ወሎ /ቤተ አማራ/ ቦሩ ሜዳ ከደሴ ከተማ በቅርብ እርቀት የሚገኝ ሲሆን ታሪካዊው ቤተክርስቲያኑ ስራ የመጀመሩ ምክንያት በ1876 ዓ.ም በቦታው ላይ የተፈፀመ ተአምራዊ ታሪክ ይወስደናል በወቅቱ የሸዋው #ንጉስ_ምኒልክ እና የጎጃሙ #ንጉሥ_ተክለሐይማኖት በድንበር ምክንያት ተጣልተው እምባቦ ላይ ጦር መማዘዛቸውን የሰሙት አፄ ዮሐንስን ቦሩ ሜዳ ድረስ ሁለቱም ንጉስ መጤተው እንዲገናኞቸው ትእዛዝ አስተላለፉ።
ሶስቱም ንጉስ በቦሩ ሜዳ አርፈው በነበረ ወቅት በ1876 ዓ.ም መስከረም 10 ቀን ከሌሊቱ 5 ሰአት ላይ አንድ ተአምር ተከሰተ የአፄ ዮሀንስ ግዚያዊ ማረፊያ የነበረው ቤተመንግሥት ሌሊት ላይ በብርሀን ተሞላ በየሰፈሩ የነቀሩት ራስ ቢትወደድ ደጃዝማች ህዝቡ ሁሉ የንጉሱ ቤት ተቃጠለ ብለው ወደ እዛ ቢመጡም በብርሀን የተሞላ ነበር ጳጳሳቱም ንጉሶቹም በመደነቅ ሲያዩ አፄ ዮሐንስም "በእኔ ሀጢያተኛ ቤት ላይ እንዴት እንደዚህ አይነት ነገር ሊታይ ቻለ እንግዲህ ይሄ ቤት የሶስቱ ስላሴ መቀደሻ ቤት ይሁን " አሉ።
በነገታውም የሥላሴን ታቦት አስገብሀው ቦታውንም አበራ ሥላሴ ብለው ሰየሙት ግዚያዊ ቤተመንግሥት ተብሎ የተሰራው በቂ ባለመሆኑ ሌላ የተሻለ ህንፃ ቤተክርስቲያን እንዲሰራ አሰቡ ነገር ግን እሳቸው በተለያየ የሀገሪቱ ጉዳይ ስራ ስለበዛባቸው ለራስ ሚካኤል ሀላፊነቱን የሰጧቸው ።
ይሄ መቃረቢያ ቤተክርስቲያን በቁንዲ ተራራ ጫፍ የነበረ ሲሆን ህዝቡ ግን አተራራው ግርጌ የሰፈረ በመሆኑ ህዝቡ ተራራ በመውጣት እና በመውረድ የተቸገረ በመሆኑ ውሀም እንደ ልብ ባለመገኜቱ ያጤኑት ራስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከተራራው ወርድ አሁን ከሚገኝበት ምቹ ቦታ እንዲሰራ ወሰኑ በ1898 ዓ.ም አናጢዎች ከመንዝ እና ከበጌምድር በማስመጣት ማሳነፅ ጀመሩ።
ህዳር 30 ቀን 1940 ዓ.ም የታተመው ዜና የቤተክርስቲያን የተሰኜው ጋዜጣ እንደጠቀሰው ሙስሊሞችም ጨምሮ የአካባቢው ነዎሪዎች ግብአት በማቅረብ የጉልበት ስራ በማገዝ ምግብ በማዘጋጀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራቸው ከዛም በ1902 ዓ.ም ተመረቀ በዚህም ወቅት ብዙ ህዝብ እና መኳንንት ተገኝተዋል ራስ ገብረህይወት ሚካኤል ..ደጃዝማች አሊ ሚካኤል ...ራስ ወሌ ብጡል ..ራስ ጉግሳ ወሌ..የግሼኑ አለቃ መምህር ገብረ ሚካኤል ..የሐይቅ እስጢፋኖስ መምህር ዓምደ ስላሴ እና የተንታ ሚካኤል አለቃ አስካለ ይገኙባቸዋል ።
የቤተክርስቲያኑ አገልግሎት በአግባቡ እንዲከናወን ራስ ሚካኤል ከላስታና ከመንዝ እንዲሁም ከጎንደር መምህራን እና ካህናትን አስመጥተዋል በተለይም በቦታው ላይ ታላቁ #መምህር_አካለወልድ በኖራቸው ቦሩ ሜዳ ስላሴ የትምህርት መአካል እንዲኖር አድርጓል በዘመኑ 450 የማያንሱ ተማሪወች በቦታው ነበሩ ራስ ሚካኤል የተማሪወቹን ወጭ ሙሉ በሙሉ በመሸፈን የበኩላቸውን ድርሻ ተወጥተዋል።
ምንም እንኳን ይህን ትልቅ ቤተክርስቲያን 1944 ዓ.ም ፈርሶ #እቴጌ_መነን /የንጉስ ሚካል ልጅ የወይዘሮ ስህን ልጅ ናቸው/ በአዲስ ባሰሩት እንዲተካ ተደርጓል በዱሮው የቤተክርስቲያን ላይ ራስ ሚካኤል ያሳሏቸው የቤተክርስቲያን ስእሎች ደብዝተው ይገኛሉ ።
የዶክተር ምስጋናው ታደሰ መፅሐፍ
"ሚካኤል ንጉሥ ወሎ ወትግሬ"
No comments:
Post a Comment