ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ቁጥር 10 መዝሙር አስመረቀ፡፡ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15

አትሮንስ ዘተዋሕዶ ብሎግ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን ጠብቆ በድምጽ፤ በምስልና በጽሑፍ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት የቀሲስ ንጋቱ አበበ ነው።

አትሮንስ ዘተዋሕዶ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትንና ደንብን ጠብቆ በድምጽ፤ በምስልና በጽሑፍ ዘገባዎችን በቀሲስ ንጋቱ አበበ ይቀርባሉ፡፡

አትሮንስ ዘተዋሕዶ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትንና ደንብን ጠብቆ በድምጽ፤ በምስልና በጽሑፍ ዘገባዎችን በቀሲስ ንጋቱ አበበ ይቀርባሉ፡፡

በቅርብ የተጻፉ

Home Top Ad

Post Top Ad

Monday, December 14, 2020

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ቁጥር 10 መዝሙር አስመረቀ፡፡

 “ ስምንቱን መዝሙር የሰራሁት ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ጋር Quarantine በነበርንበት ወቅት ነበር፡፡ ” ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

“ሊቀመዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍና አገልጋዮች በአጠቃላይ በያለንበት የሚደርሱ የቤተክርስቲያን ድምጽና የመንግስተ ሰማያት ጥሪ ናቸው” ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ
“ሊቀመዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ሙሉ ጊዜውን ለአገልግሎት የሚሰጥ ብርቱ አገልጋይ ነው፡፡ Quarantine በነበርንበት ወቅት አፉ ከማዜም ና ከመዘመር አያርፍም ነበር” መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
“ ጽንሱ ጤነኛ እንዲሆን እናትን መንከባከብ ግድ እንደሆነ ሁሉ አገልግሎትን ለማጠንከርና ለማግኘት አገልጋዮችን ማገዝና ማበረታታት ያስፈልጋል” መምህር ምህረተአብ አሰፋ
“ሊቀ መዘምራን ያልዘመራቸው ጉዳዮች አሉ ብሎ ደፍሮ ለመናገር ይከብዳል” መጋቤ ምስጢር ብሩክ አስማረ
ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ የዋህ፣ መልካም፣ ደግ፣ ሰው ወዳድና ሁሉ ዘመዱ የሆነ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ እጅግ ውብና ደማቅ በሆነ መርሐ ግብር ነው 10ኛ የመዝሙር ሲዲውን ያስመረቀው፡፡ ሊቀ መዘምራን ከልጅነቱ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ያደገና ቤተክርስቲያንን በብዙ ዝማሬዎቹ ያበለጸገ ልዩ የሰው መውደድ ያለውና ዝማሬዎቹ ሁሉ ልብን የሚገዙና የተለየ ጸጋ ያለው ድንቅ አገልጋይ ነው፡፡እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ይጠብቅልን፡፡ አሜን፡፡
No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages