መምህር ኤፍሬም ተስፉ ማርያም ቤዛዊት ዓለም አትባልም ላሉት ጳጳስ የሰጡት መልስ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, April 24, 2025

መምህር ኤፍሬም ተስፉ ማርያም ቤዛዊት ዓለም አትባልም ላሉት ጳጳስ የሰጡት መልስ



በመምህር ኤፍሬም ተስፉ

ቤዛ ነት ይተነተናል እንጅ አይከለከልም እንኳን ለቅደስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ማርያም ለወይዘሮ ቤዛም የተገባ ስም ነው። ቤዛማለት ምትክ፣ ለውጥ፣ ካሳ፣ ዋጋ፣ ዋስ ማለት ነው። በዚህ ስም የሚጠሩ ለውጤ፣ምትኬ፣ ዋሴ፣ ካሳየ የሚባሉ ስሞች ሁሉ በዶግማ ሊከለከሉ አይገባም።

 ቤዛነት ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሲነገር ዘዚአነ ሞተ ነስአ ወእንቲአሁ ሕይወተ ወሀበነ የኛን ሞት ወስዶ የርሱን ሕይወት ሰጠን ማለት ሲሆን ቤዛነቱ ሞት የተፈረደበት አዳም ሊቀበለው የተገባውን መከራ ተቀብሎ ግንድ ተሸክሞ በመስቀል ተቸንክሮ የአዳምን ሞት ሞቶ ሕይወት ስለሰጠን መለኮት ሥጋን ከተዋሐደ በኋላ ስለተቀበለው መከራ እኛን ስለማዳኑ ለወልድ ብቻ የሚያስተረጉም ለርሱ ብቻ የተሰጠው ስምነው። 

ክርስቶስ ቤዛ መባሉ በአዳም ለውጥ ሁለተኛ አዳም ሁኖ ስለተገለጠ ነው። ሞት በአዳም በኩል መጥቶ ሁሉን እንዳጠፋ ሕይወት በክርስቶስ ለሁሉ ደርሷልና ክርስቶስ ዳግማይ አዳም ይባላል። በዚህም መጠሪያው ቤዛ ኩሉ እንለዋለን። 

 ድንግል ማርያም ቤዛ ስትባል ደግሞ በሞቷ አዳነችን ደሟን አፍስሳ ነጻ አወጣችን ማለታችን አይደለም። የድንግል ማርያም ቤዛ መባል የሔዋን ምትክ የሔዋን ለውጥ ማለት ነው። ሔዋን የመርገም ድምጽ ሰምታ የሞት መጀመሪያ ቃኤልን ወለደች።ድንግል ማርያም ግን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤልን የብስራት ድምጽ ሰምታ የሕይወት መገኛ ክርስቶስን ወልዳለችና የሔዋን ለውጥ የሔዋን ምትክ ቤዛ ትባላለች። 

ቤዛ ኩሉ የምትባልበትም ሔዋን የሁሉ እናት እንደሆነች ድንግል ማርያምም እንድ ቅዱስ ዮሐንስ በመስቀሉ ሥር ለተገኙ ሁሉ እናት ናትና ቤዛ ኩሉ የምትባለው ለዚህ ነው። ሔዋን በዓለሙ ውድቀት ውስጥ ቀድማ እንደተገኘች ድንግል ማርያምም በዓለሙ ድኅነት ውስጥ ቀድማ የተገኘች ናትና በሔዋን ለውጥ ቤዛ ኩሉ ትባላላች። ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት ነው ብለን። ሆሲፒታል ላይ የሚታዘዙ መድኃኒቶች ስማቸው ይቀየር አንልም። 

 ግብር ለይተን እንናገራለን እንጅ አጅንዳው ስለተነሳ የተረዳኝን ለማስረዳት ጻፍኩ ።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages