከመገዛት ይድኑ ዘንድ።
፨ትዕዛዜን ጠብቁ፨
በዚያን ዘመን ሰዎች ጥርስ አውጥተው ፀጉራቸው ሸብቶ ይወለዳሉ ሃይማኖታቸውን ያፈርሳሉ አንደበታቸው እንደተሳለ ምላጭ ነው አፋቸው ለዐመፅና ለተንከኰል እንደ ንቃቃት የተከፈተ ነው ከዕውነት ይልቅ ሐሰት መናገር ይወዳሉ ልባቸው ለክደት ሆዳቸው ለክፋት የተዘጋጀ ነው።
በዚያን ጊዜ የሚጣፍጠው ውሃ የሚጥመው እህል መራራ ይሆናል ሕዝብ እርስ በእርስ ይተላለቃል ምግባር ትሩፋት የሚሰራባት ሃገር ትሠወራለች ሃይማኖት የሚፀናባት አገር ትጠፋለች ከቀድሞው በደል የበለጠ በደል ይሠራል በአዝዕርት በአትክልትና በአበባ አጊጦ የሚታየው ይህ ዓለም ይፈርሳል ይጠፋል መሬት ምድረ በዳ ትሆናለች ዓለም በመከራ ትታወካለች ፀሐይ በድንገት ሌሊት ትወጣለች ጨረቃም እንዲሁ በቀን ታበራለች ።
፨በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ ፨
በዚያን ጊዜ ያንዱ መንግስት ሀገር የሌላውን መንግስት ሀገር በውኑ ባንቺ ዘንድ በእውነት የሚሰራ አለወይ ብላ ትጠይቃለች እሷም የለም ትላለች በዚያ ሰዓት ከመከራውና ከስቃዩ የተነሳ ሰው ሞትን ይመኛል ከባሕር ቢጠልቅ ከገደል ቢገባ ሞትን አያገኝም።
==================
በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ በዚያን ጊዜ በየሐገሩ ሽብር ይሆናል እሳትም ከሰማይ ተጠቅሎ ይወርዳል ከእንጨት ደም ይፈሳል ድንጋይም አፍ አውጥቶ ይጮሀል ከሰማያት ወረድኩ ከድንግል ተወለድኩ የሚል ሐሰተኛ መሲህ ይመጣል ሕዝብ ይታወካል ብዙዎች በምትሐቱ ያስታል በዚያን ጊዜ እንዳያስታችሁ በሕገ ልቦና ፀንታችሁ ተቀመጡ።
በዚያን ጊዜ ሐሰተኞች ነቢያት የበግ ለምድ ለብሰው ከአጋንንት ጋራ ሁነው የሚያስቱ የሚያሳብዱ የሐሳዊ መሢህን ነገር የሚያስተምሩ ሰዎች ይመጣሉ በውስጣቸው ግን ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው በዘመኑ ትውልድ ላይ በማር የተለወሰ መርዝ ይነዙበታል እውነተኛ መምሕር ለመምሰል በየአደባባዩ ሰላምታን ያበዛሉ የቀሚሳቸውን እጅጌ ያሰፋሉ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ እናንተ ግን አትመኗቸው እምቢ በሏቸው የሚመጣው የሚታወኩበት ዘመን ነውና በየለቱ በየአመቱ ክፉ ነገር ይጨመራል ሰውም በምሳሌ ይኖራል እንጂ መንፈስ እግዚአብሔር አያድርበትም።
በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ በዚያን ጊዜ ምሽት በሆነ ጊዜ ዛሬ ሠማዩ አቅላልቷል ብራ ይሆናል ወይም በምራአብ በኩል ደመና ሢመጣ ባዩ ጊዜ ዝናም ይዘንማል እንዲሁም በሠሜን በኩል ንፋሥ በነፍሠ ጊዜ በሽታ ይሆናል በማለት የአየሩንና የሣማዩን ጠባይ ለመመርማር ይሞክራሉ የሠማይን ሥራ የአየርን ጠባይ
መርምሮ ማወቅ የሚቻለው ማነው ሥጋውን ከነፍሡ ነፍሡን ከሥጋው ለይቶ መናገር የሚቻለው ማነው ።
በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ በዚያን ጊዜ ነግሥታት መኲንንት መሣፍንት የሀገር ሹማምንት ከዚያም በታች ላሉ ሰራዊት በሐሠት የሚምሉ በየእለቱ ቃለቸውን የሚለዋውጡ ሠዎች ይፈጠራሉ ጧት የተናገሩት ለማታ አይደገምም ።በዚያን ጊዜ ተጠበቁ በዚያን ጊዜ ፍቅር የሌላት ባጅርነት መተማመን ያሌላት ጒደኝነት ትፈጠራለች ጥል በደል መሥራት፤ መቀማት፤ሃሜት፤ሀሠት በልባቸው የመላ ሠዎች ይፈጠራሉ ።መብል ፤ መጠጥ በዩ ጊዜ ነፍሣቸውን ለጋሃነመ እሣት ይሸጣሉ እናተ ግን እንደነሣቸው አትሁኑ። አጥብቃቹ ተጠንቀቁ
በኔ ፍቃድ ለሚሄዱ ሠዎች ግን በቅን ልቡና በሌሊትና በመአልት ለሚጋገዙልኝ ሠዎች እኔ እንደ ወዳጆቼ እንደ አብረሃምና ይህሣቅ እንደ የዕቆብና ሙሤ እንደ ባሮቼ እንደ ዳዊት እንደ ዳኒኤል እንደ ኤልያሥና እንደ ሚኪያሥ በሚመጣው ዘመን እጠብቃቸዋለው ተድላ መንግሥተ ሠማያትንም አወርሣቸዋለው ።
በዚያን ጊዜ ወሬ ለመሥማት ነገር ለማየት ወዲህና ወዲያ ይቅበዘበዛሉ ነገር ግን ያዩትን የሠሙትን በሉቦናቸው አያሣድሩም። በዚያን ዘመን ተጠበቁ በዚያን ጊዜ እንደ እሣት የሚያቃጥሉ ፀሀይና ጨረቃ ከዋክብት ይፈጠራሉ ከዚህ ቡሃላ ክረምት እና በጋ አንድ ወገን ይሆናሉ ዝናምም ከአመት እሥከ አመት ይዘንማል ።
የእህል በረከትም ይጎድላል የሠውም ሀይል ሢሦም ይቀንሣል የበቅሎ፤ የግመል፣የእንሥሣ፤ የአራዊት ሃይል ሁሉ
ስሥት ሦሥት እጅ ይነሳለታል ።
ቅቤም ማርም ጣአም በረከትም የለውም በአመት አመቱ እየተቀነሠ ይሄዳል።
ክፍል-3-ይቅጥላል.........

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages