አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መኰንኑም በቀስቶች እንዲነድፏቸው አዘዘ ግን ቀስቶች አልነኳቸውም። ሁለተኛም እሳትን አንድደው በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው ጌታም መልአኩን ልኮ አዳናቸው።
ከዚህም በኋላ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው ከቀርጥስ ከተማ እስከ ይምንሑር አገር ድረስ ይጐትቷቸው ዘንድ አዘዘና ይህንንም አድረጉባቸው ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰባቸውም።
ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧችው አዘዘ ከይምንሑር ከተማም አውጥተው ራሶቻቸውን ቆረጡአቸው። ፃ ከሚባል አገር ሰዎች መጥተው የቅዱስ አባ አክራን ሥጋውን ወሰዱ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት በብዛት ተገለጡ። እንዲሁም የእነዚያን የሦስቱን ቅዳሳን የፊልጶስን፣ ለአብጥልማንና የዮሐንስን ሥጋቸውን ከይምንሑር ከተማ ሰዎች መጥተው ወሰዱ በመልካም ልብሶችም ገነዙአቸው ጥሩ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእነርሳቸውም ቁጥር የሌለው ድንቅ ተአምር ተገለጠ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፤ ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ
No comments:
Post a Comment