ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በጀርመን ከሙንስተር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ጋር ውይይት አደረጉ። - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, March 16, 2023

ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በጀርመን ከሙንስተር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ጋር ውይይት አደረጉ።
መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በጀርመን ሙንስትር ከተማ በመገኘት ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሙንስተርና አካባቢ ጳጳስ ከኾኑት ዶክተር ፊልክስ ጌን ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በውይይታቸውም ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ሁኔታ ለሊቀ ጳጳሱ በሰፊው አብራርተውላቸዋል።

በተጨማሪም ሀገረ ስብከቱ በጀርመን ለመመሥረት ባስበው ገዳም ዙርያና ይህንኑ አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያን በምትፈልገው ዕርዳታ ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

በሙንስተር ከተማ ስላለው የመንበረ ንግሥት በዓታ ለማርያም አጥቢያ ጉዳይም ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

በሁሉም ጉዳዮች የብፁዕነታቸውን ማብራሪያ የሰሙት ሊቀ ጳጳስ ዶ/ር ጌንም ጽሕፈት ቤታቸው በሁሉም ጉዳዮች ላይ በተቻለው ዐቅም አብሮ እንደሚሠራ፣ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግም ቃል ገብተውላቸዋል።

የሙንስተር ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት በጀርመን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከሚገኙት አኅጉረ ስብከት የኮለንን ሀገረ ስብከት ተከትሎ በሁለተኛ ደረጃ ብዙ ካቶሊካውያን የሚገኙበት ሀገረ ስብከት ነው። ዘገባው የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።

ምንጭ፤ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages