የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ። - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15

አትሮንስ ዘተዋሕዶ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው::

አትሮንስ ዘተዋሕዶ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው::
ጥያቄና አስተያየት ካለ www.atronsvideo@gmail ያድርጉ

በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, October 25, 2022

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።


ጥቅምት ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም

አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

*የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን የመግቢያ መልዕክት አዳመጠ።
* ሰባት ብፁዓን አባቶችን በአጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ፤
*በአጀንዳ አርቃቂዎቹ የቀረቡትን ፳፪ አጀንዳዎች ተወያይቶ አጸደቀ፤
*በቅዱስ ሲኖዶስ ከጸደቁት ፳፪ አጀንዳዎች መካከል በዛሬው የጉባኤ ውሎው በሁለቱ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው እለት በጀመረው ዓመታዊ ጉባኤው የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትን የመክፈቻ መልዕክት እና የ፵፩ ኛውን ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን የአቋም መግለጫን በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ሰባት አባላትን ያቀፈ አጀንዳ አርቃቂ ብፁዓን አባቶችን ሰይሟል።የአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴው በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሰብሳቢነት የሚመራ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአስረጅነት ተሳትፈዋል። በአጀንዳ አርቃቂነትም፦
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል
ብፁዕ አቡነቴዎፍሎሰ
ብፁዕ አበነ ፊሊጶስ
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ(ሲያትል)
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በመሆን ተመርጠዋል። በአጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ብፁዓን አባቶችም ፳፪ የመወያያ አጀንዳዎችን ቀርጸው ለቅዱስ ሲንዶስ ምልአተ ጉባኤው አቅርበዋል።ቅዱስ ሲኖዶሱም ተዘጋጅተው በቀረቡት የመወያያ አጀንዳዎች ላይ ከመከረ በኋላ አጽድቋቸዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ የከሰአት በኋላ ውሎውም ከጸደቁት ፳፪ አጀንዳዎች መካከል ሁለቱን ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።ቀሪዎቹ አጀንዳዎችም በቀጣዮቹ ቀናት በቅደም ተከተል እየቀረቡ ውሳኔ እንደሚተላለፍባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል።
 Source:
  የ፵፩ ኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
 

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages