የወደፊቱ የግእዝ ዩኒቨርሲቲ ‼ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, October 31, 2022

የወደፊቱ የግእዝ ዩኒቨርሲቲ ‼

 


የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል "የባሕር ዳር ጽርሐ ጽዮን መንፈሳዊ ኮሌጅ " እንዲከፈት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ጉባኤ ላይ ውሳኔ በማሳለፉ የተሰማኝ ደስታ ታላቅ ነው፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቱን ከመንፈሳዊ ኮሌጁ ጋር በማስተሳሰር የግእዝን ቋንቋ ትምህርት የሚሳለጥበት የወደፊቱ የግእዝ ዮኒቨርሲቲ እንደሚሆን ተስፋዬ ታላቅ ነው ፡፡
ብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሃም ይህን እዚህ ለማድረስና የፕሮጀክቱ ግንባታው አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ያስቀመጡትን አሻራ ታሪክ አይረሳውም ፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ላይ የተሳተፋችሁ አሻራችሁን ያስቀመጣችሁ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ከክቡር ዋና ሥራ አስኪያጁ ጀምሮ ያላችሁ ሠራተኞች ፡ ሊቃውንት ፡ ካህናት ፡ የሰንበት ተማሪዎች ፡ መንፈሳዊ ማኅበራት ፡ ሁላችሁም ኦርቶዶክሳውያን ከሀገር ውጭ ፡ ከሀገር ውስጥ የምትገኙ በሙሉ ደስ ይበላችሁ ፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ ፡፡
ብፁዕ አባታችን ሆይ እንኳን ደስ አለዎ!

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages