ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, April 15, 2020

ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ †♥† አባ ዮሐንስ ሐጺር†♥† ( ጥቅምት ፳ አዕረፈ) †♥† “ከቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ.፻፲፭/፻፲፮፡፲፭ (115/116፡15 †♥† “እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡“ (እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“”†♥† መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8) †♥† በዚህች ቀን አባ ዮሐንስ ሐጺር አረፈ። ቁመቱ አጭር ስለሆነ ነው ዮሐንስ ሐጺር የተባለው። በ18 ዓመቱ በገዳመ አስቄጥስ መንኩሶ በተጋድሎ የኖረ ሲሆን ይህ አባት “ነጽሮተ ስሉስ ቅዱስ” የደረሰ አባት ነው። †♥†እዚህ ደረጃ የደረሱ አባቶች ቀና ቢሉ ሥላሴን ይመለከታሉ ዝቅ ቢሉ እንጦሮጦስን ያያሉ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን የገዳሙ አበምኔት ሊፈትነው ብሎ ደረቅ እንጨት ሰጠው ይህንን ተክለህ አለምልመህ ፍሬውን አምጣልኝ አለው። †♥†እርሱም እንጨቱን ተከለውና፤ 3 ዓመት ሙሉ ከሩቅ ቦታ ውሃ እየቀዳ አጠጣው። በ3ኛው ዓመት ጸደቀ፤ ለመለመ፤ ትልቅ ዛፍም ሆነ፤ ፍሬም አፈራ፤ መነኮሳቱ ይህ የትእግስት ውጤት ነው ብለው ፍሬውን ቀምሰውለታል፡፡ †♥†አንዲት “አትናስያ” የምትባል ሴት ነበረች። መጀመሪያ ጻድቅ ነበረች በኋላ ላይ በዝሙት ወደቀች ዘማዊም ሆነች። የቀድሞ ቅድስናዋን የሚያውቁ መነኮሳት ሊመክሯት ቢመጡ ሳቀችባቸው። አሁን ማንን እንላክ ብለው አሰቡ ዮሐንስ ሐጺርን ላኩት። ተራ ሰው መስሎ ገባ፤ ለዝሙት የመጣ መስሏት ተቀበለችው። ተጫወት አለችው ዮሐንስ ሐጺር ማልቀስ ጀመረ ምን ያስለቅስሃል ትለዋለች። †♥†መልክሽ ደስ ብሎኝ ይላታል፤ ደስ የሚል መልክ ያስቃል እንጂ መች ያስለቅሳል ትለዋለች። የለም ነገ ገሃነም እንደምትወርጂ ታይቶኝ ነው፤ አንድም ብዙ አጋንንት በሰውነትሽ ሲወጡ ሲወርዱ አያለሁ አላት። ደነገጠች ምን ይሻለኛል? ትለዋለች። ንስሃ ግቢ ማን ያስታርቀኛል ኃጢያቴ ብዙ ነው ትለዋለ። እኔ አስታርቀሻለሁ ተከተይኝ ብሎ ወጣ ልዋል ልደር ሳትል በሯን እንደተከፈተ ተከተለችው። በልስላሴ የኖረ እግር ተበጣጥሶ በበዙ ድካም ሲመሽ ከገዳሙ ደረሱ። †♥†የምታርፍበትን ቦታ ለይቶ ሰጣት፤ ሌሊት ለጸሎት ሲነሳ መላአክት ሲወጡ ሲወርዱ ያያል፤ ምንድን ነው ብሎ አንዱን መልአክ ይጠይቀዋል። ትላንትና አንተን ተከትላ የመጣችው ሴት ሞታ ነፍሷን እያሳረግን ነው ይለዋል። እግዚኦ ንስሃ ሳትገባ ብሎ ይደነግጣል። †♥† አንተን ልትከተል ገና አንድ እግሯን ከቤት ስታወጣ ኃጢያቷ በሙሉ ተፍቆላታል። አሁን ወደ ገነት እየወሰድናት ነው ይለዋል። ዮሐንስ ተገረመ፤ የመቃብሯስ ነገር አለው፤ አንበሶች ይመጣሉ ቦታውን ለካላቸው ይለዋል፤አንበሶች ቆፍረውለት ቀብሯታል። ዮሐንስ ሐጺርም በተጋድሎ ኖሮ በዛሬዋ ዕለት ማለትም ጥቅምት ፳ አርፏል፤ በረከቱ ረድኤቱ ይደርብን። “የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።” ያዕ.፭፡፲፮ (6፡16) †♥† ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡ †♥† በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ ምንጭ፡­- መጽሐፈ ስንክሳር

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages