የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶችን ደንብ አጸደቀ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, October 29, 2022

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶችን ደንብ አጸደቀ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች ደንብ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጸደቀ።
 

ጥቅምት ፲፯፰ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ 
 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ምልአተ ጉባኤ በዛሬ ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻ ፲፭ ዓ.ም የጉባኤ ውሎው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶችን ደንብ በንባብ ካዳመጠ በኋላ ማስተካከያዎችን በማድረግ አጽድቆታል ።
 
የደንቡ መጽደቅ የቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡትን አገልግሎቶች በተሻለ አቅም ማከናወን የሚያስችላቸው ከመሆኑም በላይ ግልጽ የሆነ ደንብ ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በፍርድ ቤቶቹ አሰራር ውስጥ የሚስተዋሉትን የመፈጸምና የማስፈጸም ችግሮች በመቅረፍ ፍትሀዊ አሰራርን እንዲሰፍን የሚያደርግ በመሆኑ ፍርድ ቤቶቹ ትክክለኛና ውጤታማ ሥራ እንዲያከናውኑና አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ያደርጋቸዋል። 
 
ከዚህ በተጨማሪ ቅዱስ ሲኖዶስ አዳዲስ አህጉረ ስብከትን ለማቋቋም በቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን መመዘኛ ሰነድ መርምሮ ያጸደቀ በመሆኑ በመመዘኛው መሰረት አዳዲስ አህጉረ ስብከት የሚቋቋሙ ይሆናል።
በሌላ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሠራተኞች ደንብን በንባብ ያዳመጠ ሲሆን በነገው እለት ጉባኤው ውይይት በማድረግና መሻሻል የሚገባቸውን አንቀጾች በማሻሻል ካጸደቀው በኋላ። በቀሪ አጀንዳዎች ዙሪያ በመወያየት ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages