ሚያዝያ ፲፩ ግጻዌ (ዐቢይ ጾም/ኒቆድሞስ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 23, 2021

ሚያዝያ ፲፩ ግጻዌ (ዐቢይ ጾም/ኒቆድሞስ


ስንክሳር:- ሚያዝያ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፣ቅድስት ታኦድራ ገዳማዊት፣አባ በኪሞስ ጻድቅ፣ ስምኦን ዘለምጽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ኤዺስ ቆዾስ
#ወር በገባ በ፲፩ የሚታሰቡ በዓላት ፣ቅዱስ ያሬድ ካህን
ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት፣ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና፣አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
 ቅድስት ታኦድራ ገዳማዊት 
በዚች ዕለት  ሚያዝያ ዐሥራ አንድ ቀን የከበረችና የነጻች እመሜኔት ታዖድራ አረፈች።ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ከታላላቆች ባለጸጎች ወገን ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ።እነርሱም ዋጋው ብዙ በሆነ በወርቅና በብር ያጌጡ የከበሩ ልብሶችን አሠሩለት ከእርስዋ በቀር ልጅ ስለሌላቸው ሊአጋቡአት እነርሱ ያስባሉና።
እርሷ ግን የምንኲስና ልብስ ለብሳ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ልትጋደል ትወዳለች መከራ መስቀሉንም ልትሸከም ትወድ ነበር የዚህን የኃላፊውን ሠርግ አልፈለገችም ።ከዚህም በኃላ የወላጆቿን ዕቃ ገንዘብ ወስዳ ለሚሸጥላት ሰጠችው ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተች በቀረውም ከእስክንድርያ ውጭ በስተምዕራብ አብያተ ክርስቲያናትን አነፀች።
ወደ እስክንድያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ አትናቴዎስም ሔዳ ራሷን ተላጭታ ከእርሱ ዘንድ መነኰሰች ።ከደናግል ገዳማትም ወደ አንዱ ገብታ በገድልም ተጸምዳ ጽነዕ ገድልን ተጋደለች አምላካዊ ራእይንም ታይ ዘንድ ተገባት መላእክትን ታያለችና የሰይጣናትንም ሥራቸውን ለይታ ታውቃለችና ለሠሩ የታሰቡትን የምታውቅበትና የምትፈትንበት እውቀት ተሰጣት።
ቅዱስ አትናቴዎስም በእርሷ ፈጽሞ ደስ ይለው ነበር ወደርሱም ይጠራታል እርሱም ሊጎበኛት ወደርሷ ይሔዳል ኀሳቧንም ትገልጥለታለች እርሱም የጠላት ደያብሎስን ወጥመዱንና ምትሐቱን ያስገነዝባታል።ከመንበረ ሢመቱ ከእስክንድርያ በአሳደዱትም ጊዜ ብዙዎች ድርሳናትን ጽፎ ላከላት።
ይቺም ቅድስት እጅግ እስከአረጀች ድረስ ኖረች በመንፈሳዊ ተጋድሎም የጸናች ናት እርስዋ ከአምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ተምራለችና ።እሊህም እለ እስክንድሮስ አትናቴዎስ ጴጥሮስ ጢሞቴዎስና ተዎፍሎስ ናቸው።
እንዲህም ብለው ጠየቋት ሰው ተርታ ነገር ቢናገር ዝም በል ሊሉት ወይም እንዳይሰሙት ጆሮአቸውን መክደን ይገባልን እንዲህም ብላ መለሰች ምንም ምን ሊሉት አይገባም ነገሩ ደስ እንዳላቸው ሆነው ዝም ይበሉ እንጂ ሰው ማዕዱን በፊትህ ቢያኖር በላይዋም በጎ የሆነና ብላሽ የሆነ ምግብ ቢያኖር ይህን ብላሹን ከእኔ ዘንድ አርቀው አልሻውም ልትለው አይቻልህም መጥፎውን ትተህ ከምትፈቅደው ትበላለህ እንጂ ያለ ትሕትና ያለ ጾምና ጸሎት ሰይጣንን ድል የሚነሣው የለም። አጠቃላይ ዕድሜዋም  መቶ ዓመት ሆኖዋት በሰላም አረፈች ጸሎቷ በረከቷ ከኛ ጋራ ለዘላለም ይኑር አሜን።
#በዘችም ቀን የጋዛ ኤጲስቆጶስ የዮሐንስ መታሰቢያው ነው ።ደግሞ የእስክንድርያው የአባ በኪሞስ የስምዖን ዘለምጽና እግዚአብሔርም በጸሎታቸው ለዘላለሙ ይማረን አሜን።
ሚያዝያ፣ ፲፩ ምንባባትና ቅዳሴ
__________________________
መልእክተ ጳውሎስ
ወደ ሮሜ ሰዎች ም. ፲፮ ቊ. ፩ - ፫
___________________________
መልዕክት
፪ኛ ዮሐ ፩፣ ፩-፲፩
______________
ግብረ ሐዋርያት
የሐዋርያት ሥራ ም. ፲፫ ቊ. ፲፮ - ፳፩
_____________________________
ምስባክ ዘቅዳሴ
______________
አዋልደ ንግሥት ለክብርከ
ወትቀወወም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት
መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፭ ቊ. ፱ - ፲፯
____________________________
፱ የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
፲ ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤
ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፯ ቊ. ፲፬ - ፳፬
_______________________________
የዕለቱ ቅዳሴ
__________
ዘእግዝትነ (ጎሥዓ)
 ወስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages