የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ
ጉባኤ በተመረጡ ዘጠኝ ርዕሶች ዙሪያ የቡድን ውይይት በማድረግ
ላይ ነው።
ጥቅምት ፲ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
፵፩ኛው አጠቃላይ የሰበካ ዓለም አቀፍ መንፈሳዊ ጉባኤ የአህጉረ ስብከትና የድርጅቶችን ሪፖርት ሲያዳምጥ ከሰነበተ በኋላ በዛሬው ዕለት ቀደም ሲል በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት ማጠቃለያ ላይ የተገለጹትን የመወያያ ነጥቦች መነሻ በማድረግ ጉባኤተኛው በአራት ቡድን ማለትም ማቴዎስ ፣ማርቆስ፣ሉቃስና ዮሐንስ ተብለው በተመደቡ ቡድኖች አማካኝነት የቡድን ውይይት እያደረገ ይገኛል።
የቡድን ውይይቱ በቤተክርስቲያናችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ከአህጉረ ስብከት በተመረጡ ሥራ አስኪያጆች መሪነት የሚካሔድ ሲሆን ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊውም የቡድን ውይይቱን አጠቃላይ ሂደት እየተዘዋወሩ በመመልከት ላይ ናቸው።ከዚህ የቡድን ውይይት የሚገኘው ሀሳብ በየቡድን አወያዮቹ ለጠቅላላ ጉባኤው ከተገለጸና የአቋም
መግለጫው አካል በመሆን ከጸደቀ በኋላ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ሲጸድቅ የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ በመሆን ያገለግላል።
Source :
No comments:
Post a Comment