የበገና ትርጉም እና በገናን እንዴት እንደርድር? - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, September 2, 2019

የበገና ትርጉም እና በገናን እንዴት እንደርድር?






የበገና አገልግሎት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፦
እንደሌሎች የሃገራችን ጥልቅ ብሔራዊ የታሪክ ሃብቶችና በታሪክም ከእስራኤል ቀጥሎ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛ ጥንታዊ የዜማ መሣሪያ ጥንታዊ ይዘቱን የጠበቀ የሀገር ሀብት እንደ መሆኑ መጠን ሁለት ዓይነት ትርጉም አለው፡፡
እነርሱም፡-
  • ሰዋስዋዊ ትርጉምና
  • ሥነ ቃላዊ ትርጉም…………..ይባላሉ፡
 
የበገና ሰዋስዋዊ ትርጉም
“በገና” የሚለው ስምና “በገነ” የሚለው ግሥ በተለያዩ መዝገበ ቃላትና የቋንቋ ሊቃውንት ተተርጉሞ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ፡- አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ”መጽሐፈ ሰዋስው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ” በሚል መጽሐፋቸው በሁለት መልኩ ማለት “ሲጠቅብና ሲላላ”ብለው በማመሳጠር እንዲህ ብለው ተርጉመውታል፡፡
በገና ፡- በዕብራይስጥ ናጌን ይባላል ካሉበኋላ ሲተረጉሙት ፡- ነዘረ፣ መታ፣ ደረደረ፣ማለት ነው፡፡ ሲጠብቅ ግን ፡- ነደደ፣ ተቆጣ… ያሰኛል ብሏል፡፡
በገና፡ – በቁሙ መዝሙር ማለት ነው ብለውም ፈትተውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልደክፍሌ፡ መጽሐፈ ስዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)
አባ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የትግርኛመዝገበ ቃላት በተባለ መጽሐፋቸው፡- በገናንበቁሙ በገና ብለው ተርጉመውታል፡፡ (አባዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር፣ ትግርኛ አማርኛመዝገበ ቃላት፣ 1948፣አሥመራ)
ከሳቴ ብርሃን ተሰማ “የአማርኛ መዝገበቃላት” በተሰኘ መጽሐፋቸው እንዲህ ዓይነትትርጉም ሰጥተውታል፡፡
በገና፡- በአሥር አዉታር ጅማት በገናን ሠራ፣ቃኘ፣ ደረደረ፣ ድምጽን እያጣራ፣ እያጣቀሰ፣እየነዘረ… በገናን በገነ… ካሉ በኋላ በገነኛ፡-የሚለው ደግሞ በገናንየሚመታ፣ በገናንየሚያውቅ ደርዳሪ… ማለት ነው ብለውተርጉመውታል፡፡ (ከሳቴ ብርሃን ተሰማ፣የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ 1951 ዓ.ም፣አርቲስቲክማተሚያ ቤት፣ አዲስ አበባ)
  1. የበገና ሥነ ቃላዊ ትርጉም፡-
በገነ፡- አደረቀ፣ አቃጠለ፣ አነደደ… ማለት ነው፡፡በገናም ከዚህ የሚወጣ ስም ነው፡፡ የዚህትርጉምማግኘት ዋና ምክንያትም ሁሉም ነገር (የበገናሁለገብ ሰውነት) በደረቅ ነገሮች ማለትምበደረቅእንጨትና በደረቅ ቆዳ እንዲሁም በደረቅ ጅማትየሚሠራ ወይም የሚዘጋጅ ስለሆነ በገና ተባለተብሎ ይተረጐማል፡፡
በገና፡- “በ” እና “ገና” በመነጣጠል የሚያስገኘውትርጉም በመጠቀም… በ … ገና…. በገና በዓልወይ በገና ወቅት የሚደረደር የምስጋና መሣርያስለሆነ በገና ተባለ ተብሎ ይተረጎማል፡፡
በገና፡- በገነ ማለት ደረደረ ማለት ነው፡፡ ስለሆነምበገና ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር… ማለትነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሠረት በማድረግይተረጎማል፡፡ ለምሳሌ፡-
“አቤቱ አምላኬ በበገናአመሰግናለሁ” መዝ.42/43፡4
“ለእግዚኣብሔር በገናደርድሩለት” መዝ.48፡5
“እግዚኣብሔርንበመሰንቆ አመስግኑትአሥር አውታር ባለውበበገና ዘምሩለት”መዝ.32/33፡2
የዚህ አጭር ጥናታዊ ጽሑፍ ኣቅራቢ ግንከሁለቱም ወገን በሚወሰዱ የትርጉም መመሳሰልበመነሳት በምስጢር ከበገና መንፈሳዊናማኅበራዊ አገልግሎትጋር የተሻለ ቀረቤታ ያለውንትርጉም ቢሆን ይመርጣል፡፡
በመሆኑም፡- በገነ፡- ደረደረ፣ መታ፣ አነዘረ…. ወዘተማለት ነው በሚለው መልካም ትርጉምይስማማል፡፡ ምክንያቱም ከነባራዊ የበገናማኅበራዊም ሆነ መንፈሳዊ እሴት ማለትምከድርጊቱ ወይም ከአቀራረቡ (ከአገልግሎቱ) ጋርአብሮ ይሄዳልና ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት፡-
በገና፡ -ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር…ወዘተ ማለት ነው፡፡ በገነኛው ቅዱስ ዳዊትበመዝሙሩ በገናን ሲተረጉም መዝሙር፣ምስጋና… በማለት ሲገልጽ እናገኘዋለንና፡፡
የበገና ታሪካዊ አጀማመር፡-
በገና፡- በትክክል መቼና እንዴትተጀመረ የሚለውጥያቄ መልሱ ከባድ ቢሆንም ሁላችንምእንደምናውቀው፣ ዓለምም ቢሆን በስፋት በግልጽበአደባባይ እያወደሰው እንዳለ የሁሉም ጥበባትማለትም ሥጋዊ ጥበብንም ጨምሮ መገኛቸውወይም ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡በመሆኑም በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜተገል ጾ የምናገኘው የምስጋና ወይም የዜማመሣሪያ በገና ብቻ ነው፡፡
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነታ የመረመርነው እንደሆነ፡-
በገና ለመጀመሪያ ጊዜ የደረደሩት የላሜህ ልጅየዩባል /ኢዮቤል/ ልጆች ነበሩ (ዘፍ.4፡19-24)፡፡ይኸውም ዓይነ ስውር (ማየት የተሳነው) የነበረላሜህ አያታቸው በበረሃ እየሄደ እያለ ቃኤልተቅበዝባዥ ነበርና ለብቻው በዱር ተሰውሮሲንኮሻኮሽ ሰምቶ መንገድ ይመራው ለነበረውረድእ “እጄ ይሞቅብኛል ቅጠሎች ሲንኮሻኮሹእሰማለሁ አራዊት መጥቶብናል መሰለኝ ስለዚህድንጋይ አቀብለኝ” ኣለውና ድንጋዩን ተቀብሎቢወረውር የቃየን ግንባሩን መትቶ ገደለው፡፡ቀርበው ሲመለከቱት የራሱ አባት ቃየን ሆኖሲያገኘው እጅግ መሪርየሆነ ለቅሶ አለቀሰ፡፡ ወደቤቱ ተመልሶም ዓዳና ሴላ ለሚባሉት ሚስቶቹ″ስምዓኒ ዓዳ ወሴላ አንስትያየ አነ ቀተልክዎለቃየን አቡየ፡- ዓዳና ሴላ ሚስቶቼ ሆይ ስሙኝ፤እኔ ዛሬ አባቴ ቃየንን ገድየዋለሁና….” በማለትነገራቸው፡፡ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ታሪካዊተዋረዱን ጠብቀው የታሪክ እውነታውንለልጆቻቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህም የላሜህ የልጅልጆች (የዩባል ልጆች) በቃየን ሞት ብቻሳይሆንበወላጆቻቸው የአሟሟት ሁኔታ እጅግ አዘኑ፡፡ይህም አቤል በቅንዓት ምክንያት በገዛ ወንድሙበቃኤል መገደሉ፤ ቃየንም “ተባርዮን የማያስቀርአምላክ ነውና” በገደለው ዓይነትየአገዳደል ዘይቤበድንጋይ በልጁ በላሜህ መሞቱ… እያወጡእያወረዱ እጅግ ከማዘናቸው የተነሳ በገናለመጀመርያ ጊዜ ከደረቁ ቁሳቁሶች አበጅተውበመሥራት በበገና እያንጎራጎሩ ሐዘናቸውንገልጸዋል፡፡
በዚህም በገና ከፍጥረተ ዓለምብዙም ባልራቀሁኔታ (ከአዳም አምስተኛ ልጆች በሆኑ አበው)የተገኘ የመጀመርያ የሐዘን፣ የእንጉርጉሮ፣ የንስሐ፣የልመናና የምስጋና መሣሪያ ነው እንላለን፡፡ተዋረዱም፤
አዳም፡- ቃኤልን ይወልዳል ቃኤል፡- ላሜህንይወልዳል ላሜህ፡- ዮባልን ይወልዳል ዮባል፡-በገና የሚደረድሩትን ይወልዳል (ስማቸውበመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አልተገለጸም)፡፡በመሆኑም የአራተኛ ትውልድ ልጆች ማለትምከአዳም አምስተኛ ትውልድ በሆኑት በእነዚህአበው ምክንያት በገናን ተዘጋጅቶ መደርደርተጀመረ፡፡
ቃለ በገና፡- ቃለ ማኅዘኒ
ድምፀ ማኅዘኒ … ነው፡፡ ምክንያቱም በተለይየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንሊቃውንት አራቅቀው እንደሚተረጉሙት ይህምድራዊ ማኅዘኒ ዜማ የመጣው በዮባል ልጆችኃዘንና እንጉርጉሮ ምክንያት እንደሆነ ይኸው ከላይየተጠቀሰው ታሪክ ጠቅሰው ያትታሉ፣ያመሰጥራሉ፡፡ ይኸውም ከላይ እንደተገለጸው፡-ቃየል ወንድሙ አቤልን መግደሉ፤ ቃየል ደግሞበልጁ በላሜህ መገደሉን፤ እያስታወሱ የዩባልልጆች የደረቀ እንጨት ጠርበውና አለዝበው፣ ቆዳወጥረው፣ ፍቀው፣ አድርቀውና ዳምጠው፣ ጅማትአክርረውና አበግነው… በቃለ ማኅዘኒ፣ በድምፀማኅዘኒ… ያንጐራጉሩ ነበር በማለትሊቃውንቶቻችን ያትታሉ፡፡ በዚህ ታሪካዊ እውነታምክንያት ነው “በገና” ቃለ ማኅዘኒ፣ ድምጸ ማኅዘኒሆኖ የሐዘን ማለትም የንስሐ፣ የልመናና የምስጋናማቅረቢያ የዜማ መሣሪያ በመሆን አገልግሎትበመስጠት ላይ የሚገኘው፡፡ የበገና የአጀማመሩታሪክ በዩባል ልጆች ቢሆንም ዘመናት አልፎከትውልድ ትውልድ ሲተካ ይዘቱም ሆነ ዓይነቱእየተሸሻለ መጥቶ የበገና አጠቃላይ ማኅበራዊሚናውም ሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ይበልጥጎልቶ የታወቀው ግን በመዝሙረኛው (በበገነኛው)በቅዱስ ዳዊት ምክንያት ነው፡፡
የበገና አገልግሎት፤
በገና የሚያገለግለው ለመንፈሳዊትሩፋትማለትም ለምስጋናና ለልመና ብቻ ነው፡፡በመሆኑም ተመርጦ ለቤተክርስቲያን አገልግሎትይውላል፡፡ ለምሳሌ፡-
“አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀለሁ”መዝ.42/43/4
“አሥር አውታርም ባለው በበገናዘምሩለት” መዝ.32/33/2
“ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት”መዝ.4.8/5/… ወዘተ ከተመዘገቡትመጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃዎች ጥቂቶቹናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱለማኅበራዊ እሴት፣ ለሃገር ክብር፣ ለሉዓላዊነት…በገና ይደረደራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማስረጃችን በአፄቴዎድሮስ ጊዜ የተደረደረውና እስከ አሁን ድረስየበገና መማርያ የሆነው የበገና አገልግሎት ነው፡፡ከዚህ ውጭ በገና ለዓለማዊ ፍላጐትማስፈጸሚያ ማለትም፡- ለዳንስና ለዳንኪራለዘፈንና ለጭፈራ ለዝናና ለጉራ ለቀልድና ለፉከራ… ወዘተ ፈጽሞ አገልግሎት አይሰጥም፡፡
የበገና ጥቅም፡-
ከላይ እንደተገለጸው በገና በዋናነት ለመለኮታዊየእግዚአብሔር ፈቃድ ማስፈጸሚያማለትምለምስጋናና ለልመና የሚያገለግል ሲሆንበተጨማሪም ለማኅበራዊ እሴት መግለጫየሚውል መንፈሳዊና ጥንታዊ የዜማ መሣሪያነው፡፡ ለምሳሌ፡- እግዚአብሔርን ለማመስገን እናእግዚአብሔርን ለመለመን። ስለ በገና በመጽሐፍቅዱስ የተጻፉ በአብዛኞቹ የሚገልጹት “በገናለምስጋናና ለልመና ሲቀርብ” ነው
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ማውጫ ያገኘኋቸውእነሆ፡ የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል
ኦሪት ዘፍጥረት
4፥21 “የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ እርሱምበገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ።”
31፥27 “ስለምን በስውር ሸሸህ? ከእኔም ከድተህስለምን ኮበለልህ? በደስታና በዘፈን በከበሮናበበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም?”
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
10፥5 “ከዚያም በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህወደዚያም ወደከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥ በገናናከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢትእየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱየነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል።”
16፥16 “በገና መልካም አድርጎ የሚመታ ሰውይሹ ዘንድ ጌታችን በፊቱ የሚቆሙትን ባሪያዎቹንይዘዝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ክፉ መንፈስበሆነብህ ጊዜ በእጁ ሲመታ አንተ ደኅና ትሆናለህአሉት።”
16፥17 “ሳኦልም ባሪያዎቹን፦ መልካም አድርጎበገና መምታት የሚችል ሰው ፈልጋችሁአምጡልኝ አላቸው።
16፥18 “ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ፦ እነሆ፥መልካም አድርጎ በገና የሚመታ የቤተልሔማዊውን የእሴይን ልጅ አይቻለሁእርሱምጽኑዕ ኃያል ነው፥ በነገርም ብልህ፥መልኩም ያማረ ነው፥ እግዚአብሔርም ከእርሱጋር ነውአለ።
16፥23 “እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉመንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞበእጁ ይመታ ነበር ሳኦልንም ደስ ያሰኘውያሳርፈውም ነበር፥ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅነበር።”
18፥10 “በነጋውም ሳኦልን ክፉ መንፈስከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፥ በቤቱም ውስጥትንቢት ተናገረ።ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረበእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁይዞ ነበር።
19፥9 “ሳኦልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦሳለ ክፉመንፈስ ከእግዚአብሔርዘንድ ያዘው። ዳዊትምበእጁ በገና ይመታ ነበር።
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
6፥5 “ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ በቅኔናበበገና በመሰንቆም በከበሮም በነጋሪትና በጸናጽልበእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱነበር።
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
10፥12 “ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨትለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት መከታ፥ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ እስከ ዛሬምድረስ እንደዚያ ያለ የሰንደል እንጨት ከቶአልመጣምአልታየምም።”
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
3፥15 “አሁንም ባለ በገና አምጡልኝ አለ። ባለበገናውም በደረደረ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅመጣችበት”
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
13፥8 “ዳዊትና እስራኤል ሁሉ በቅኔና በበገናበመሰንቆና በከበሮ በጸናጽልና በመለከትበእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱነበር።
15፥16 “ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገናበጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውንይሾሙ ዘንድ ለሌዋውያን ኣለቆችተናገረ።
15፥21 “መቲትያ፥ ኤልፍሌሁ፥ ሚቅኒያ፥ዖቤድኤዶም፥ ይዒኤል፥ ዓዛዝያ ስምንት አውታርባለው በገና ይዘምሩ ነበር።
15፥28 “እንዲሁ እስራኤል ሁሉ ሆ እያሉ ቀንደመለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆምበገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳንታቦት አመጡ።
16፥5 “አለቃው አሳፍ ነበረ ከእርሱም በኋላዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድኤዶም፥ይዒኤል በመሰንቆና በበገና አሳፍም በጸናጽልይዘምሩ ነበር።
25፥1 “ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍናከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገናበጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎችለማገልገል ለዩ በአገልግሎታቸውም ሥራ የሠሩሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ
5፥12 “መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውምወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልናበገና መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብበመሥራቅ በኩል ቆመው ነበር ከእነርሱም ጋርመቶ ሀያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር። ካህናቱምከመቅደሱ በወጡ ጊዜ፥
9፥11 “ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨትለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት ደርብ፥ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ እንደዚህምያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር።
20፥28 “በበገናም በመሰንቆም በመለከትም ወደኢየሩሳሌም ወደእግዚአብሔርም ቤት ገቡ።
29፥25 “ይህንም ትእዛዝ እግዚአብሔር በነቢያቱእጅ አዝዞአልና እንደዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይእንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ጸናጽልናበገና መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንንበእግዚአብሔር ቤት አቆመ።
መጽሐፈ ነህምያ
12፥27 “የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርምበጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑንበየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።
መዝሙረ ዳዊት
33፥2 “እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት።
43፥4 “ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ጕልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬእገባለሁ አቤቱ አምላኬ፥ በበገና አመሰግንሃለሁ።
49፥4 “ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፥ በበገናምምሥጢሬን እገልጣለሁ።
54፥0 “ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ዜፋውያን መጥተው ለሳኦል፦ እነሆ ዳዊት በእኛ ዘንድ ተሸሽጓል ብለው በነገሩት ጊዜ የዳዊት ትምህርት።
55፥0 “ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት ትምህርት።
57፥8 “ክብሬ ይነሣ፥ በገናና መሰንቆም ይነሡ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
61 “ለመዘምራን አለቃ በዎች የዳዊት መዝሙር።
67 “ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር።
71፥22 “እኔም በበገና ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ የእስራኤል ቅዱስ አምላክ ሆይ፥ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።
76 “ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ አሦራውያን የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
81፥2 “ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር
92፥3 “አሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።
108፥2 “በገና ሆይ፥ ተነሥ፥ መሰንቆም እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
144፥9 “አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ አሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።
150፥3 “በመለከት ድምፅ አመስግኑት በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።
ትንቢተ ኢሳይያስ
5፥12 “መሰንቆና በገና ከበሮና እምቢልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፥ እጁም ያደረገችውን አላስተዋሉም።
14፥10 “እነዚህ ሁሉ። አንተ ደግሞ እንደእኛ ደክመሃልን? እኛንስ መስለሃልን? ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ
ሰቆቃው ኤርምያስ
5፥14 “ሽማግሌዎች ከአደባባይ፥ ጕልማሶች ከበገናቸው ተሻሩ።
ትንቢተ ሕዝቅኤል
33፥32 “እነሆ፥ አንተ መልካም ድምፅ እንዳለው እንደሚወደድ መዝሙር ማለፊያም አድርጎ በገና እንደሚጫወት ሰው ሆነህላቸዋል ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም።
ትንቢተ ዳንኤል
3፥5 “የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁጊዜ፥ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል።
3፥7 “ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉየመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመሰንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፥ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ።
3፥10 “አንተ፥ ንጉሥ ሆይ። የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ
3፥15 “አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ ከእጄስየሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው።
የዮሐንስ ራእይ
5፥8 “መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።
14፥2 “እንደ ብዙ ውኃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ፥ ደርዳሪዎችም በገና እንደሚደረድሩ ያለ ድምፅ ሰማሁ።
15፥2 “በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፥ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።
18፥22 “በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህበአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥከቶ አይሰማም፥
ትንቢት ለመናገር
ቅዱስ ዳዊት የተናገራቸው ቃለ ትንቢቶች በሙሉ መመልከት ወይም ማንበብ በቂ ነው፡፡
“ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል” 1ኛ መ. መሳ. 10፡5
ከመናፍስት ሥቃይ ለመዳን
“እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፡፡ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር” (1ኛሳሙ.16፡23) እንዲል፡፡
የሀገር ሉዓላዊነት ለመግለጽ … ወዘተ ይጠቅማል፡፡
“ፈረሱ አባ ታጠቅ ስሙ ቴዎድሮስ….. እኔ መዩ ቱርክን ባይ የምሸሽ ነኝ ወይ….” እንደ ምሳሌ ልንወስደው እንችላለን፡፡
በገና ወደ ሀገራችን እንዴት መጣ?
የበገና ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የአመጣጥ ታሪክ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡
  1. የሀገራችን ኢትዮጵያ የሥልጣኔዋ ውጤትና በሕገ ልቡና የማመንዋ ውጤት ነው፡፡ /የተጀመረ እዚሁ ሀገራችን ነው የሚል አስተምህሮ ነው፡፡/
  2. በቀዳማዊ ምኒሊክ ጊዜ ከታቦተጽዮን ጋራ አብረው ከመጡት የዜማና የሥርዓተ አምልኮ ንዋያተ ቅድሳት፣ መጻሕፍት… ወዘተ አንድ ሆኖ የመጣ ነው የሚሉ ሲሆን ይህንኑ አመለካከትም ይበልጥ በሀገራችንጠበብት ሊቃውንት በስፋት ይተረጉማል፣ ይተረካል… ይታመናልም፡፡
የበገና አሠራር፡-
በገና የሚሠራው፡-
ከደረቀ እንጨት /ተጠርቦና ለዝቦ እንዲሁም በልዩ ጥበብ ተውቦ/
ከደረቀ ቆዳ፡- /ተፍቆና ተዳምጦ እንዲሁም ዙሪያውን ተሰፍቶ/
ከደረቀ ጅማት፡- /በግኖና ከርሮ ከላይ እስከ ታች ተወጥሮ፣በቁጥር ተቀምሮ ይሠራል፡፡/
የበገና አቀራረብ ዘዴዎች፡-
በገና በሁለት መልኩ ሊቀርብ ወይሊደረደር ይችላል፡፡
  1. በእጅና፡-
  2. በድሕንጻ፡- (ድሕንጻ፡- መግረፊያ ሆኖ እጅግ መሳጭና የበለጠ በሚመስጥ መልኩ በገናውን የሚያስጮኽ ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ወይም የበገና ማጫወቻ ነው) “በድሕንጻ መንፈስ ዝብጢ አውታረመሰንቆሁ ለልብየ ወአስተንፍሲ ውስተ አፉየ ከመ እኩን እንዚራሁለበኩርኪ……) እንዲል (መጽሐፈ ሰዓታት፡ እሴብሕ ጸጋኪ ይመልከቱ)
ከበገና ምሳሌያዊ ትምህርቶች፡-
ላይኛው፡- የፈቃደ እግዚአብሔር
ታችኛው፡- የማኅፀነ ድንግል
ግራና ቀኙ፡- የሚካኤልና የገብርኤል
አሥሩ አውታር፡- የዓሠርቱ ቃላት
አውታሩ በእጅ ሲመታ ሁለቱም ማለትም አውታሩንና እጁን ተዋሕደው ድምፁ የሚሰማው ከታችኛው (ከቆዳው) ዘንድ እንደ ሆነ ሁሉ መለኮትና ሥጋ ተዋሕደውከማኅፀነ ድንግል ዘንድ ለማደራቸው ምሳሌ ነው፡፡
አንድም፡-
ላይኛውና ታችኛው፡- የሰማይና የምድር
ግራና ቀኙ፡- የብሉይና የሐዲስ
አሥሩ አውታር፡- የዓሠርቱ ትእዛዛት
በብሉይ ኪዳን ፈጣሪና ፍጡርንየሚያገናኙ ዓሠርቱ ትእዛዛት ስለነበሩ በዚሁ ተመስሏል፡፡
የበገና ቅኝቶ፡-
በገና ሦስት ዓይነት ቅኝት አለው፡፡ እነርሱም፡-
  1. በበገና ቅኝት ሰላምታ በተለምዶ አምባሰል እንደሚባለውነው፤
  2. በበገና ቅኝት እርግብና ዋኔንበተለምዶ ትዝታ እንደሚባለው ነው፤
  3. በበገና ቅኝት ስለቸርነትህ በተለምዶ አንቺ ሆዬ ለኔ እንደሚባለው ነው፤
በተለምዶ ያልኩበት ምክንያት በሌሎች የዜማ መሣርያ (በዘፈን መሣርያዎች) የሚሰጣቸው ስም ሲሆን በገና ደግሞ የራሱ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያበረክትበት የራሱ መዝሙርናየቅኝት ስልት ያለው እድሜ ጠገብቅርስ በመሆኑ “በተለምዶና በበገና” ተብለው ቀርበዋል፡፡ ከሁለቱም በአንዱ ግልጽ እንዲሆን ታስቦ ብቻ ነው፡፡ በመጨረሻ ስለ በገና ለወደፊት ሰፊ ነገር የምለው ነገር ቢኖረኝም ግን ለጊዜው ለማጠቃለል ያህል፡-
በበገና፡-
እግዚአብሔር፡- ይመሰገንበታል፣ ይቀደስበታል፣ ይለመንበታል… ፡፡
ቅዱሳን፡- ይከበሩበታል፣ ይታሰቡበታል… ፡፡
ሕሙማን፡- ይፍወሱበታል፡፡
ሕዙናን፡- ይጽናኑበታል፡፡
አማኞች፡- ይመከሩበታል፡፡
የሀገረ ክብር፡- ይገለጽበታል፣ ይነገርበታል… እያልኩ ለወደፊትበገና እንዴት እንደሚደረደር ለማሳየትና የድምጹን ሁኔታ ለማስተማር በድምጽ፣ እንዲሁም በድምጽ ወምስል ለማዘጋጀት ሐሳብ አለ፤ ሁሉን የሚፈጽም ግንእግዚአብሔር ስለሆነ የዚህ ታሪካዊና ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጣዕም ለሥርዓተ አምልኮ፣ ለልመናና ለምስጋና ተጠቅመንበትሕይወታችን በንስሐ መርተን ፍጻሜአችን ያማረ የተስተካከለ እንዲሆንልን አምላከ ዳዊት እግዚአብሔር ይርዳን፤ የወላዲተአምላክ ድንግል ማርያም ጣዕም በአንደበታችን ፍቅርዋንም በልቡናችን ይሣልልን፡፡ አሜን
በመቀጠል 
  • በገና የልምምድ 
  • የበገና ዝማሬ በህብረት
  • የበገና ዝማሬ በተናጠል
  • የበገና አሰራር (አቀራረጽ)
  • የበገና ማሰርና መፍታት እንዴት እንደሆነ በቪዲዮ እንመለከታለን
  • ሌሎች ዘማርያን በገና መዝሙር እንመለከታለን
  • የበገና ዝማሬ ዜማውን እንለያለን ለምሳሌ ሰላምታ፤ ትዝታ፤ አንቺሆየ፤ አምባሰል፤ ባቲ የቱ እንደሆነ በመዝሙሩ አድምጠን መለየት አንችላለን ስለዚህ ተከታተሉን።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages