ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤
ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤
አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤
አማን ኪዳንኪ ኢየኃልቅ፡፡
ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ፦ ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግኹ>(መዝ ፹ወ፰፥፫)።
በ፮ቱ ኪዳናት በዘመነ ብሉይ ሰዎች ከመቅሠፍተ ሥጋ ይድኑ ነበር፤በ፯ተኛው ኪዳን በኪዳነ ምሕረት ግን ከመቅሠፍተ ሥጋ ወነፍስ መዳን ተችሏል። የመዳናችን ፍጹም ምክንያት የኾንሽ እናታችን ቅድስት ካዳነ ምሕረት ኾይ በዓሥራት ሀገርሽ ኢትዮጵያ ምድር በየገዳማቱና አድባራቱ፣በየቦታው በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ፣የሚፈስሰውን ደም በተሰጠሽ ቃል ኪዳን ታስታግሽልን ዘንድ እንማጸንሻለን። በኀዘን የቆሰለው ልባችንን በምሕረትሽ አለስልሽው።
እንኳን አደረሰን፤አደረሳችኹ!
የካቲት 16/2016 ዓ.ም።
በቃልኩዳኗ በምድሪቱ ላይ ሰላም ታውርድልን፤
ከልጇም ፊት ታስምረን ታስታርቀንም
No comments:
Post a Comment