ሰሙነ ሕማማት ዘረቡዕ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, April 16, 2020

ሰሙነ ሕማማት ዘረቡዕ


 

  ለምን የምክር ቀን  ተባለ?   
የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ወይም የያዙበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት በመሆኑ፤ብዙውን ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱን የሚያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ-መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ.26፤1-5፣ ቁ14-16፣ ማር.14፤1-2 ቁ.10-11፣ ሉቃ 22፤1-6)
      
     
የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚህ ዕለት በቤተክርስቲያን ተሰብስበው ከእህል ከውኃ ተለይተው መላ ሰውነታቸውን የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ፣ ነገረ መስቀሉን የሚያወሳውን ሁሉ በመዘመርና በማንበብ እንዲሁም እስከ ሥርቀተ ኮከብ (እስከ ኮከብ መውጫ) በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከዚህ በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
                    መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል
ምክንያቱም ጌታችን ቢዘህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ቤጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ዘመኗን ሰውነቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ ዕፍረት፣ ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ያለዋጋ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፤ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ነው፡፡
                                     የዕንባ ቀንም ይባላል
          ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ (ማቴ.26፤6-13፣ ማር.14፤3-9፣ ዮሐ.12፤1-8) ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages