መልእክተ አትሮንስ ዘተዋሕዶ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, September 19, 2022

መልእክተ አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ
በዚህ የጡመራ መድረክ ነገረ ሃይማኖት፣ ነገገ ማርያም፤ ነገረ ቅዱሳን፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፤ ገዳማት፣ አድባራት፣ ቃለ መጠይቅ፣ ምክረ አበው፤ ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ የአብነት ት/ቤቶች፣ የፀበል ቦታዎች፣ ታሪካዊ ቦታዎች ፤ ቤተ መዘክሮች፣ አብያተ መፃሕፍት፣ ሰንበት ት/ቤቶች እና ሌሎችም መካነ ታሪኮች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን መዓዛ የሆኑ የቅዱሳን፣ ፃድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት፣ ነቢያት ሐዋርያት፣ አበው ወእማት፣ መምህራን፣ ሊቃውንት፣ ጳጳሳት፣ ወንድሞችና እህቶች አርአያነት ያላቸው ሰዎች ዜና መዋዕል፣ ገድል፣ ትሩፋት፣ ብሒል የሚዘከርበት የሀገራችን የሚንቀሳቀሱ እና የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ፤ በዓላት፤ ዕሴቶች እና ሌሎችም የሚዳሰሱበት ይሆናል፡፡ በዚህ የጡመራ መድረክ (Blogging site) የሚወጡትን የተለያዩ ጽሁፎችን፣ ሥዕሎችን፣ ቪዲዮዎችና የተለያዩ መረጃዎች የጡመራ መድረኩ ባለቤት በተለያየ ጊዜ ታትመው የወጡ መጻሕፍት፣ መጽሔት፣ ጋዜጣ፣ ዜና መዋዕሎች፣ በራሪ ወረቀቶች እና ድረ ገጾች (websites) በዋቢነት ከመጠቀሙም ባሻገር የተለያዩ ቦታዎችን በአካል በመሔድ የሚያደርጋቸው ቅኝቶች ግብዓቶች ናቸው፡፡ የጡመራ መድረኩ ተሳታፊዎች ወደፊት በሚሰጡት፣ የነቃ፣ የጎላ፣ እና የሰላ ምክር እና አስተያየት ለሁላችንም መልካም የትምህርት መድረክ እንደሚሆን ተስፋዬ ነው፡፡ የጅማሬም የፍፃሜም ባለቤት እግዚአብሔር ሁላችንም ያጽናን፡፡ የአባቶቻችን ዕምነታቸው ፀጋ በረከት ረድኤታቸው ጥርጥር የሌለባት ንጽሕት ተዋሕዶ ዕምነታቸው በእኛ ዘንድ ፀንታ ትኑር:: በቅድሚያ ልናውቅ የሚገባን ነገር አለ። እሱም ሃይማኖታችንን ጠንቅቀን ማወቅ እና ቅዱሳን አባቶቻችን የሄዱበትን የሃይማኖት መንገድ መከተል ነው። ለምሳሌ፤kየሕይወትና የክብር ባለቤት ወደ ሆነው የባህርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረጉትን ጉዞ የሚያሳይ ስለሆነ በዚህ ብሎግ ላይ የምናስተላልፋቸው መልእክቶች የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፤ ቀኖና እና ትውፊትን የጠበቀ ከመሆኑም በላይ ከአባቶቻችን የወረስናቸውን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የጠበቀ ትምህርት፤ መዝሙሮች፤ ስብከቶች፤ እና ሌሎች ጥሩ ምክር አዘል ቁም ነገሮችን አትሮንስ ታስተላልፋለች:: 1) ፍኖት ማለት መንገድ ማለት ነው:: በመጽሐፍ ቅዱስ የሰው ሕይወት በመንገድ ተመስሏል:: በመንገድ ላይ ሳለህ በጠላትህ እወቅበት ማለቱ በዚህ ዓለም ሕይወትህ በጠላት ዲያብሎስ ላይ ጠቢብ ሁንበት ማለት ነው:: ማቴ 5;25:: የሰው ሕይወት በመንገድ የተመሰለው በመንገድ ላይ አንዱ ሲወጣበት ሌላው አንዱ ሲወርድበት ሁሉም ወደ አሰበው ሲደርስበት እንደሚኖር ሁሉ በዚህ ዓለም ሕይወትም አንዱ ጽድቅ ሠርቶ ከክብር ወደ ክብር ሲሸጋገርበት ሌላው ደግሞ በሚያልፍ ዘመኑ ፍዳው የማያልፍ ኃጢአት ሲሠራ ኖሮ በወደደው ኃጢአት እንደ ጠፍ ጨረቃ ከክብር እያነሰ ስለሚሄድበት ነው:: ቅዱሳን መንገድ በተባለ በዚህ ዓለም ሕይወታቸው በጠላታቸው በዲያብሎስ ላይ አውቀውበት እርሱን ጠቅጥቀው አልፈው ለክብር የበቁ ሲሆን ይህ ብሎግም ይህንኑ የቅዱሳን ጥበብና ተጋድሎ በአጠቃላይም 2) ሰው የፈጣሪውን ሕግ በማፍረሱ ምክንያት ወደዚህ ዓለም ቀጥሎ ወደ አምላኩ የሚያደርሰውን እውነተኛ መንገድ አጥቶ አምስት ሽህ አምስት መቶ ዘመን ሲባዝን ኖረ:: ይህ ዓመተ ፍዳ ሲያልቅ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆኖ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ሰውን ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኘውን እውነተኛውን መንገድ አስተማረ:: ገላ 4;4:: እርሱም "አነ ውእቱ ፍኖተ ጽድቅ ወሕይወት - የጽድቅና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ" በማለት ከፈጣሪው አንድነት ተለይቶ ከክብር ተራቁቶ የነበረውን የሰው ልጅ ወደራሱ አንድነት ሊያዋህደው እንደመጣ አስረዳ:: እርሱን በፍጽም ሕይወታቸው ለሚመስሉት ወደ ሕይወትና ክብር የምትወስደውን ጠባብ መንገድ በቃል ያስተማረና በተግባር ሠርቶ ሥሩ ያለ ቅዱሳንን የጠራ የተቀበለና ያከበረ እውነተኛው ፍኖተ ቅዱሳን ኢየሱስ ክርስቶስ ለወዳጆቹ ያለውን ፍቅርና ተቆርቋነት እንዲሁም ያዘጋጀላቸውን ክብር ስለሚያስረዳ የአትሮንስ ብሎግ ጉዞአችን ቅዱሳን አባቶቻችን የተከተሉትን መንገድ መከተል ነው። 3) ነቢየ እግዚአብሔር ሆሴዕ "ይህን ነገር የሚያስተውል ጠቢብ የሚያውቃትም አስተዋ ማነው? የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነው ጻድቃንም ይሄዱበታል ተላላፊዎች ግን ይወድቁበታ" ብሎ የጻድቃንን እና የኃጥአንን መንገድ ልዩነት አስረድቷል:: ሆሴ 14:9 ጠቢቡ ሰሎሞን" የጻድቃን መንገድ እንደ ንጋት ብርሃን ነው ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል" ይላል ምሳ 4:18 ስለዚህ አትሮንስ ዘተዋሕዶ ብሎግ ጻድቃን የሄዱበትን ቅንና ርቱዕ የሆነውንና እግዚአብሔር ቅድስናን እና ፍጹምነትን ለሚሹ ያዘጋጀው መንገድ ስለሚያሳይ አትሮንስ ዘተዋሕዶ ብሎግ የምታስተላልፋቸውን ቁም ነገሮች በየጊዜው እንድትከታተሉ ስትል ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ለተጨማሪ መረጃ አትሮንስ ዘተዋሕዶ ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ:- 1. ድረ-ገጽ:- www.atronsmedia.com 2. ፌስ ቡክ ገጽ:- አትሮንስ ዘተዋሕዶ https://www.facebook.com/profile.php?id=100024269512002 3. ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/+g1P9CKSgY3A0OTAx 4.Youtube channel: https://www.youtube.com/channel/UCwApU3UcFfOaZx16y-oXx0A የቅዱሳን በረከታቸው እና ረድኤታቸው አይለየን::

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages