እኔ በበኩሌ ፍኖተ ጽድቅ ሚዲያን እጅግ ዘለግ ባለ ጥርጣሬ እንድመለከተው ሆኛለሁ ። ብጹዕነታቸው አቡነ ገብርኤል በፍኖተ ጽድቅ ሚዲያ ስለ "ጸጋ" ብቻ አይደለም የተሳሳቱት ጥሩ ሌሎች ጉዳዮችም አሉ ።
በእውነቱ ከሆነ በአውደ ምህረት ላይ ቢሆን ይኸንን ያስተምሩ ነበር ወይ !? ብለን ብንጠይቅ አይሞክሩትም ባይ ነኝ ።
ለዚህ የተሳሳተ ትምህርታቸው መቼት ያደረጉት ፍኖተ ጽድቅ ሚዲያን ነው ። ይኸ ደግሞ በአጋጣሚ ሳይሆን ሆን ተብሎ ነው ነኝ ። ፍኖተ ጽድቅ ሚዲያ የገንዘብ ኃይል እንጂ የእግዚአብሔር ኃይል የራቀው ሚዲያ ነው ብለን ለመደምደም ጫፍ ደርሰናል ።
አስተውላችሁ ከሆነ ስለ ጸጋ የተሳሳተ ግንዛቤ ብጹዕነታቸው በሚያስተላልፉበት ወቅት እዚያው በፍኖተ ጽድቅ ሚዲያ የሥራ ድርሻ ያለው ስሙን ለጊዜው የዘነጋውት ጥቁር የሰባኪ ጋዎን የለበሰ ሰው ይስቅ ነበር ።
ሳቁም "ለዘመናት የተከማቸ ተረት የሆነ ትምህርት በብጹዕነታቸው ተደረመሰ" የሚል ተሃድሶአዊ ሳቅ ይመስላል ። ተሃዶሶዎች ሲስቁ እንዲህ ነው የሚስቁት ።
ለማንኛውም ብጹዕ አቡነ ገብርኤል እንወድዎታለን እናከብርዎታለን እኛ (ምዕመናን) የእናንተን ቅንጣት ታክል አቅም ፣ ዕውቀት ፣ ጸጋ እና ትጋት የለንም ። ነገር ግን በእርስዎ ትምህርት ጸረ ቤተ ክርስቲያን አቋማቸውን በየጊዜው የሚያንጸባርቁ ሰዎች በደስታ ሲቦርቁ በተቃራኒው ለዚህች ቤተ ክርስቲያን በኑሮም በዕውቀትም በሁለንተናቸውም ዋጋ የከፈሉ ኦርቶዶክሳዊያን ሲያዝኑ ተመልክተናል ።
ነገሩን ስንመረምረውም እጅግ አደገኛ እና እንኳን አንድ ሊቀ ጳጳስ ይቅርና ጀማሪ ሰባኪ ሊሳሳተው የማይችለውን ስህተት ነው የተሳሳቱት ። የምግባር ስህተት ቢሆን ይኸንን ያክል እርቀት ሄጄ በሊቀ ጳጳስ ላይ ለመጻፍ በፍጹም አልደፍርም ነበር ። ነገሩ ሃይማኖታዊ ሆነና እንዲህ ተዳፍረን ጻፍን ።
ለማንኛውም መምህር ያረጋል አበጋዝ ያሉትን እንስማ ። በነገራችን ላይ ይኸ የመምህር ያረጋል አበጋዝ ግሳጼ የተላለፈው በራሱ በፍኖተ ጽድቅ ሚዲያ እንደሆነ በቪዲዮ ላይ የሚታየው የፍኖተ ጽድቅ ሎጎ ያመለክታል ። ይኸ ጥሩ ጎናችሁ ነው ።
No comments:
Post a Comment