ማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎትን እሁድ ቢሮ በገቡ ሀላፊዎች ያሳገደው መግለጫ ይህ ነው - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Sunday, May 21, 2023

ማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎትን እሁድ ቢሮ በገቡ ሀላፊዎች ያሳገደው መግለጫ ይህ ነው

 " የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥን ጣቢያ " በመንግስት በጊዜያዊነት ታገደ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዛሬ እሁድ በፃፈው ደብዳቤ " ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ " ን በጊዜያዊነት እንዳገደ አሳውቋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም " ሰበር ዜና " በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሚና ውጪ በሆነ አግባብ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሄደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት ማሰራጨቱን አረጋግጫለሁ ብሏል።
ይህም የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን የሚተላለፍና በሀገር ሁለንተናዊ ሰላም ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል እንደሆነም ገልጿል።
ከጉዳዩ አጣዳፊነትና ሊያስከትለው ከሚችለው ጉዳት አንፃር በቀጣይ በባለሥልጣኑ ቦርድ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት የታገደ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በመገናኛ መረቡ " ሰበር ዜና " በሚል ያሰራጨው " ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ችግርን ለመቅረፍ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ " በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሂደት ላይ አወጥቶታል ያለውን መግለጫ ነው።

የግንቦት 2015 ዓ/ም ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከቀናቶች በፊት ተጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን በየዕለቱ በቤተክርስቲያኗ ቴሌቪዥን ዕለታዊ መረጃዎች/ውሳኔዎች ሲተላለፉ ነበር ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ጉባኤው መቋጫ አግንኝቶ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ለምዕመኑ የተሰጠ አጠቃላይ መግለጫ የለም።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages