ፍካሬ ኢየሱስ ክፍል 3 - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ በድምጽ፤ በምስልና በጽሑፍ ዘገባዎችን ያቀርባሉ፡፡

አትሮንስ ዘተዋሕዶ ብሎግ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን ጠብቆ በድምጽ፤ በምስልና በጽሑፍ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ነው።

በመምህር ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ብሎግ ነው፡፡

በመምህር ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ብሎግ ነው፡፡

በቅርብ የተጻፉ

Home Top Ad

Post Top Ad

Saturday, June 27, 2020

ፍካሬ ኢየሱስ ክፍል 3

No photo description available.
ፍካሬ ኢየሱስ ክፍል 3
=:=:=:=:==:=:=:=:=:=:=
በዚያን ዘመን ተጠበቁ
ወርቅ ይናቃል መዳብ ይከብራል ወርቅ የተባለው ወርቅ አይደለም ወርቅ የተባሉ ክርሥቲያኖች ናቸው ።መዳብ የተባሉ አረመኔዎች ናቸው።አረመኔዎች እራሣቸውን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ ግብዞችና ማሥተዋል የሌላቸው ሠዎች እለዚያም ይወዳሉ ያከብራቸዋልም።
በዚያን ዘመን ተጠበቁ
በዚያን ጊዜ አንድ ወንድ 7 ሤቶች ባል ይሆናል እነሡም እንጀራችንን ሰርተን እንበላላን ልብሣችንንም ፈትለን እንለብሣለን ሠም ብቻ በኛ ለይ በባልነት ይጠራ ባል የላቸውም ከመባል አድነን ይላሉ።
በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ
በዚያን ጊዜ በናተቸው ማህጸን ሣሉ የሚጮሁ ውሾች
ይወለዳሉ።ውሾችም የተባሉት ውሾች አይደሉም በዚያን ጊዜ የሚወለዱ ህፃናት ናቸው እንጂ።
በዚያን ዘመን የሚወለዱ ሕፃናት ቃላቸውን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ
በወላጆቻቸውም ላይ ይነሣሣሉ ለወላጆቻቸውም አይታዘዙም። አባት እናታቸውን አያከብሩም እናተ የመናገር ችሎታ የላቹምና እኛ እንናገር ነገራችንን አታሠናክሉብን
ይሏቸዋል ሞትን አያሥቡም።
እህሊናም አይምሮም የጎደላቸው መንፈሥ እግዚአብሔር የተለያቸው ናቸው።እግዚአብሔር ሓጢያታቸውን ሥለ ታገሣቸው እንደሌለ ይቆጥሩታል በሥራቸው የጎሠቆሉ በሀሣባቸው የረከሡ ናቸው ።
ባህላቸውል ይለውጣሉ የያዙትን ይጥላሉ ያላዩትን ይናፍቃሉ ሠብአዊ በህሪያቸውን በእንሥሣ በህርይ ይለውጣሉ ነውርን ይንቃሉ ሐፍረተውን ይገልጣሉ ሥጋዊ ፍትወትን በሚያስፍፅሙ ሥራዎች ሁሉ የሃሣዊ መሢሆች ተንኮል ልባቸውን ያጠፋዋል አምላካቸውን ያሥረሣቸዋል የሀገር ፍቅር የሀገር ክብር አይሠማቸውም ።
የአባት የእናታቸውን ምክር አይቀበሉም ተውን ልቀቁን እንሩጥ እንፈርጥጥ ይላሉ።በዝሙት ፍቅር ይወድቃሉ በየሸሎቆውና በየ ጎጡ እንደ በግ ታጉረው ጭለማን ለብሠው የሚፈፅሙት ተግባት ከሠዶምና ከጎመራ ሠዎች ግብር ያልተለየ ነው።
የሚያደርጉትን አያውቁትም እግዚአብሔር አያሥተውልም ይላሉ ይመለከታቸውም አይመሥላቸውም እሡ ግን ከሠማይ ሆኖ ይሣለቅባቸዋል ይሥቅባቸዋልም በመዓቱም ያውካቸዋል በውኑ ጆሮን የሠራ እግዚአብሔር አይሠማምን አይንንሥ የፈጠረ አምላክ አያይምን በዚህም ግንባራቸው ዕድሜያቸው ያጥራል በዋጣትነት ዘመናቸው ይቀሰፋሉ ፈጥነውም ይጠፋሉ።
በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ
በዚያ ጊዜ ለብሩ ክብር የታጩ በማዕረግ በሹመት የደጉ በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አደራቸውን ይዘነጋሉ።ሀገራቸው ይክዳሉ መሐሃላቸውን ያፈርሣሉ ከበለሟልነታቸው ይወጣሉ ከማዕርግና ሹመት ጒደኞቻቸው ይለያሉ ክፉ ሥራቸው በተገለፀባቸው ጊዜ ግን ይፀፀታሉ በገዛ እጃቸው ታንቀው ተሠቅለው ወይም በአልባሌ ቦታ ወድቀው ሞተው ይገኛሉ።
በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ
አባት ልጁን ወንድምም ወንድሙን ይጠላል እህት እህቷን አማትም አማቷን አቶድም ባልንጀራም ባልንጀራውን ይክዳል።
አባትም ልጁን ለሞት አሣልፎ ይሠጣል አባት እናታቸውም ያሥገድሏቸዋል ለሠው ጠላቱ ቤተሠቡ ይሆናል።
=:=:=:=:=:=:=:=:=:=:=
በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ
አበያና ባለሞያ በሬዎች ይጠመዳሉ የሚሥበውን ይገርፉታል አብያውን ይተውታል በሬ የተባለ በሬ አይደለም ሠው ነው እንጂ ዋሥ ይከፈላል ባለእዳ ያመልጣል የሚያዘውም የለም
በዚያን ጊዜ ተጠበቁ
ብሉን ብሉን የሚሉ ጣፋጭ ወይንና ትርንጎ ይፈጠራሉ
ይናቃሉ እንጂ የሚበለቸው የለም ።እሬት መራራ ይበላሉ
ውይንና ትርንጎ የተባሉት ውይንና ትርንጎ አይደሉም
መጻሕፍትና ሊቃውንት መምህራን ናቸው ሢመክሩ
ሢያሥተምሩ ይንቊቸዋል እንጂ አይሠሟቸውም ።
በዚያ ጊዜ ተጠበቁ
በዚያን ጊዜ የምድር ባዳ አውሬዎች ቦታቸውን ትተው ወደ
ከተማ ይገባሉ አውሬ የተባሉ ባህታዊያን ናቸው ባህታዊያን
ነን ሢሉ የብህትውናን ሥራ አይሠሩም ጾም ጸሎት ሌሊት
መንቃት የለባቸውም ።
መነኮሣት ነን ሢሉ ከዚህ ሁሉ አንድ ሥራ አይሠሩም ፍቃደ
እግዚአብሔርን አይፈጽሙም ወንድማቸውን ባልንጀራቸውም
አይወዱም እንደ አለማዊ ሠው የዚህን አለም ሹመት ይሻሉ።
በረከቴን ፤ ቸርነቴን በምድር ለይ ሣፈሥ ይህንን ትተው
መራራ ይበላሉ የዛር ዘፈን ይወዳሉ ።በዚያን ዘመን ሠራዊቱም
፤ መኲንንቱም ፤ ነግሥታቱም ፤ህዝቡም ፤ደንቆሮውም
፤ብልሁም ፤ ንጹሁም፤እርኩሡም ፤ባሪያም፤ጌታም ለአጋንንት ያድራሉ ።
በሃጢያት በትእቢተ ይታጀራሉ ፍቅር ትህትና ሥለሌላቸው
ጸሎታቸው በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ የለውም እጣናቸው ወደ ሠማይ አያርግም ።
እነዚን ለመሣሠሉ ሁሉ የገነት ደጅ አይከፈትላቸውም ።
በዚያን ጊዜ ተጠበቁ
ቁራ ቀሚሥ ወደንገቱ ያጠልቃል ቁራ የተባለው ቁራ
አይደለም ቄሥ ነን የሚሉ መንፈሥ ቅዱሥ ያላደረባቸው ወደ
ቤተ ክርሥቲያን የማይሄዱ ይህንን አለም የሚወዱ
የእግዚአብሔር ምሥጋና ትተው የዚህን አለም የተከተሉ ህጌን
ትተው 3 ፤4 ሚሥት የሚያገቡ ለወንዱም ለሤቱም ሀሠት
የሚያሥተምሩ ባሥሜ የሚገዙትን በአምልኮቴ የሚቀኑትን
የሚንቁ ናቸው።
በዚያን ጊዜ ተጠበቁ
በዚያን ጊዜ ደንቆሮች ብልሆች ብልሆች ደንቆሮችይሆናሉ
። ውሃ አሻቅቦ ይፈሣል ውሃ አሻቅቦ ይሥፈሣል የተባለው
በማይገባቸው እኔ እነግሥ እኔ እነግሥ የሚሉ ናቸው እኔ
እግዚአብሔር የባህርይ ንጉሥ ሣለው ፤ የምገድል
፤የማነሣ፤የምቀጣ፤ የምምር ፤ የምሾም፤የምሽር ከሠማይ
በታች ከምድር በላይ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና።
ክፍል-4-ይቀጥላል......

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages