ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ!!! - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, June 2, 2021

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ!!!

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ!!!
በጉብኝቱ መርኃ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የሚኒሶታና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የአትላንታና ጆርጂያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የዳላስና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የደንቨር ኮሎራዶ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ አቡነ በርናባስ የሰሜን ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የዋሽንግተንና ሲያትል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የጣልያንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ወለጋና ሆረጉደሩ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ❖ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ፣ ❖ ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሣ የዩኒቨርስቲው ምክትል አካዳሚክ ፕሬዚዳንት፣ ❖ ሊቀ አእላፍ ኢያሱ ናሁሠናይ/ቀሲስ/ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት፣ ❖ የዩኒቨርስቲው ፋክልቲ ዲኖች፣ ❖ የዩኒቨርስቲው ማኅበረ ሰብ፣ ❖ አጠቃላይ የዩኒቨርስቲው ደቀ መዛሙርት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ግንቦት 24/2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አጠቀላይ የጉብኝት መርኃ ግብር ተካሂዷል፡፡ በጉብኝቱ መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲው ሕንፃዎች፣ የደቀ ማዘሙርት ማደሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ዲጂታል ቤተ መፃሕፍት ፣ ተጨማሪ የአብነት ት/ቤት (Extra Curriculum) እና ሲሳይ የመንፈሳዊ ዜማ መሣሪያ ትምህርት ቤት (ማሰልጣኛ) ተጎብኝተዋል፡፡ ከጉብኝቱ መርሃ ግብር በኋላ በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ቢሮ ከ11፡00 እስከ ምሽቱ 12፡30 ሰዓት ውይይት እና ምክክር የተካሄደ ሲሁን ዩኒቨርስቲው የቅዱሳን ፓትርያርኮች፣ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መፍለቂያ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በተለይም በዩኒቨርስቲው ተምረው ለሊቀ ጵጵስና ማዕርግ የበቁት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በዩኒቨርሲቲው የነበራቸውን የ5 ዓመታት ቆይታ እና አገልግሎት ዘመን በጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ ለተገኙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና እንግዶች ልምዳቸውን አካፍለዋል ፡፡ በተለይም የዩኒቨርሲቲው ፍሬ ከሆኑት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እንደ ገለፁት ዩኒቨርሲቲው ከዓለም ዓቀፍ እና ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲዎች እና ግብረ ሠናይ ድርጅቶ በጋራ መሥራት እንዳለበትና ለዚሁ የሚያግዝ ራሱ የቻለ ቢሮ በዩኒቨርሲቲው መከፈት አለበት ብለዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፍሬ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሆነው እንዲመረጡ ብፁዕነታቸው ያደረጉትን አስተዋጽዖ ገልፀዋል፡፡ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ በጀት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚመድብ ገልፀው ቅዱስ ሲኖዶስም ለቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የተሻለ በጀት በመበጀት ለመማር ማስተማሩ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበት ገልፀው ለዩኒቨርስው እድገት በጋራ አብረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡ በጉብኙቱ መርሃ ግብር ላይ ለተገኙት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ጥሪውን አክብረው ዩኒቨርሲቲውን በመጎብኘታቸው እና የደረሰበትን የእድገት ደረጃ በማየታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸውላቸዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባደረጉት ንግግር ለብዙ ዓመታት በመማር ማስተማር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው አንጋፋውና ታሪካዊው ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲን በመጎብኘታቸው እና ዩኒቨርሲቲው በዚሁ ደረጃ አድጎ በማየታቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ከገለፁ በኋላ፤ ከዚሁ የበለጠ ዩኒቨርሲቲውን ለማጠናከር አብረው እንደሚሠሩ እና እንደሚያግዙ ቃል ገብተዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ ሲሳይ የመንፈሳዊ ዜማ መሣሪያ ትምህርት ቤት /ማሰልጣኛ ተቋም በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት መርኃ ግብር ለተገኙት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና እንግዶች የበገና መጽሐፍ በስጦታ አበርክቷል፡፡ በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ከሰጡ በኋላ የዕለቱን መርሃ ግብር በጸሎት ተዘግቷል፡፡ በተመሳሳይ ዜና ከሁለት ሣምንታት በፊት በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋባዥነትና መሪነት ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች እና ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ማለትም ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር፣ ዶ/ር ሣሙኤል ኡርቃቶ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር፣ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሣው የባህና ቱሪዝም ሚኒስትር፣ ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ፣ ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዩ የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ፣የጠቅላይ ሚኒስተሩ የኢኮኖሚ አማካሪ፣ አቶ ተካ በለጠ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፣ የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፌድራል ፍርድ ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ድርጅት የመጡ የሥራ ኃላፊዎች ዩኒቨርስቲው መጎብኘታውና ወደ ፊት ዩኒቨርሲቲውን ከዚሁ የበለጠ ለማጠናከር አብረው እንደሚሠሩ፣ በተለይም ከ15 እስከ 20 ዓመት የሚያገለግል ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀትና ግቢውን ለማስዋብ በሚደረገው እንቅስቃሴ በግንባር ቀደም እንደሚሳተፉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ ፦www.htu.edu.et/

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages