፨፨፨፨፨፨ፍካሬ ኢየሱስ፨፨፨፨፨፨
(ማቴ ምዕ 24 ንና ምዕ 25 ን ሙሉውን ያንብቡ።)
አቤት የዚያን ጊዜ ክርሥቶሥ ሢመጣ፣
ትንሹም ትልቁም መድረሻውን ሢያጣ፨
"" ዘመኑ ቀርቧልና ይህን መፀሐፍ የሚያነብው የትንቢቱን ቃል የሚሠሙትና በውስጥ የተፃፈውን የሚጠብቁት በፁሃን ናቸው! ""
፨፨፨፨ፍካሬ ኢየሱስ-ክፍል- 1፨፨፨
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
በመለኮቱ ኅልፈት የሌለበት በአካል በግብር ሦስት በመለኮት በባሕርይ በሕልውና በአገዛዝ በሥልጣን ትክክል በመሆን ለዘለዓለም ህያው ሆኖ የሚኖር የነገሥታት ንጉሥ የገዥዎች ገዢ በሰማይ በምድር በሁሉ ፍጥረታት ሁሉ አንደበት ለዘወትር የሚመሰገን አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አምነን ፍካሬ ኢየሱስን መፃፍ እጀምራለሁ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጌታ ሐዋርያትን በደብረ ዘይት ሰብስቧቸው ሳለ በኋለኛው ዘመን በሚመጣው ትውልድ የሚደረገው ምልክቱስ ምንድር ነው እስኪ ንገረን ብለው ጌታችንን ለመኑት ጌታም መለሰላቸው አላቸውም ወዳጆቼ ሆይ በኋለኛው ዘመን ለሚመጣው ክፋት ምልክት ዢራታማ ኮከብ ይፈጠራሉ ያን ጊዜ በያገሩ ጭንቀት ይሆናል ሹም ከሹም ፣ ንጉስ ከንጉሥ ይጋጫል የበረዶ ድንጋይ ፣የእሳት ዲን ይዘንባል።
ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በዚያን ጊዜ እኔ ክርስቶስ ነኝ በማለት በስሜ ይመጣሉ ብዙዎችንም ያሳስታሉ ጦርነት የጦርነት ድምፅ በየአህጉሩ ይነሣል ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ ዳሩ ግን መጨረሻው አደለም ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግስት በመንግሥት ላይ በጠላትነት ይነሳል።
ረሃብ ቸነፈር የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል እነዚህ ሁሉ የምጥ የጣር መጀመሪያ ናቸው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨በዛን ጊዜ ተጠንቀቁ፨
በዚያን ጊዜ ብዙ ሰዎች ይሰነካከላሉ እርስ በእርሳቸው ለሞት አሳልፈው ይሰጣጣሉ ከዓመፅና ከተንኮል የተነሣ በሰዎች መካከል ፍቅር ትጠፋለች መተማመን አይኖርም አንዱም አንዱን እንደ አውሬ ይመለከተዋል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ፨
ለአህዛብ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ ይህ የመንግስት ወንጌል በዓለሙ ሁሉ ይሰበካል በዚያን ጊዜ መጨረሻው ይመጣል እናንተ ግን ተጠንቅቃችሁ ጠብቁት።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በዚያን ጊዜ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያልሆነ ከእንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል በዚያም ወራት ላሉ ለእርጉዞችና ለነፍሰ ጡሮች እንዲሁም ለእመጫቶችና ለሚያጠቡ ሁሉ ወዮላቸው እነዚያ ቀኖችስ ስለደጋጎችና ስለተመረጡ ሰዎች ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ የለበሰ ሁሉ አንዳችም ባልዳነም ነበር እንግዲህ ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት ተግታችሁ ፀልዩ።
ትዕዛዜን አክብሩ ቃሌንም ጠብቁ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በዚያን ጊዜ ብዙ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞ ነብያቶች ይነሣሉና ማንም እነሆ ክርስቶስ በዚህ አለ ወይም ከዚያ ነው ቢሏችሁ አትመኑ ብዙ ድንቅና ታላላቅም ምልክቶች በማሳየት የተመረጡትን ለማሳት ይሞክራሉ እንግዲህ እነሆ አስቀድሜ ነገርኋችሁ ክርስቶስ በበርሃ ነው ወይም በእልፍኝ አለ ቢሏችሁ አትቀበሏቸው የሰው ልጅ መብረቅ ከምስራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ ነውና። ( ዘመኑ ቀርቧልና ይህን መፀሐፍ የሚያነብው የትንቢቱን ቃል የሚሠሙትና በውስጥ የተፃፈውን የሚጠብቁት በፁሃን ናቸው!)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨በዚያን ሰዓት ተጠንቀቁ፨
ምሳሌውን ከበለሲቱ ተማሩ ጫፏ ሲያቆጠቁጥ ቅጠሏም ሲለመልም በዚያን ጊዜ ጊዜው እንደቀረበ ትረዳላች እንዲሁም ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደደረሰ ዕወቁ ዕውነት እላቸዋለሁ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ አያልፍም።
ከዚያም ወራት መከራ በውኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም ከዋክብትም ኋይላት ይናወጣሉ በዚያም ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ የሰውም ልጅም በታላቅ ኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል መላእክቱም በታላቅ የመለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በዛን ጊዜ ከዓመፅና ከተንኮል የተነሳ በምድር ላለ ሁሉ ይቅርታ የለም የኔን ገናናነት አላወቁምና ነገር ግን ወደኔ ቢመለሱ እና ንሰሐ ቢገቡ እኔም ይቅር እላቸዋለሁ። ወደኔ ግን ባይመለሱ እኔም ፊቴን ከርሳቸው እመልሳለሁ። ኤሳው ብኩርናውን ለመብል እንደሸጠ በረከትንም እንዳጣ እለዚያም በመንፈስ ቅዱስ የሰጠኋቸውን ልጅነት ለአምልኮ ጣዖት ይለውጡታልና።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ፨
በዚያን ጊዜ ሐሜት ትዕቢት ስድብ ራስንመውደድና ማክበር መማለጃ ወይም ጉቦ ተቀብሎ ፍርድ ማጣመም ገንዘብ መቀማት ወንድምን መግደል በሐሰት መመስከር መስረቅ ሐሰት መናገር ድንበር ማፍረስ ወሰን መግፋት አጥር መስበር ይበዛል ወንድም ወንድሙን ለገንዘብ ይለውጣል ፍቅርም ከነርሱ ይርቃል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ፨
በዚያን ጊዜ ሴቶች ለባሎቻቸው አይታዘዙም ታዛዦችም ለአዛዣቸው አይታዘዙም
ሴቶች በስልጣን ወንበር ላይ መቀመጥን ይወዳሉ ሴቶችም በወንድ መሳሪያ ያጌጣሉ
እንዲህም ይላሉ "በዳኝነት ተቀምጠን ፍርድ እንፍረድ ይላሉ።
ሴት የተናገረችው ለባሏ አይጥመውም ባልዋ የተናገረውም ለሚስቱ አይጥማትም። የባልዋን ፈቃድ አትሠራውም። ባልዋ ስለ ንብረቱ ይታገሣል። ፈቃዱን ታደርግ ዘንድ እሺ ብትለው ለጊዜው ደስ ይለዋል እምቢ ብትለውም ስለ ንብረቱ እያዘነ ይኖራል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ ፨
በዚያን ጊዜ ከሀብታቸውና
ከብልፅግናቸው የተነሳ የእግዚአብሔርን መኖር ይዘነጋሉ እህላቸውን የሚያደልቡበት ሰፊ ጎተራ ለመስራት ገንዘባቸውንና ወርቃቸውን የሚያከማቹበት ከፍተኛ ሳጥን ለማዘጋጀት ይፋጠናሉ ነፍሳቸውንም ለብዙ ዘመን የሚበቃሽ የደለበ እህል የተከማቸ ወርቅና ገንዘብ አለሽና ከእንግዲ ዓርፈሽ ብይ ጠጪ ደስም ይበልሽ ይሏታል ነገር ግን ባላሰቡበት ሰዓትና ጊዜ ሞት ነፍሳቸውን ነጥቆ ይወስዳታል ያደለቡትና ያከማቹች ሀብት ለማንም ይሆናል፡፡ እግዚአብሔርን ያላሰበ በባለጠግነቱም ብዛት የተማመነ ዕድሉ እንዲሁ ይሆናል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨በዚያን ጊዜ ተጠንቀቁ ፨
የሰው ህይወት በገንዘብ ብዛት አይጠበቅም በሀብቱም መደርጀት ዕድሜው አይረዝምም ከሞትም አያመልጥም ለሀብት ከመጎምጀቱና ከከንቱ ምኞት ተጠበቁ፡፡
ሉቃስ12: 13
ለምትበሉትና ለምትጠጡት ወይም ለምትለብሱትና ለምታጌጡት አጥብቃችሁ አትጨነቁ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ አይዘሩም አያጭዱም ዕቃ ቤት ወይም ጎተራ የላቸውም ምግባቸውን ከእግዚአብሔር ያገኛሉ፡፡
እንዲሁም አበባዎችን እዩ አይደክሙምም አይፈትሉም ነገር ግን እላችኀለሁ ጥበበኛውና አስተዋዩ ሰሎሞን ስንኳ በክብሩ ከነዚህ እንደአንዲቱ አለበሰም እንግዲህ ከሰማይ አሞሮችና ከበረሃ አበቦች ምን ያህል ብልጫ እንዳላችሁ ከእግዚአብሄርም ዘንድ የቱን ያህል ክብር እንደተሰጣችሁ አስቡ ከእናተ መካከል ተጨንቆና ተጠቦ በቁመቱ ላይ አንዲት ስንዝር መጨመር የሚቻለው ማነው እንግዲያውስ ቲኒሹን ነገር ለማድረግ የማይቻላችሁ ከሆነ ስለሌላው አትጨነቁ፡፡
ሉቃስ12:24
ከዓመት ልብሳችሁ ከዕለት ጉርሳችሁ የተረፋችሁን ለነዳያን መፅውቱ ከሀብታችሁ ቀንሳችሁ ከርስታችሁ ቆርሳችሁ ለበጎአድራጎት ስጡ ከዚያ ሌባ በማይሠርቀው ነቀዝ በማያበላሸው ብል በማይበላው ሰማያዊ መዝገብ ይከማችላችኀል ስለዚህም ተግባር ወገባችሁ የታጠቀ ጆሯችሁ የነቃ ዓይናችሁ የበራ ይሁን የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና፡፡
ክፍል-2-ይቀጥላል.......
No comments:
Post a Comment