#አክሱም_ፅዮን_ማርያም_ትግራይ_ኢትዮጵያ - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ በድምጽ፤ በምስልና በጽሑፍ ዘገባዎችን ያቀርባሉ፡፡

አትሮንስ ዘተዋሕዶ ብሎግ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን ጠብቆ በድምጽ፤ በምስልና በጽሑፍ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ነው።

በመምህር ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ብሎግ ነው፡፡

በመምህር ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ብሎግ ነው፡፡

በቅርብ የተጻፉ

Home Top Ad

Post Top Ad

Tuesday, May 19, 2020

#አክሱም_ፅዮን_ማርያም_ትግራይ_ኢትዮጵያ


“አቢሲኒያውያን በእግዚአብሔር ጣቶች አሥርቱ ቃለት የተጻፈባት፣ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ያሉባት የቃል ኪዳኑ ታቦት አለቻቸው፡፡”
ብሎ የታሪክ ጸሐፊው አቡሳላህ በማለት ጽፎ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ #ኅዳር 21 ቀን በታላቅ ክብር ታከብረዋለች፡፡#በኢትዮጵያ ታሪክ ልዩ ሥፍራ ከያዙት ቦታዎች ግንባር ቀደምትዋ የአክሱም ከተማ ናት፡፡ አክሱም #የኢትዮጵያ የታሪክና የሃይማኖት እናት ከተማ ስትሆን ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2ሺ ዓ.ዓ. እንደተቆረቆረች መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ #አክሱም የቤተ ክህነቱም ሆነ የቤተ መንግሥቱ ማዕከል በመሆን ለብዙ ዘመናት አገልግላለች፡፡ በተለይም እግዚአብሔር ለሊቀ ነቢያተ ሙሴ የሰጠው የታቦተ ጽዮን መንበር በመሆኗ ከተማዋን ድንቅ ሁኔታን ያጎናጽፋታል በዚሁ ዕለት #የእመቤታችን ወዳጆች ምእመናን በዓሉን ለማክበርና ለመሳለም ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በብዛት ይገሠግሳሉ፡፡ ዕጣን፡ ጧፍ፡ ዘቢብ መባውን ይሰጣሉ፡፡ ካህናቱም ከዋዜማው ጀምረው በከበሮና በጸናጽል ስብሐተ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፡፡ በድርሳነ ጽዮን መጽሐፍ ካህናቱ እንደተገለጠው በጽዮን ፊት እንደየመዓርጋቸው ቆመው “እግትዋ ለጽዮን ወህቅፍዋ” የሚለውን መዝሙር ከዳዊት እያወጣጡ ይጸልያሉ፡ ይዘምራሉ፡፡ ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ የታቦተ ጽዮንን ተራዳኢነት በምእመናን ፊት ይመሰክራሉ፡፡

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages