ደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ጎንደር - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, June 6, 2020

ደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ጎንደር


ሰንበት ት/ቤት ዘጎንደር



እናስተዋውቃችሁ- ፮
🍂የሰ/ት/ቤቱ ሥም :- ደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን /መንበረ ጵጵስና
🍂ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ጊዜ :- በ 1633ዓ/ም ዓ.ም በአፄ ፋሲለደስ ሲሆን ከጎንደር አርባ አራቱ ታቦታት አንዱ ነው፡፡
🍂ዓመታዊ ክብረ በዓል፦ ታህሳስ 19፣ታህሳስ22፣ሰኔ 26 ፣ሐምሌ 19
🍂ሰ/ት/ቤቱ የተመሠረተበት ጊዜ:- 1974 ዓ/ም
🍂መገኛ ሀገረ ስብከት:-በማ/ጎንደር ሀገረ ስብከት በጎንደር ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት
🍂የቤተ ክርስቲያኑ አድራሻ፤ ጎንደር ዞብል ክፍለ ከተማ፤ ገብርኤል ቀበሌ 14
🍂የሰንበት ት/ቤቱ የጉባዔ አከፋፈል፤ የህጻናት፣ማዕከላውያንና የአዋቂዎች
፩/የህፃናት ጉባኤ መርሐ ግብሮች-
➡️ለ/ቅዳሜና እሁድ ከ4፡00-6፡00 መደበኛ የጉባዔ መርሐ ግብር
➡️ሀ/ማክሰኞ ከ 11:30-12:30 መዝሙር ጥናት
፪/ ማዕከላውያን መርሐ ግብር
➡️ሀ/ሀሙስ እና ቅዳሜ ከ11:30-12:30 የተከታታይ ትምህርት
➡️ለ/ሰኞና ማክሰኞ ከ 11:30-12:30 መዝሙር ጥናት
➡️መ/እሁድ ከ7:00-9:00 መደበኛ መርሐ ግብር
፫/ የአዋቂዎች ጉባኤ መርሐ ግብሮች
➡️ሀ/ የሁሉም የአገልግሎት ክፍሎች በራሳቸው የሚያዘጋጁት ጉባዔ በየ ወሩ/ የስነ ጽሁፍ ቀን፣ዝክረ ቅዱስ ያሬድ፣የህጻናት ቀን ወ.ዘ.ተ/ ሁሉም በዓመት 3 ጊዜ ይደርሳቸዋል/
➡️ለ/መንፈሳዊ ሥልጠና ከሰኞ-አርብ ከ11:30-12:30
➡️ሐ/የቤተሰብ ውይይት መርሐ ግብር ሀሙሰ ከ11:30-12:30
➡️መ/ተከታታይ ትምህርት ቅዳሜ ከ9:00-11:00
➡️ሠ/የመደበኛ መርሐ ግብር እሁድ ከ9:00-11:00
➡️ረ/ የሴቶች ጉባዔ በየ አራት ወሩ
➡️ሰ/የሠራተኞች ጉባዔ በየወሩ/በ19/
፬/ የሁሉም የጋራ መርሐ ግብሮች
➡️የመሐረነ አብ ጸሎት መርሐ ግብር ረቡዕና አርብ በሠርክ ከ11:30-12:30
➡️የአብነት ትምህርት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 12:00-1:30
➡️የሁሉም የውስጥ የጋራ አንድነት ጉባዔ በየ 3 ወሩ
➡️የአባ ደቅስዮስና የቅዱስ ገብርኤል ጽዋ መርሐ ግብር በወር አንድ ጊዜ
➡️የወላጆች ጉባዔ በዓመት 02 ጊዜ
🍂በደብሩ የሚገኙ የአብነት ት/ቤቶች
➡️፩/የቅኔ ትምህርት ቤት
➡️፬/የላይ ቤት አቋቋም ትምህርት ቤት
➡️፫/የቅዳሴ ትምህርት ቤት
➡️፬/የድጓ ትምህርት ቤት
🍂የደብሩ አዋሳኞች
➡️በምስራቅ:- መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤ/ን
➡️በምዕራብ:- ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
➡️በሰሜን:- ደብረ ጉባዔ ዳረገንዳ ኤዎስጣቴዎስ ቤ/ን/ብልኮ
➡️በደቡብ:-አውቶ ፓርኮ
🍂ከሰ/ት/ቤቱ አርያአነት ያለው ተሞክሮ ፤
፩/ ሰንበት ት/ቤቱ በ3 አደረጃጃት በሥራ አመራር፣ሥራ አስፈጻሚና በአገልግሎት ክፍሎች የሚመራ መሆኑ
፪/ በአባላት ክፍል የሚመራ የምክርና የምክክር አገልግሎት መኖሩ
፫/ የአብነት ትምህርት በቋሚነት የሚሰጥ መሆኑ እና ራሱን ችሎ በክፍል የተዋቀረ መሆኑ
፬/ ሁሉም አገልግሎት ክፍሎች የየራሳቸው ሥራ አስፈጻሚዎች ያላቸው መሆኑ
፭/ ያሬዳዊ ወረብ/ዜማ /ለዘብ/ በከፍተኛ ትኩረት ጥናት የሚደረግ መሆኑ
፮/ የበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በሥፋት የሚሰራ መሆኑ / ለነዳያን እንክብካቤ ማድረግ ፣ ረዳት የሌላቸውን ወደ ሥራ ማስገባት፣ቤት ለቤት የአቅመ ደካሞችን ቤት መጠገን፣ ፣ እስረኞችን ማጽናናት ወ.ዘ.ተ/
፯/ንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ ያለው መሆኑ
፰/ ዓመቱን በሙሉ ተከታታይ መንፈሳዊ ሥልጠናዎችን የሚሰጥ መሆኑ/12ኛ ዙር ደርሷል/
፲/ ሥራ አመራር አባላት የሚመረጡበት ሂደት እንደ ሐዋሪያት ቅዳሴ ተቀድሶ በዕጣ የሚከናወን መሆኑ፡፡
➡️የሰ/ት/ቤቱ ሥራ አመራር ሰብሳቢ፦አቶ አፈራ ጌታሁን 251968363646 እና ሥራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ አበበ ፀጋው 2518224661

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages