ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ 20 - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, May 2, 2023

ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ 20

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም


ሚያዝያ ሃያ በዚህች ቀን ደንደራ ከሚባል አገር ደግሞ እልበደራ ከሚባል አገር ቅዱስ በብኑዳ በሰማዕትነት አረፈ። ይህ ቅዱስ ለብቻው የሚኖር ዕውነተኛ ተጋዳይ ነው የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጦለት የመቀደሻ ልብስ ለብሰህ ወርደህ ለመኰንኑ ተገለጥለት አለው።
በዚያን ጊዜ መኰንኑ አርያኖስ ከመርከብ ወርዶ ወደዚያች አገር ወደብ መድረሻው ጊዜ ነበር። ይህንንም ባሕታዊ ፈልጎት አላገኘውም ነበር ። እነሆ ቅዱስ በብኑዳም በፈቃዱ መጥቶ ወደ መኰንኑ ሔዶ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን በግልጥ እኔ ክርስቲያን ነኝ ብሎ በታላቅ ቃል ጮኸ።
መኰንኑም ፈልጎ ያጣው የታወቀ ባሕታዊ መሆኑን በአወቀ ጊዜ እንዲአሠቃዩት በእግር ብረትም አሥረው ከጨለማ ቤት እንዲጥሉት አዘዘ። በዚያን ጊዜም ብርሃን ወጣ የእግዚአብሔር መልአክም ከሕማሙ ፈወሰው አበረታው አጽናናውም።
በዚያችም አገር ስሙ ቄርሎስ የሚባል ምእመን ሰው ነበረ ከእርሱ ጋራም ሚስቱና ዐሥራ ሁለት ጐልማሶች ልጆቹ አሉ። እነዚህን ሁሉንም የከበረ በብኑዳ አስተማራቸው አጽናንቷቸውም ራሶቻቸውን ቆርጠዋቸው በሰማዕትነት ሙተው አክሊልን ተቀበሉ።
አርያኖስም ተቆጥቶ በቅዱሱ አንገት ከባድ ደንጊያ ሰቅለው ወደ ባሕር ይጥሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ በእግዚአብሔር ኃይልም ከድንጋዩ ጋራ ዋኘ። ደግሞ ከሰሌን ዛፍ ላይ ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ ያቺም ሰሌን ዐሥራ ሁለት ዘለላን አፍርታ ለመጪው ትውልድም መታሰቢያ ሆነች።
ከዚህም በኋላ የከበረች ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages