የመነኩሴው የሴት ጅንጀና በድምጽ ቅጅ ያድምጡ፡ በመምህር ፋንታሁን ዋቄ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, October 9, 2026

የመነኩሴው የሴት ጅንጀና በድምጽ ቅጅ ያድምጡ፡ በመምህር ፋንታሁን ዋቄ



 #ፓትሪያሪክ አቡነ #ማትያስ እና የሚመሩት #ሲኖዶስ #አመንዝራዎችን አሰማርተው ሊያጠፉን ስውር ስምምነት ከጠላት ዲያብሎስ ጋር ካልተፈራረሙ በስተቀር ቀሊቀ ጳጳስ እስከ ዲያቆን ያለውን የአመንዝራዎች ስምሪት በአሁኑ 2019 ዓ.ም. ሲኖዶስ ጉበዔ #ያክቁምልን።ከቤተ መቅደሶቻችን አገልግሎት ከግዶ በምእመንነት ይመድብልን።

መነኩሴ ከበአቱ ወጥቶ በከተሜነት፣ በጎሰኝነት፣ በኢአማኒነት እና በሆድ ባርነት ሲያዝ እንደዚህ አመንዝራ ከመሆን አልፎ በተቀደሰውና በኃይል አድራጊው የእግዚአብሔር ወዳጆች መልዐኩ ቅዱስ ገብርኤልና በአምላክ እናት በቅድስት ድንግል ማርያም ስም "እናመንዝር" እያለ የተቀደሱና በጌታችን በመድኀኒታችን ክቡር ሥጋና ቅዱስ ደም የታተሙትን የክርስቶስ ታማኝ ምእመናንን ያረክሳሉ።
ክርስቲያኖች ይህን መልእክት ለቅዱስ ሲኖዶሱና ለሰብሳቢው ፓትሪያሪክ እንዲደርስ አጋሩት። ቤታችን ይጽዳ፣ የእግዚአብሔር የምህረት ዓይን ይመለስልን።
====
ተጠያቂ ማድረግ ያለብን ቀኖና ሐዋርያትን አፍርሰው እነዚህን ፈትተው ያሰማሩብንን ፓትሪያሪክና ጳጳሳቱን ነው።
ቀኖና ካላስከበሩ፣ የክርስቶስን የአካሉ ብልቶች የሆኑትን ምእመናን ቀድሶና አጽንቶ ለመንግሥቱ ከማብቃት በተቃራኒ በስለት ገንዘብ ደልበው ምእመናንን የሚያረክሱ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መልክ ከሚያጠፉ የከተማ ኮርማ ስመ መነኮሳትን ያሰማሩትን ጳጳሳት ተጠያቂ ናቸው።
ምእመናንንም ከጭብጨባና እልልታ ወጥተው በመተባበር ይህን ለማስተከከል በጳጳሳቱ መካከል ያሉትንም የሐሰት መነኮሳትና ባለ ቅምጥ ሁሉ በጭካኔ መመንጠር እንዲችሉ መግፋት እንጂ አንድ በሚዲያ የተጋለጠ ጋጠወጥ፣ ዘረኛና የታወቀ ሌባ መውቀስ መፍትሔ አይሆንም።
አሜሪካና አውሮፓ ሴት እየደፈረ ፖሊስ ሲፈልገው እያመለጠ 5 ከመሎ የሚመሽገው ፣ አዲስ አበባእና በየከተማው ቅምጥ እያማገጠ ብፁዕ፣ ሰው አስገድሎም ብፁዕ፣ ሰርቆም ብፁዕ እየተባባለ በርኩሰት የሚደራጅ የውስጥ እንቅፋቶችን "አባታችን" እየሠሉ መልመጥመጥ ክርስቲያናዊ ሕይወትም አይሰጥም፣ እምነትንም አይገልጽም።
ለወደቀውም ለምእመኑም መዳን ቀኖናውን ማስከበር ነው።
መስቀሌን ተሸክሞ የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም ያለው በስሙ የተጠመቅንበት እግዚአብሔር ወልድጰራሱ ነው።
👉 ካልከበድዎት ሙሉውን ደመፅ እዚህ ያድምጡ
https://t.me/defend_orthodoxy_EOTC_Followers/173954 ምንጭ፡ በመምህር ፋንታሁን ዋቄ የቀረበ ፌስቡክ አድራሻ https://www.facebook.com/reel/2211739696070765

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages