አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ይህም አባት አስቀድሞ የእስክንድርያ አገር ቤተክርስቲያን መጋቢ ነበር ከእርሱም በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ሁሉም ኤጲስቆጶሳት መኳንንቱና ሊቃውንቱ ሕዝቡም በአንድ ምክር ተስማሙ በእግዚአብሔር ሕግ በመጽናት ያደረገው መልካም ተጋድሎውና ቅድስናው ስለርሱ ስለተነገረ መንፈስ ቅዱስም እንደ አደረበት ስለ ተረዱ ያለ ፈቃዱም ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና የክርስቶስን መንጋዎች በምክሩ፣ በትምህርቱ፣ በጸሎቱ ከዲያብሎስ ተኵ*ላዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው እሊህም ሃይማኖትን የሚለውጡ መና*ፍቃን ናቸው።
በሊቀ ጵጵስናውም ፯ት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
No comments:
Post a Comment