ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የከምባታ ፣ ሀድያ፣ ስልጤ እና የደቡብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ዶ/ር ኢንጂነር መሰለ ኃይሌ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኘውን የመቄት ወረዳ ቤተ ክህነት የአስፋ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈለገ አእምሮ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቄት ወረዳ ቤተ ክህነት ስር የሚገኙትን ጉባኤ ቤቶችንና በግንባታ ላይ የሚገኘውን ባለ 9 ወለል (B+G+7) ሁለገብ ሕንፃ የጎበኙ ሲሆን ለጉባኤ መምህራን፣ ደቀ መዛሙርትና አስተዳደር ሠራተኞች ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል። አስፋ ገነተ ጽጌ ፈለገ አእምሮ አዳሪ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በአምስት ጉባኤ ቤቶች ከ80 በላይ ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ እያስተማረ እንደሚገኝ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዘግቧል።
ምንጭ፤ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
No comments:
Post a Comment