ስንክሳር ዘወርኀ መጋቢት 2 - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, March 10, 2023

ስንክሳር ዘወርኀ መጋቢት 2

 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

መጋቢት ሁለት በዚች ቀን የኒቅዮስ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አባ መከራዊ በሰማዕትነት ሞተ። የሮሀ አገር የሆነ የተሠወረውን የሚያይ ቅዱስ ጎርጎርዮስ አረፈ።

አቡነ ጎርጎርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት፡- ይኽም ቅዱስ በሌላኛው ስሙ ጎርጎርዮስ ዘሀገረ ሮሐ እየተባለ ይጠራል፡፡ ረዓዬ ኅቡዓት ማለት ምስጢራትን የተመለከተ ማለት ነው፡፡ ይህም ጻድቅና ሊቅ በቅዳሴው፣ በሃይማኖተ አበው፣ በስንክሳር፣ በገድለ ሰማዕታትና በገድለ ቅዱሳን ስሙ ተደጋግሞ ተጠቅሷል፡፡ በመጀመሪያ የክርስቲያኖች ጠላት የነበረ ሲሆን ዐመጸኛና ኃጥእ ነበረ፡፡

ክርስቲያኖችንም እየፈለገ ያሠቃይና ይገድል ነበር፡፡ አንድ ቀን ድንገት ሳያስበው መልአክ መጥቶ ነጥቆ ወስዶ የኃጥአንንም የመከራ ቦታዎችንና ሲኦልን አሳይቶ መልሶ አምጥቶ መሬት ላይ ሲጥለው እጅግ ደንግጦ በፍጹም ንስሓ ተመልሶ ሐዲሳትንና ብሉያትን ጠንቅቆ በመማር በብዙ ተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡
በሌላ ጊዜ አሁንም መልአኩ በረድኤት ተገልጦለት ነጥቆ ወስዶ ገነትን፣ ብሔረ ሕያዋንን፣ ብሔረ ብዑዓንን፣ መንግሥተ ሰማያን ሁሉ አሳየው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአመፁ ወደ እግዚአብሔር በንስሓ ተመልሶ መነኮሰ፡፡ በምንኩስናም ሆኖ በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ የተሰወረውን ሁሉ የሚያይ ቅዱስ አባት ሆነ፡፡ በሊቀ ጳጳስነት ተሾሞ በማገልገል ብዙ ጣዖታትን አፈራርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ፡፡ በመጨረሻም ሹመቱን በመተው በዓቱን አጽንቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ መጋቢት 2 ቀን በክብር ዐርፏል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!!!


መጋቢት 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት (ዘሃገረ ሮሃ)
2.አቡነ መክፈልተ ማርያም ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ)
3.አባ መከራዊ ዘሃገረ ኒቅዮስ (አረጋዊ: ጻድቅ: ጳጳስና ሰማዕት)

ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
4.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
5.ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
6.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
7.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages