ከ2.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተገዛው የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉ ተገለጸ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, July 14, 2026

ከ2.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተገዛው የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉ ተገለጸ

በሚኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ውስጥ ባሳለፍነው ወርኃ ሚያዝያ ከ2.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገዝቶ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን መቃጠሉ ተገለጸ።
በሚያዛያ ወር ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረው የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሐምሌ ፮ የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ወርኃዊ በዓል የቅዳሴ አገልግሎት ከተፈጸመ በኋላ መቃጠሉ ተገልጿል።
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በቤተ ክርስቲያኑ ላይ በተከሰተው የእሳት አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸው በችግር ዙሪያ ከደብሩ ካህናት ጋር ውይይት አድርገዋል።
 ትናንት በሚኒሶታ ግዛት ሮዝማውንት ከተማ በሚገኘው የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰውን አሳዛኝ የእሳት አደጋ ተከትሎ፣ የሃይማኖት አባቶች በስፍራው በመገኘት ምዕመናኑን ማጽናናታቸውን ቀጥለዋል።
የደብሩን ካህናት እና ምዕመናን ለማጽናናት በቦታው ከተገኙት አባቶች መካከል፣ የሚኒሶታው ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ መጋቢ ምሥጢራት ቀሲስ ገብረማሪያም ጫኔ ይገኙበታል። ኃላፊው በስፍራው ለተገኙት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በሰጡት መግለጫ በደረሰው የንብረት ውድመት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው፤ ለቀጣይ የመልሶ ግንባታ ስራ ጠንካራ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
መጋቢ ምሥጢራት ቀሲስ ገብረማሪያም የተፈጠረው ክስተት እጅግ የሚያሳዝን እና ልብ የሚሰብር መሆኑን ጠቅሰው፣ አደጋው የዕለቱ መንፈሳዊ አገልግሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ባልታወቀ መንስኤ መነሳቱን ገልጸዋል።
"በእርግጥ ንብረት በመውደሙ እና የደብሩ መገልገያዎች ሙሉ በሙሉ በዛው በመቅረታቸው በጣም እናዝናለን፣ እናለቅሳለንም" ያሉት አባቱ፤ ነገር ግን በዚህ ከባድ አደጋ የትኛውም ምዕመን፣ አባት ወይም እህት ላይ የአካልና የህይወት ጉዳት ባለመድረሱ ፈጣሪን አመስግነዋል። "ሰው እስካልተጎዳ ድረስ ገንዘቡን አዋጥተን፣ ተረባርበን ዳግም እንገነባዋለን" ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በታሪኳ ፈተናዎችን እያለፈች፣ እየፈረሰች እና እንደገና እየታነጸች እዚህ መድረሷን ያስታወሱት ኃላፊው፣ "በፈተና የሚጸና የተባረከ ነውና ነገሮች ሁሉ ለበጎ ይደረጋሉ" በማለት ምዕመናኑ እንዳይዝሉ አበርትተዋል።
በሚኒሶታ እና በመላው ዓለም የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች በሙሉ ያጋጠማቸውን ሀዘን ወደ ጥንካሬ በመቀየር ለቤተክርስቲያኗ ግንባታ እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲነሱ ጥሪ አቅርበዋል። "ሁላችንም በአንድ ላይ ሆነን፣ ይህን ቤተክርስቲያን ከነበረበት በበለጠ መልኩ ሰርተን ያዘኑትን ክርስቲያኖች እናጽናናለን፤ እግዚአብሔርም ያግዘናል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን እና ታቦተ ቅድስት አርሴማን ወደ ክብራቸው እና ቦታቸው መመለስ ስላለብን፣ ሁላችንም በቁርጠኝነት እንድንሰራ በእግዚአብሔር ስም አሳስባለሁ" በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል
🙏 Please Keep Our Church in Your Prayers 🙏
Today, a devastating fire struck Minnesota Debre Bisrat St. Gabriel & St. Arsema Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Rosemount. The church building suffered severe damage, and the cause is under investigation. Thankfully, there have been no reports of injuries.
This church is more than a building—it’s a place of worship, faith, and community. During this difficult time, let’s come together in prayer and support our church family in any way we can.
Please keep everyone affected in your thoughts and prayers, and let’s stand united as a community.
Source/መረጃው የሀገረ ስብከቱ ነው።

 

                                                     

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages