"የኔታ ሲሳይ" - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, September 15, 2022

"የኔታ ሲሳይ"

ብዙ የድጓ መምህራንን አስተምረዋል። ድጓ እግዚአብሔርን በዜማ የማመስገንን ስልት የምናውቅበት ትምህርት ነው። እንዲያው በጨረፍታ መምህራንን እናስተዋውቅ ብዬ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ለቤተክርስቲያንም ለሀገርም የቆሙ ድንቅ ድንቅ እልፍ አእላፋት ሊቃውንት አሉ። የፌስቡኩ ትውልድ የሚያውቃቸው የዩቲይብ ሸቃዮችን ብቻ ነው። ያውም ደግሞ ብዙዎች ከግብረ ድቁና የዘለለ ምንም ያልተማሩ ሰዎችን። ነገር ግን ዝምታ ሲበዛ ዋኖቹ ሊቃውንት ተረስተው ጥቃቅኑ እንደትልቅ ታይተው ለቤተክርስቲያንም ለሀገርም ዋና ተደርገው ሲታሰቡ በጨረፍታ ዋኖችን ለማሳወቅ ያህል እንጂ ዘርዝሮ አሳውቆ መጨረስ አልችልም። ።ለኢትዮጵያም ለቤተክርስቲያንም የሚያስቡ ፌስቡክ ቴሌግራም ዩቲይብ በጠቅላላው ማህበራዊ ሚዲያ የማይጠቀሙ እልፍ አእላፋት ሊቃውንት አሉ። በረከታቸው ይደርብን። በዋናነት የሃይማኖት ትምህርትን ወደ ቤተክርስቲያን ቀርበን እንማር። አምላከ ሊቃውንት እግዚአብሔር ሊቃውንትን ይጠብቅልን።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages