የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሁለት አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, June 10, 2023

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሁለት አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች

ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት ሁለት አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾማለች።
የኤጲስ ቆጶሳት በዓለ ሢመት በሊባኖን መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ ማር አግናጥዮስ ኤፍሬም ዳግማዊ እና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ ዕድ የተፈጸመ መሆኑ ተመላክቷል።
በኤጲስ ቆጶስነት የተሾሙት ሁለቱ አባቶች አባ እንድርያስ ባሂ እና አባ አውጂን አልካሳ የተባሉ አባቶች ሲሆኑ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ ባሂ በመንበረ ፓትርያርክ የወጣቶች እና ክርስቲያናዊ ትምህርት ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ አውጂን አልካሳ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የበላይ ኃላፊ ጳጳስ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።
አዳዲሶቹ ኤጲስ ቆጶሳት በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት በቃለ መሐላ እና በፊርማ ቤተ ክርስቲያኒቱን በሙሉ አቅማቸው ለማገልገል እና የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና ጠብቀው ለማስጠበቅ ቃል ገብተዋል።
No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages