#ወሎ_ሐይቅ_እስጢፋኖስ_አቡነ_ኢየሱስ_ሞአ_ገዳም - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, May 19, 2020

#ወሎ_ሐይቅ_እስጢፋኖስ_አቡነ_ኢየሱስ_ሞአ_ገዳም


ዛሬ ህዳር 26 በታላቅ ድምቀት የተከበረው የአባታችን #ኢየሱስ_ሞአ የእረፍት ቀን ነው ገዳሙ የሚገኜው ወሎ/ቤተ አማራ/ ከደሴ 30 ኪሎሜትር እርቀት ሲሆን በሀይቅ ውሃ የተከበበ መሬት ነው።የመካከለኛው ዘመን ዩኒቨርስቲ" የሆነው
ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም አመሠራረቱ ከአቡነ ኢየሱስ ሞዓ መምጣት 300 ዓመታት ቀድሞ ነው።
(ገድለ አባ ኢየሱስ ሞአ፣ገጽ 33)
ሐይቅ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የተሠራው በ842 ዓ.ም.ነው።ሃይቅ እስጢፋኖስ ገዳም በአጼ ድልናኦድ ዘመነ መንግስት /908-918 ዓ.ም/ ከግብጽ አገር በመጡና በጊዜው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ #አባሰላማ በሚባሉ የሃይማኖት አባት አማካይነት ነው።
☞ አባ ኢየሱስ ሞአ የተወለዱት #ጎንደር ጎርጎራ ልዩ ስሙ ዳህና ሚካኤል ነው:: በ30 ዓመታቸው መንነው ደብረ ዳሞ ሄዱ በአባ ዮናኒ እጅም መነኮሱ በተጋድሎም ኖሩ::
ከዚያም ቅዱስ ገብርኤል እየመራቸው ሐይቅ እስጢፋኖስ መጡ::
በቤተክርስቲያንነት መመስረቱና በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደግሞ ወደገዳምነት እንደተሸጋገረ ይነገርለታል፡፡የመሰረቱት ካልዕ ሰላማ የተባሉ ግብጻዊ ጻድቅ ናቸው፤ ገዳሙን ከሰሩ በኃላ የማንን ታቦት እናስገባ ብለው ሲያስቡ ቶራ የምትባል እንስሳ ጭነት ተጭና ከመካከላቸው ተገኘች፤ ጭነቱን አውርደው ቢያዩት በሐር ጨርቅ የተጠቀለለ ሁለት ታቦት አገኙ አንዱ የእስጢፋኖስ አንዱ የጊዮርጊስ " ይህንን ታቦት በእ...የሩሳሌም የሚኖሩ የተሰወሩ ቅዱሳን ከእግዚያብሔር ታዘው የላኩት ነው" የሚል ጽሑፍም አገኙ ይላል። ይህ ከሆነ ከ 300 ዘመን በኃላ ነው አባ እየሱስ ሞኣ ወደዚህ ቦታ የመጡት ለ 52 ዓመት ቀን ቀን መንፈሳዊ ስራቸውን ይሰራሉ ሌሊት ሌሊት ሐይቁ ውስጥ ቆመው ሲጸልዩ ያድራሉ
አባ ኢየሱስ ሞዓ በሐይቅ እስጢፋኖስ በአበምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ከየገዳማቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን
በመገልበጥና በማስገልበጥ ብሎም በማሰባሰብ የመጀመርያው ዘመናዊ የቤተ ክርስቲያን ቤተ መጻሕፍት በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም እንዲቋቋም አድርገዋል፡፡ በዚሁ ገዳም ውስጥም የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ቋሚ ት/ ቤት በማቋቋም 8ዐዐ መነኮሳትን በትምህርተ ሃይማኖት አሠልጥነው በንቡረ ዕድነት ማዕረግ በመላ ሀገሪቱ
እንዲሠማሩ አድርገዋቸዋል፡፡ ከተማሪዎቻቸውም መካከል #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት (ዘደብረ ሊባኖስ)፣ ተክልዬን ያመነኮሱ አባት ናቸው። #አባ_ኂሩተ_አምላክ (ዘጣና ሐይቅ)፣ #አባ_ጊዮርጊስ (ዘጋሥጫ)፣ አባ ዘኢየሱስ፣
አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ አባ አሮን (ዘደብረ ዳሬት) ጥቂቶች ናቸው፡፡ #አፄ_ይኩኖ _አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት ያነፁት እርሳቸው ናቸው፡፡
በገዳሙ ውስጥ በተለያየ ጊዜ የነገሱ ነገስታት በስጦታ መልክ ያበረከቷቸው ውድ እቃዎች፣ ነዋዬ
ቅዱሳት፣ እጅግ በርካታ የብራና መፅሀፍት፣ ገድሎች ከእንጨትና ከድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ልዩ ልዩ
ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ወንጌላዊ ሉቃስ ከሳሏቸው አራቱ ስእለማርያም መካከል አንዷ በገዳሙ
መኖሯን የገዳሙ ኃላፊዎች ይገልፃሉ፡፡
ቀደምቱ ደጋ እስጢፋንኖስ በ 19ኛው ክፍለ ዘመን በእሳት ሲቃጠል አሁን የቆመው ቤ/ክርስቲያን በምትኩ ተሰርቷል። በዚህ ምክንያት ከታሪክ አንጻር የቤ/ክርስቲያኑ ዋና መስዕብ ሆኖ የሚቀርበው ሳይቃጠል የተረፈው ቤተ-መዘክሩ ነው። በዚህ መዘክር የ ይኩኖ አምላክ ፣ ቀዳማዊ ዳዊት ፣ ዘርአ ያዕቆብ ፣ ዘድንግል ፣ ፋሲለደስ ና
ባካፋ የደረቁ ቅሬቶች ይገኛሉ። አጼ ሃይለ ስላሴ በ 1951 ደሴቲቱን ከጎበኙ በኋላ የነገስታቱ እሬሳ በመስታውት ሳጥን እንዲቀመጥ አደረጉ። የፋሲለደስ ቅሪት ከሌሎቹ ነገስታት በበለጠ መልኩ እስካሁን ብዙ ሳይበላሽ በመቆየቱ የፊቱን መልክ ከቅሪቱ መገንዘብ ይቻላል።
የገዳሙ የወንዶች እና የሴቶች መነኩሳት ከሃይማኖታዊ ተግባራት ጎንለጎን ወንዶችም ሆነ ሴቶች በተለያዩ የልማት ሥራዎች በመሠማራት የመልካም ሥራ ማሳያና ማስተማሪያ ለመሆን በቅተዋል የራሳቸው የሆነ የእርሻ ቦታ ላይ በማረስ በማረስ እና አትክልት እና ፍራ ፍሬ በማልማት ሴቶቹም የተለያዩ እደ ጥበቦች በመስራት ለሌሎችም ገዳማት የሚሆን ልመናን የተፀየፈ ተግባር ይሰራሉ፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በሐይቅ እስጢፋኖስ አንድ ታላቅ ቤተ-መጽሐፍት አቋቁመው ነበር፥ራሳቸው አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ለሐይቅ እስጢፋኖስ 89 መጻሐፍት ሰጥተዋል።የገዳሙ ተማሪዎች ለትምህርትና ለጽሕፈት የተጉ እጅግ ጠቢባን ነበሩ።በዚህም ምክንያት ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም "የመካከለኛው ዘመን የሥነ-መለኮት ዩኒቨርስቲ"በመባል ይታወቃል።
በኋላኛው ዘመን የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት መላሽ የተባሉት ዐፄ ይኩኖ አምላክም የሐይቅ እስጢፋኖስ ተማሪ ነበሩ።
በእንዲህ ያለ ፍጹም ተጋድሎ ኖረው ህዳር 26 በዛሬዋ ቀን አርፈዋል፤ በዚህ ገዳም የሚከበሩ በዓላት መስከረም 15 የእስጢፋኖስ ፍልሰተ አጽሙ፤ ህዳር 26 የአባታችን እረፍት እንዲሁም ጥር 1 የእስጢፋኖስ እረፍቱ ናቸው፤ በእውነቱ የሚገርም የሚደንቅ ታላቅ ገዳም ። ቦታውን ለማየት ያብቃን የጻድቁ በረከትንም ያሳትፈን።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages