#ጥንታዊቷ_እመ_ምዑዝ_ቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ_ገዳም_ወሎ_መቄት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, May 18, 2020

#ጥንታዊቷ_እመ_ምዑዝ_ቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ_ገዳም_ወሎ_መቄት

በሰሜን ወሎ/ቤተ አማራ/ ሀገረ ስብከት በመቄት ወረዳ ጥባ ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በምትባል ቦታ ላይ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህረት እና ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም ነች፡፡
ይህች ገዳም ከአዲስ አበባ በወልዲያ ወደ ባህርዳር በሚወስደው መንገድ 665 ኪሎ ሜትር ከወልዲያ 145 ኪሜ ከተጓዙ በኋላ ገረገራ /ፍላቂት/ ከምትባለው ከተማ በመውረድ በእግር 2፡30 /ሁለት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ/ እንድተጓዙ ከ400 ዓመት ዕድሜ በላይ ያስቆጠረቸውንና በስሚዛ የተሰራዉን በስመ እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህረት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በአንድ ቀን የሠራቻትና ለጌታ በአራቱም አቅጣጫ የሰገደችውን ታላቅና ድንቅ ቤተ መቅደስ ያገኛሉ ፡፡
እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህረት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳምም በዓላቶቿ የሚከበሩት ታህሳስ 16 የቅዳሴ ቤቷ እንዲሁም የካቲት 29 ቀን በዓለ እረፍቷ ይከበራል፡፡
ይህቺን ታላቅና ጥንታዊት ገዳም በመጎብኘት ከዚች ቅድስት እናት በረከትንና ረድኤትን እናፍስ ዘንድ አደራ እላለሁ፡፡
Image may contain: text, outdoor and nature

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages