ኦርቶዶክስን "ኦርቶዶክስ" የሚያሰኝው ዶግማ ቀኖና ገደል ገባ!!! መምህር ፋንታሁን ዋቄ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, July 17, 2026

ኦርቶዶክስን "ኦርቶዶክስ" የሚያሰኝው ዶግማ ቀኖና ገደል ገባ!!! መምህር ፋንታሁን ዋቄ

ኦርቶዶክስን "ኦርቶዶክስ" የሚያሰኝው ዶግማ ቀኖና ገደል ገባ!!! 
አዳዲሶቹ የጎሣ ጳጳሳት ሃይማኖተ አበው፣ መጽሐፈ መነኮሳትን፣ ሥርዓተ አበውን መጥቀስ ትተዋል። መከራከሪያቸው "እኔ ብቻ ነኝ። እንዴ እንዲህ ያደረግሁት? እንደዚህ የምኖርው እኔ ብቻ ነኝን? ልጅ ያለኝ እኔ ብቻ ነኝ? ከተማ የምኖር መነኩሴ እኔ ብቻ ነኝ? አሜሪካ ዋሺንገተን ዲሲ በርገር ከሚበላው፤ በአፊርካ ከተሞችና በአዲስ አበባ ከምንኖረው ሲነጻጸር ለምን ጉዳይ ይሆናል ውዘተ" በሚል ንጽጽራዊና አንጻራዊ አመክንዮ አምጥተው ቀኖና እና ዶግማውን ገደል ከተቱት። አመጣጣቸው በሆድና በፖለቲካ ነውና "አንተ ዋሽንግተን ዲሲ በርገር እየበላህ እየተንደላቀቅህ መነኩሴ ይውጣ ትላለህ። አንተ ውጣ ይላሉ። በዚሁ ውድቀት ውስጥ ብፁዕ የቀዱስ ሲኖድስ አባል፣ አባት እየተባለላቸው ከቀጠሉ በሚቀጥለው የምንሰማው
 1) "መነኩሴ ከሴት ጋር መተዳደፍ ያቁም" ሲባሉ መልሳቸው "አንተም ትማግጣለህ ፤አንተ እስክታቆም አናቆምም" 
(2) "ሰዶማዊ መኑክሴ ይወገዝ" ሲባል መልሳቸው "በሰለጠነው ዓለም ይደረጋል እና አንወገዝም" እንደሚሉ አትጠራጠሩ። 
እነዚህ ሁሉ "የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን" የሚለው ከግብር የተፋታ ቅጽል ግን እንደተንጠለጠለላቸው ይቀጥላሉ 
ምንጭ፡ መምህር ፋንታሁን ዋቄ እንደጻፉት (ከፌስ ቡክ መንደር) ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በአውደ ምሕረት እንዲህ አሉ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages