መማር ለሚፈልግ ሁሉ ሼር አድርጉለት
ከሰኞ ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምረን የቅዱስ ያሬድን ድጓ በአማርኛ እየተረጎምኩ በክፍል በክፍል እንማማራለን። ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ላይ ጥያቄ ያላችሁ ካላችሁም በቅደም ተከተል መጠየቅ ትችላላችሁ። ይህንን ክረምት ከድጓ ቀጥለን ዝክረ ቃል፣ መልክአ ጉባኤ፣ ሰዓታትና...በጠቅላላው በዜማ መጻሕፍት ዙሪያ ተሐድሶዎች ለሚያነሧቸው ጥያቄዎች መልስ እንሰጣለን። እነዚህ የዜማ መጻሕፍት ወንጌልን ምን ያህል ባማረ አገላለጽ እንደገለጹትና ትምህርታቸው ነገረ ክርስቶስ፣ ነገረ እግዚአብሔር፣ ነገረ ቅዱሳን መሆኑን መልካቸው መጽሐፍ ቅዱስን የመሰሉ አዋልድ መሆናቸውን በደንብ እያብራራን እንመለከታለን።
ከዚህ ቀደም ምዕራፍ ዘቅዱስ ያሬድን፣ ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድን፣ ዝማሬ ወመዋሥእት ዘቅዱስ ያሬድን ተማምረን ተጠያይቀን አልፈናል። እነዚህ ያመለጧችሁ ከነተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በPDF በቴሌግራም ቻናሌ አሉ። ገብታችሁ ማውረድ ትችላላችሁ። ትምህርቱ በfacebook እና በtelegram በጽሑፍ ይሰጣል። የአጫብር ድጓን፣ የቤተልሔም ድጓን፣ የቆሜ ድጓን ወይም የተመቻችሁን እያነበባችሁ ጠይቁ። እነዚህ በዜማው እንጂ በዘሩ ብዙም ስለማይራራቁ እኛ ደግሞ የምንማማረው ዜማውን ሳይሆን ምስጢሩን ስለሆነ ችግር የለውም።
© በትረ ማርያም አበባው ካሣ
የቴሌግራም ቻናሌ በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw ወይም ሊንኩ https://t.me/betremariyamabebaw ነው።
የዩቲይብ ቻናሌ ንሕነ ዘክርስቶስ We belong to Christ ወይም ሊንኩ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=GWc54SKTPg4RBlfN

No comments:
Post a Comment