በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኮሳት በኦነግ ሸኔ ተገደሉ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, February 23, 2024

በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኮሳት በኦነግ ሸኔ ተገደሉ

 በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን "ኦነግ ሸኔ" ብሎ የሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ፣
1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት
የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ገልጸዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሙ ጸጥታውን የሚያስከብረበት መሣሪያዎች በቡድኑ በመወረሳቸው ምክንያት ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ገዳሙ በከፍተኛ የጽጥታ ችግር ላይ መሆኑን እና ብቸኛው ተስፋውም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ብቻ እንደሆኑ ተነግሯል፤ በግፍ በጥይት ተደብድበው ለተገደሉት መነኮሳት አባቶቻችን ሰማዕታት በረከታችሁ ይደርብን እያልን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ግን ወደ ማን መጮኸ እንዳለብን መለየት ይኖርብናል፤ መንግሥት እና ቤተክህነት ግን መፍትሄ ያመጣሉ ማለት "ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ" ማለት ይመስለኛል።
በጎውን ጊዜ ያምጣልን፤ የሰማዕታቱ በረከት ይደርብን።

SOURCE፤ EOTC TV

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages