ስንክሳር: ሚያዝያ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
አቡነ ሳሙኤል ዘቆየጻ (ኢትዮዽያዊ) ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ ቅዱስ አቤሜሌክ ኢትዮዽያዊ
ቅዱስ ባሮክ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ዘኢየሩሳሌም
#ወርሐዊ በዓላት ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት) ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ቅዱስ ድሜጥሮስ
አባ እለእስክንድሮስ አረፈ
ሚያዝያ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አባ እለእስክንድሮስ አረፈ። ይህ ቅዱስም አስቀድሞ በቀጰዶቅያ አገር ኤጲስቆጶስነት ተሹሞ ነበር። እርሱም የከበሩ ቦታዎችን ተሳልሞ በረከት ተቀብሎ ወደ አገሩ ሊመለስ አስቦ ኢየሩሳሌም መጣ።
በኢየሩሳሌምም ስሙ በርኪሶስ የሚባል መቶ ዐሥር ዓመት የሆነው ጻድቅ ሰው ነበረ ሹመቱንም ሊተው ይወድ ነበረ ወገኖቹ ግን አልለቀቁትም ።
ቅዱስ እለእስክንድሮስም ሥራውን ፈጽሞ ወደ አገሩ ቀጰዶቅያ ሊመለስ በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ የሚል ቃል እነሆ ከሰማይ አሰማ። ወደ እገሌ በር ውጡ አስቀድሞ የሚገባውንም ይዛችሁ በላያችሁ ኤጲስቆጶስነት ሹሙት። ያን ጊዜም ሲወጡ አባ እለእስክንድሮስን አገኙትና ያዙት። እርሱም እኔ የቀጰዶቅያ ኤጲስቆጶስ ነኝ የክብር ባለቤት ክርስቶስ በእነርሱ ላይ የሾመኝን መንጋዎቼን ልተው አይቻለኝም አላቸው።
እነርሱም ከሰማይ ስለሰሙት ስለዚያ ቃል ስለርሱም እንደአመለከታቸው ነገሩት። ይህ ነገር ከእግዚአብሔር እንደሆነ በተረዳ ጊዜ ለበዓሉም የተሰበሰቡ አባቶች መከሩት ቃላቸውንም ተቀበለ ወደ ሀገሩ ቀጰዶቅያም እንዲህ ብሎ መልእክት ጽፎ ላካት። ይቅርታ አድርጉልኝ በእኔ ላይ አትዘኑ በእናንተ ላይም ኤጲስቆጶስ በእኔ ፈንታ ሹሙ እናንተም የተፈታችሁ ናችሁ ያቺን መልእክትም ከእርሱ ጋራ አብረው ከመጡ ከቀጰዶቅያ ሰዎች ጋራ ላከ።
ከዚህም በኋላ እየተራዳው አምስት ዓመት ያህል ከአባ በርኪሶስ ጋራ ኖረ። ከዚህም በኋላ ሽማግሌው አባ በርኪሶስ አረፈ። አባ እለእስክንድሮስም መንጋውን ተረክቦ እንደ ሐዋርያት በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው። ከሀዲ መክስምያኖስም በነገሠ ጊዜ ይህን አባት ይዞ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ አሠቃየው። ከዚያም በላዩ የሚያደርግበትን እስከሚያስብ ድረስ አሠረው። ጌታችንም ይህን ከሀዲ ፈጥኖ አጠፋው ወገኖቹም ይህን አባት እለእስክንድሮስን ከእሥር ቤት አወጡት።
ገርድያኖስም በነገሠ ጊዜ ጸጥታና ሰላም ሆነ ከክርስቲያን ወገኖች ላይም ጥቂት ወራት መከራው ጸጥ አለ። ገርድያኖስም በሞተ ጊዜ በርሱ ፈንታ አማኒ የሆነ ፊልጶስ ነገሠ። እርሱም በክብር ባለቤት በጌታችን ስለሚአምን በክብር ባለቤት በጌታ ክርስቶስ ሰም የታሠሩትን ምእመናንን ፈታቸው እጅግም አከበራቸው ይህም አባት በጸጥታ ኖረ።
ከዚህም በኋላ ከሀዲ ዳኬዎስ ተነሣ ፊልጶስንም ገድሎ መንግሥቱን ወሰደ ክርስቲያኖችንም እጅግ አሠቃያቸው ይህንንም አባት ያዘው ብዙዎችንም የቤተ ክርስተያን ሊቃውንት ጽኑ ሥቃይም አሠቃያቸው። ይልቁንም ይህን አባት አብዝቶ አሠቃየው ጽኑ ግርፋትንም ገርፎ ስለት በአላቸው በትሮች የጐኑ ዐጥንቶች ተሰብረው ወደሆዱ እስቲገቡ አስመታው።
ከዚህም በኋላ እስከ እሥር ቤት ጐትተው በዚያ እንዲጥሉት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። እግዚአብሔር ለመረጣቸው ያዘጋጀውን መንግሥተ ሰማይ እስከ ወረሰ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ እስከ ሰጠ ድረስ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየታመነ በዚያ ወድቆ ኖረ በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ
----------------------------
በዚችም ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ነቢዩ ኤርምያስ ላከው ጠባብና ረግረግ ከሆነ እሥር ቤት ሴዴቅያስ ንጉሥ በአሠረው ጊዜ የንጉሡ ባለሟልና የጭፍራ አለቃ የሆነው አቤሜሌክ አወጣው።
ያንጊዜም የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ መራራ ምርኮንም እንዳይቀምስ ኤርምያስ ነቢይ መረቀው እንዲሁም ሆነ። ስሳ ስድስት ዓመትም ተኝቶ ኖረ ከእርሱ ጋራ ወይንና በለስ ነበረ አልተለወጠም የእስራኤል ልጆች ከምርኮ እስቲመለሱ በለሱንም ከደብዳቤ ጋራ ወደ ኤርምያስ ባቢሎን አገር ላከው።
ስለዚህም የዚህን የከበረ መልአክ ሚካኤልን በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን መታሰቢያውን እንድናደርግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን አማላጅነቱ ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለም ይኑር አሜን።
#በዚችም ቀን የሀገር ጠመው ኤጲስቆጶስ የከበረ እንጦንስና የአውሳንዮስ መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለም ይኑር አሜን።
#በዚቺም ቀን መጥምቁ ዮሐንስ የተገለጠላቸው ጋይዮስና ኤስድሮስ አረፉ።በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
ሚያዝያ፣ ፲፪ ምንባባትና ቅዳሴ
=====================
መልእክተ ጳውሎስ
፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ም. ፬ ቊ. ፱ - ፲፮
______________________________
መልእክተ ጴጥሮስ
፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ም. ፪ ቊ. ፲፫ - ፲፮
__________________________________
ግብረ ሐዋርያት
የሐዋርያት ሥራ ም. ፳፬ ቊ. ፲፬ - ፳፪
_____________________________
ምስባክ ዘቅዳሴ
______________
አድኅነኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ
ወአውጽኣ እምቅሕ ለነፍስየ
ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ
መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፴፭ ቊ. ፮ - ፯
____________________________
፮ በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ።
፯ ከምድር ዳር ደመናትን ያወጣል፤ በዝናብ ጊዜ መብረቅን አደረገ፤ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል።
ምስባክ ዘነግህ
____________
ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ
ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ
ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር
መዝሙረ ዳዊት ም. ፴፬ ቊ. ፯ - ፰
___________________________
፯ የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።
፰ እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።
ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፬ ቊ. ፰ - ፳
______________________________
ወንጌል ዘነግህ
የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፬ ቊ. ፴ - ፴፮
_______________________________
የዕለቱ ቅዳሴ
_________
ያዕቆብ ዘሥሩግ (ተንሥኡ)
ወስብሐት ለእግዚአሜን።

No comments:
Post a Comment