#ከወገብ_በላይ_እና_ከወገብ_በታች_ተንታ_ሚካኤል_1896ዓ_ም! - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, May 19, 2020

#ከወገብ_በላይ_እና_ከወገብ_በታች_ተንታ_ሚካኤል_1896ዓ_ም!


ይህ 116 አመት እድሜ ያለው ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ወሎ /ቤተ አማራ/ ተንታ የሚገኝ ሲሆን ከወገብ በታች እና ከወገብ በላይ ያለው ስራ በሁለት ባለሙያዎች በመሰራቱ አስተውለው ላዩት ይለያያል ከመሰረት ጀምሮ ከስከወገቡ ድረስ የሰራው #ከሃንጋሪ በመጣ መሀንድስ #ሙሴ_ቡኮዊች በሚባል ጥቅምት 8 ቀን በ1896 ዓ.ም ግንባታው ተጀመረ፡፡ሙሴ ቡኮዊችም በውስጥ ችግር ምክንያት ቤተክርስቲያኑን ሳይጨርሰው በ1898 ዓ.ም ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡እንደገና ንጉስ ሚካኤል ሌላ መሀንድስ በማፈላለግ #ከአረብ አገር #ፕርላንቲ የተባለ መሀንድስ አስመጥተው ከ19ዐዐ ዓ.ም ጀምሮ ማሰራት ቀጠሉ፡፡
የመጀመሪያ ክዳኑን ከአስቶዶስ /ሸክላ / መሰል ከድኖ ጀመረ ንጉስ ሚካኤል ካሳነጿቸው አብያተ ክርስቲያናት መካከል ተወዳዳሪ የሌለው የተንታ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ይገኛል፡፡ ይህንን ቤተ-ክርስቲያን ልዩ ከሚያደርጉት ዋነኛው የህንፃው አሰራር ውበት፣ ጥራትና በሶስት መቅደሶችና በሶስት ጉልላት ከመሰራቱም ሌላ የዚህ ታላቅ ንጉስ አጽም ያረፈውም በዚሁ ቤተክርስቲያን በመሆኑ ታሪካዊነቱን አጉልቶታል፡፡
ይህ ታላቅ ደብር ግንባታውም. 7 ዓመት ከ7 ወራት ከ7 ቀን ልክ በ7 ስዓት እንደተጠናቀቀ ይነገራል፡፡ ይህ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ስራው 7 ዓመት ከፈጀ በኋላ የካቲት 12 ቀን 19ዐ3 ዓ.ም ተጠናቆ ለመጀመሪያ ጊዜ በእለተ ሰንበት ጾለተ ቅዳሴ ተከናወነበት፡፡
በየአመቱም ህዳር 12 አመታዊ የቅዱስ ሚካኤል በአል ለማክበር ብዙ ምእመናን በቦታው በመገኜት ያከብራሉ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages