ዜና ዕረፍት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, March 10, 2023

ዜና ዕረፍት

 ከ40 በላይ ወንበር ዘርግተው ያስተማሩት የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔት የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ!!





(መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ )
በርካታ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስተምረው ያበቁት ታላቁ የአቋቋሙ ሊቅና የጸሎት አባት የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔት የኔታ መምህር ሐረገ ወይን ምሕረቱ በ99 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።
መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5:00 ላይ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ከበዋቸው እያሉ ነፍሳቸው ወደፈጣሪዋ አርጋለች ሲሉ አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸዋል።
የኔታ ሐረገ ወይን ከአርባ ዓመት በላይ ወንበር ዘርግተው ያስተማሩ፣ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ጊዜ ያክል ለጳጳስና ቢጠየቁም ምንኩስናዬ ይበቃኛል በማለት በዓታቸውን ያጸኑ ጸሎተኛ አባት እንደነበሩም ተገልጿል።
ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱ ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ:-
1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages