ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን....... - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, March 2, 2023

ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን.......

 ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የነበረው ክብረ በዓል ሳይጠናቀቅ መቋረጡ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓል እና 127ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል ለማክበር በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን ተገኝቶ እያከበረ እንደነበረ መዘገባችን ይታወቃል።
ነገር ግን ታቦታተ ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው የዑደት ሥነ ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ክብረ በዓሉ እየተከናወነ ባለበት ወቅት ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ የበዓሉ ሥነ ሥርዓት ሳይጠናቀቅ ታቦታተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብራቸው መመለሳቸው ተገልጿል።
ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በሚያስገቡ ሁለቱም መግቢያ በሮች በተወረወረው አስለቃሽ ጭስ በርካታ ምዕመናን በመጎዳታቸው ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages