ሃራጥቃው ተሃድሶ በሰንበት ትምህርት ቤት ላይ ጥርሱን ነክሷል። - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, September 16, 2022

ሃራጥቃው ተሃድሶ በሰንበት ትምህርት ቤት ላይ ጥርሱን ነክሷል።

ቤተ ክርስቲያናችንን በምንፍቅና አደጋ ላይ ለመጣል የእናት ጡት ነካሾች የፕሮቴስታንትን ተልዕኮ ተቀበለው በቤተ ክርስቲያናችን ሲንቀሳቀሱ ነበር። ተሃድሶ መናፍቃን የራሳችንን ሰዎች ተጠቅመው በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት የሰነዘሩ ቢሆንም የምንፍቅናውን ሴራ ለመከላከል በተደረገው ብርቱ ጥረት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ድርሻ ጉልህ ነው። ስለሆነም ሃራጥቃው ተሃድሶ በሰንበት ትምህርት ቤት ላይ ጥርሱን ነክሷል። አሁን ላይም በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ተሰግስገው ደም ወዝ እየተከፈላቸው በቀጥታ ሰንበት ትምህርት ቤትን የማዳከም ተልዕኮ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ ሃራጥቃዎች መኖራቸውን አውቀናል። ሰንበት ትምህርት ቤት የተሃድሶን ሴራ በማጋለጡ አሁን በሚታየው ነባራዊ ሁኔታ ተሃድሶ በህቡዕ ሰንበት ትምህርት ቤትን የማጥፋት ስልታዊ ስራ ላይ ተጠምዷል። ርዝራዥ የተሃድሶ ክንፍ በየትኛውም ደብር ተሰግስጎ የተመቻቸ ግዜና ምቹ ሁኔታዎችን እየተጠባበቀ ስለሆነ አብያተ ክርስቲያናትና ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንደ ከዚህ ቀደሙ የጥንቃቄ እርምጃ ቢወስዱ ተሻለ ነው እንላለን‼ በዚህ ጉዳይ ላይ ዝርዝር መረጃዎች ይኖሩናል‼

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages