ምሥጢረ ሥላሴ ክፍል ሁለት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, May 6, 2020

ምሥጢረ ሥላሴ ክፍል ሁለት




ምሥጢረ ሥላሴ ክፍል ሁለት
የአንድነትና ሦስትነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
ዘፍ 1፤1 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ  (አንድነቱን)
ዘፍ 1፤26 እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር (ሦስትነቱን)
ü እግዚአብሔርም አለ ሲል አንድነቱን
ü በመልካችን እንደ ምሳሌያችን ሲል ደግሞ ሦስትነቱን
አንድም
ü ንግበር  (እንፍጠር) ሲል ደግሞ የሦስትነቱን
ü እንደ አንድ ቃል ንግበር ሲል ደግሞ የአንድነቱን
ዘፍ 3፤22 እግዚአብሔርም አለ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ
ü እግዚአብሔርም አለ ሲል አንድነቱን   
ü ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ሲል ደግሞ ሦስትነቱን
ዘፍ 11፤7   ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው
ü ኑ እንውረድ የሚለው አንድ እግዚአብሔር
አንድም
ü ኑ እንውረድ የተባሉ ሁለትና ከዚያ በላይ እንዳሉ የሚጠቁም ሲሆን ሦስትነትን ያመለክታል
ü ሥላሴም ያንዱን ቋንቋ አንዱ እንዳይሰማው ወርደን ቋንቋቸውን እንደባልቀው አሉ
ዘፍ 18፤1   የእግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት ካለ በኋላ
ü አብርሃም የተመለከተው ሦስት መሆናቸው እግዚአብሔር አንድነት
ü ሦስት ሰዎች በፊቱ ያያቸው ደግሞ ሦስትነት ነው፡፡
ü ደግሞም አብርሃም በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ ማለቱ የአንድነቱን ይገልጻል
ü ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነህ አዘጋጅ ለውሺ እንጎቻም አድርጊ አላት
ü ሦስት መስፈሪያ ሦስትነቱ
ü አንድ ሆኖ መጋገሩ ደግሞ አንድነቱን ይገልጻል
ኢሳ 6፤3 አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮህ ነበር
ü የሠራዊት ጌታ ሲል አንድነቱን
ü ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ሲያመሰግኑ ሦስትነቱን ተናገሩ ቅዱስ የሚለው ቃል ዝቅ ብሎ ሁለት ከፍ ብሎ አራት አልሆነምና
ኢሳ 48፤16 ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ እኔ ከጥንት ጀምሬ በሥውር አልተናገርኩም ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል
ü ይህንን የተናገረው ተላኪ እግዚአብሔር ወልድ ሲሆን
ü እግዚአብሔር አብ ውረድ ተወለድ ብሎ ላከኝ መንፈስ ቅዱስም አዋሐደኝ ሲል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በየድርሻቸው በሦስትነት ተገልጸዋል
ü ወልድ ተወለደ
ü አብ ወልድን ወለደ መንፈስ ቅዱስን አሰረጸ
ü መንፈስ ቅዱስም ተዋሐደ
ማቴ 3፤16 ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ
ü በጥምቀት የእግዚአብሔር አንድነት የእግዚአብሔር ሦስትነት ታይቷል
ü አብ በደመና ሆኖ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው በተለየ አካሉ
ü ወልድ ሲጠመቅ በተለየ አካሉ በባሕረ ዮርዳኖስ
ü መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አምሳል በተለየ አካሉ
ማቴ 28፤19 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እያጠመቃችሁ  ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማርችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ
ü ስታጠምቋቸውም  በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ብላችሁ አጥምቋቸው
ü አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በግልጽ ይታያል
ሉቃ 1፤35 መል አኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል ሃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ካንቹ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል
ü የልዑል ሃይል ይጸልልሻል (አብ)
ü ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ( መንፈስ ቅዱስ)
ü መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ይመጣል (መንፈስ ቅዱስ)
ü በግልጥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል፡፡
ዮሐ 7፤28  እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር እኔንም ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴት እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው እነ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ ቦሎ ጮኸ
ü የላከው   አብ
ü የተላከው  ወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ)
ü ሁኔታው (ማስተማሩ) የመንፈስ ቅዱስ
ሐዋ 3፤14 ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል
ü አብ በስሜ የሚልከው ፡  አብ
ü ከእናንተ ጋር ሳለሁ ፤ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ
ü የሚልከው የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ፤ መንፈስ
1ኛ ቆሮ 13፤14  የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሒር ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን አሜን
ü የእግዚአብሔር ፍቅር፤  አብ
ü የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፤ ወልድ
ü የመንፈስ ቅዱስ አንድነት (ሕብረት)፤ መንፈስ ቅዱስ
1ኛ ቆሮ 12፤4  የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው፤ መንፈስ ግ ን አንድ ነው፤ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግ ን አንድ ነው፡፡
ü እግዚአብሔር ግ ን አንድ ነው፤ የእግዚአብሔር አብ
ü ጌታም አንድ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ
ü መንፈስ ቅዱስ አንድ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ (ጰራቅሊጦስ)
ኤፌ 4፤4 በመጠራታችሁ በአንድ ተሥፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መነስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ፡፡
ü የሁሉ አባት፤ አብ
ü አንድ ጌታ፤ ወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ)
ü አንድ መንፈስ፤ መንፈስ ቅዱስ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages