መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አስማረ፤ ለሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ቁጥር 10 መዝሙር የሰጡት አስተያየት - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15

(አትሮንስ ዘተዋሕዶ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው)

(አትሮንስ ዘተዋሕዶ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው)
በተጨማሪም አትሮንስ ዘተዋሕዶ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችና የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችንና ዜናዎችን ያቀርባል።

በቅርብ የተጻፉ

Home Top Ad

Post Top Ad

Monday, December 14, 2020

መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አስማረ፤ ለሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ቁጥር 10 መዝሙር የሰጡት አስተያየት

 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ቁጥር 10 የዝማሬ አልበምና የ25ኛ አመት የአገልግሎት ዘመናት።

መንፈሳዊ መዝሙር ቤተክርስቲያን ለልጆቿ ከምታወርሳቸው ሀብታት አንዱ ሲሆን ለአምልኮትም ታላቅ ድርሻ ያለው መሆኑ ግልጽ ነው :: መዝሙር ቅዱሳን ሊቃነ መላእክትና ሰራዊቶቻቸው ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርን ያለዕረፍት የሚያመሰግኑበት ነው :: መዝሙር ሰውና መላእክት ዘወትር ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ለማመስገን እንደተፈጠሩ እንዲያመሰግኑበትም የተሰጣቸው ልዩ ሀብት፣ ሰማያዊ ዜማ ነው::
እስራኤላውያን ከጥንት ጀምሮ ከጸሎትና መጽሐፍትን ከማንበብ ጋር መዝሙር በመዘመር እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩ እንዲሁም በመከራቸው ጊዜና ከድል በኋላ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን አስበው በመዝሙር ምስጋናን ያቀርቡ እንደነበር ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል
በሐዲስ ኪዳንም በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ከነበሩት ድንቅ መንፈሳዊ ገጽታዎች ቀዳሚውና ዋናው በምስጋና ለዘመናት ተለያይተው የነበሩ ሰውና መላእክት “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ :- ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” በሚል በአንድነት ምስጋና መዝሙር ነው።
መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያቱ ጋር ወደ ደብረዘይት ከመውጣታቸው በፊት መዝሙርን አስተምሯቸዋል፤ ዘምረዋልም (ማር ፲፬:፳፮):: ስለዚህም የመዝሙር አገልግሎት በቤተ ክርስቲያን ከጸሎት ከስግደት ከጾም ጋር በሥርዓተ አምልኮታችን ውስጥ ትልቅ ድርሻ አለው::
ወደ ሀገራችንም ስንመጣ የአማረኛ ዝማሬ የተጀመረበት ዘመን ስናጠና ገና መቶ አመትም ያልሞለው ሰሆን በዚህም አነስተኛ የዝማሬ እድሜ በዙ ሊቃውንት አባቶች ካህናት እንዲሁም ዲያቆናት የሰንበት ትምህርትቤት ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች ይህንን የምስጋውን
ሰልፍ ቶሎ መቀላቀል እንደቻሉ እናያለን። ከመጻሕፍት ቅዱስ ውስጥና እና ከቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰቶች የተውጣጡ እንዲሁም የተለያዩ የቤተክርስቲያን አባቶች ከደረሷቸው ድርሰትና ከተረጓሟቸው መጽሐፍት ግእዙን ወደ አማረኛ በመመለስ ለምእመናን እንደጸሎትም እንደ ትምህርትም ሆነው በማዘጋጀት እያገለገሉም ይገኛሉ።
ከነዚህ ዘማርያን መካከል በሊቀውንት ካህናትም ሆነ በምእመናን ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ወንድማችን ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ነው።
የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ትምህርት በዝማሬው በማስተዋወቅና የዘኑትን በማጽናናት እንዲሁም አዳዲስ በሥርአተ ቤተክርስቲያን ለሚጋቡ በዝማሬው እያደመቀ መለው የኢትዮጵያን ከተሟች በአፍሪካና በአውሮፖ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅና በአሜሪካ ባሉት ግዞቶች የክርስቶስን ተሸክሞ ቤተክርስቲያንን እያገለገለ እነሆ 25 አመት ደፈነ ። ይህም ሲባል የመጀመሪያ አልበሙን ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እንጂ ዘመኑን መሉ ከልጅነት እስከ ዛሬ ከቤተክርስቲያን አልተለየም። በነዚህ በ25 የአገልግሎት አመታት ያላነሳቸው ጉዳዮች አሉ ለማለት ይከብዳል። አምስቱን አእማደ ምስጢር ፣ሰባቱን ምስጢራተ ቤተክርስቲያን፣ ክበረ ቅዱሳንን ፣ ነገረ ማርያምን፣ ስርአተ ቤተክርስቲያንን ፣ነገረ መስቀሉን ፣እንዲሁም በሰው ልጆች ህይወት ያለውን ደስተና ሀዘን መግኘትና ማጣት ህመምና ጤና ሰላምና በረከት መውደቅና መነሳት የተዋህዶን የአገልግሎት ሩጫ ከሜዳ ሳያዛንፍ እና መስመሩን ሳይለቅ ለዚህ ለብር ኢዩቤልዩ ደርሷል።
ክቡራንና ክቡራት በዘንድሮም እንደቀደመው ሁሉ የቤተክርስቲያንን ስርአትእና የአባቶችን ትውፊት ያለቀቁ የሚያጽናነረ እና የሚያበረቱ መዝሙሮችን ለአስረኛ ጊዜ ዛሬ በብጹአን አባቶችና በእናንተ ፊት ለማስመረቅና በጸሎታችሁ እንድታግዙት ይህንን መርሀ ግብር አዘጋጅቷል ዘመኑ የቴክኖሎጂ እንደመሆኑ መጠን ብዙ መልካም ነገሮች ይዞ እንደመጣው ሁሉ ያዛን ያክል የሲዲ እና የካሴት ከገበያ መውጣት የኮፐፒ ራይትና ሌሎችም ጉዳዮች ተደራርበው ዝማሬው ላይ ከባድ ጥላ አጥልቶበት እናጠኛልን በዚህም የየተነሳ ብዙ ወንድሞችና እሕቶቾ መዝሙር ለመስራት ተቸግረው ይገኛሉ ። በዚ ህፈተና ሊቀመዘምራን ያለውን ተግዳሮት በመቋቋም ይህንን የምስጋና መዝሙር ስርተው ለዛሬ አድርሰውልናል። ረጅም ዕድሜና ቀሪው ያአገልግሎት ዘመን የተበረከ ይሁን እላለሁ።
መጋቤ ምስጢር ቡሩክ አሳመረ
ታህሳስ 4 2013 ዓመተ ምህረትNo comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages