መስከረም 9 የሚከበሩ ቅዱሳን በዓላት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, September 19, 2022

መስከረም 9 የሚከበሩ ቅዱሳን በዓላት

በዚህች ቀን አባ ቢሶር አረፈ። በግብጽ መጺል በሚባል ቦታ አጲስ ቆጶስነት ተሹሞ ህዝቡን በፍቅር የጠበቀ ደገኛ አባት ነበር። እንዲህ ሆነ፤ ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ በሮም ነገሰ ክርስቲያኖችን ማሰቃየት ጀመረ፤ ይህ ወሬ በግብጽ ተሰማ አባ ቢሶርም በሰማዕትነት ለመሞት ወሰነ፤ ህዝቡንም በአውደ ምህርት ላይ ሰብስቦ የእግዚያብሔርን ትዕዛዛት በሙሉ አስተማራቸው እንዲጠብቁት አዘዛቸው ከዚህ በኃላ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ለመሞት እንደሚሄድም ነገራቸው፤ ሁሉም ተላቀሱ በጣም ይወዱት ነበርና እንዳይሄድ አጥብቀው ያዙት ሊያስቀሩት ግን አልቻሉም፤ ከእነርሱ ወጥቶ ሄደ በመኮንኑም ፊት ቆመ፤ በክርስቶስ እንደሚያምን ድምጹን አሰምቶ ተናገረ፤ ጣኦታቱንም ዘለፈ በዚህም ልዩ ልዩ መከራ አደረሱበት ይልቍንም ኤጲስ ቆጶስ መሆኑን ሲያውቁ ስቃዩን አጸኑበት በመጨረሻም በዛሬዋ ዕለት አንገቱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። በረከቱ ይደርብን።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages