እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክፍል አንድ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ከመሞቷ በፊት በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መቃብሩ ቦታ ትጸልይ ነበር። መንፈስ ቅዱስም ለእመቤታችን ከዚህ ዓለም እንደምትለይ ነገራት። ጌታችንም በደብረ ዘይት ላሉ ደናግላን ነግሯቸዋልና ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፍጥነት መጡ። እርሷን መንፈስ ቅዱስ የነገራትን ነገረቻቸው።
እነሱም እንደመጡ ባየች ጊዜ እንዲህ ብላ ጸለየች። ልጄ ውዳጄ፤ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ልመናየን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም በሕይወት ያሉትንና በሕይወት የተለዩንን ቅዱሳን በሙሉ ወደ እኔም አምጣቸው። አንተ የሕያዋን አምላክ ነህና፤ለአንተም ምስጋና ይሁን አሜን አለች። በዚያን ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ትዕዛዝ ቅዱስ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አደረሰችው። ቅዱስ ዮሐንስም እንደደረሰ ሰገደላትና በፊቷ ቆሞ እንዲህ አላት፤ ሰላምታ ይገባሻል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልደሽልናልና፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። አንቺ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተሽ በክብር በምስጋና ወደ ዘለዓለም ሕይወት ትሄጃለሽና። እመቤታችንም ይህን በሰማች ጊዜ እጅግ ደስ አላት እንዲህ ብላ አምላኳንም አመሰገነችው። ጌታዬ አምላኬ ፈጣሪዬ ሆይ፤ ላንተ ክብር ምስጋና ይገባል። የለመንኩህን ሰጥተኸኛልና። አሁንም ነብሴን ተቀብለው ወደ ሰማይ ወደ አንተ ሊይሳርጓት ከሚመጡ መላእክቶችህ ጋር በመምጣትህ የምለምንህን ሁሉ ስጠኝ። በዚህን ጊዜ ከሰማይ እንዲህ የሚል ድምጽ መጣ፤ እነሆ አሁን መላእክት ይደርሳሉ። ቅዱሳን ሐዋርያትም ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ይደርሳሉ። ቅዱሳን ሐዋርያት ከዚህ ዓለም የተለዩትም፤ በሕይወት ያሉትም ሁሉ በአንድነት መጥተው ለእመቤታችን ሰገዱላት። እነርሱም አመሰገኗት እንዲህም አሏት። ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይብልሽ ፈጣሪያችን ከዚህ ዓለም ለይቶ ቃል ኪዳን እንደሰጠሽ በክብር በምስጋና ከእርሱ ጋር ያሳርግሻልና አሏት። በዚህን ጊዜ እመቤታችን በአልጋዋ ላይ ተቀመጠች። ቅዱሳን ሐዋርያትንም እንዲህ አለቻቸው። ፈጣሪዬ ፈጣሪያችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እኔ እንደሚመጣ እናንተንም እንዳየኋችሁ እንደማየው አሁን አወኩ። ከዚህ ከሥጋዬ ወጥቼ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እሔዳለሁ። ነገር ግን እናንተ እኔ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ማን ነገራችሁ? አወቃችሁ? ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱሳን ሐዋርያት በሙሉ ወደ አንቺ እንመጣ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፤ መጣን አሏት። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ይን ነገር ከቅዱሳን ሐዋርያት በሰማች ጊዜ ድምጿን ከፍ አድርጋ አምላኳን አመሰገነች። እንዲህም አለች ከ እንግዲህ ወዲያ ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሰግኑኛል። ይህን ብላ እንደጨረሰች እጣን አምጥታችሁ በማጠን የፈጣሪዬን ስም ጥሩት አለቻቸው። እነሱም እንደታዘዙት አደረጉ። በዚህን ጊዜ ጌታችን ተገልጾ ብዙ ድንቅ ተአምራትን አደረገ። በሽተኞች ወደ እመቤታችን ወደ አለችበት ቤት በቀረቡ ጊዜ ከደዌአቸው ይፈወሱ ነበር። እመቤታችን ከሥጋዋ የምትለይበት ሰዓት ሲደርስ ቅዱሳን ሐዋርያትንና ደናግልን ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኗት። እመቤታችንም እጇን ዘርግታ ባረከቻቸው። በዚህን ጊዜ ፈጣሪያችን ነፍሷን ከሥጋዋ ለይቶ በመለኮታዊ እጆቹ ይዞ በብርሃን ልብስ አጎናጽፎ ወደ ከፍተኛ መኖሪያ ከ እርሱ ጋር አሳረጋት። ሥጋዋን ግን እንደሚገባ ገንዘው፤ ወደ ጌቴ ሰማኒ ተሸክመው እንዲወስዷ ሐዋርያትን አዘዛቸው። ነፍሷ ከሥጋዋ ከመውጣቷ በፊት በሰው አንደበት ይህ ነው ተብሎ የማይነገር ብርሃን እያየች ነበር። እመቤታችንም ፈጣሪዋን ልጇን ወዳጇን እንዲህ ብላ ጠየቀችው። ልመናየን ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ። በስሜ ወደ አንተ የሚለምነውን ሁሉ፤ ልመናውን ተቀበለው በመከራም ውስጥ ሁኖ ስሜን ጠርቶ ወደ አንተ የሚለምነውን ከመከራም ሁሉ አድነው፤ በሰማይም በምድርም በሥራው ላይ ሁሉ አንተ ከሃሊ ነህና መታሰቢያየን በውስጧ የሚያደርጉባትን የሁሉንም መስዋእታቸውን ተቀበል። ፈጣሪም እንዲህ ብሎ መለሰላት። የለመንሽኝን ሁሉ አደርግልሻለሁ። እመቤታችንም ከአረፈች በኋላ ጌታችን እንዳዘዘ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሊወስዷት ሐዋርይት ገንዘው ተሸከሟት። አይሁድም በሰሙ ጊዜ ሥጋዋን ሊይቃጥሉ መጡ። ከ እነርሱም አንዱ ከምድር ይጥላት ዘንድ ይእመቤታችንን አልጋዋን ያዘ። ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እጆቹን በእሳት ሰይፍ ቀጣውና እጆቹ በአልጋው ላይ ጠንጠለጠሉ። ያን ጊዜ በጌታችን አምኖ ወደ እመቤታችን እያለቀሰ እንዲህ እያለ ለመነ። የ እውነተኛ አምላክ ይጌታ ኢይሱስ ክርስቶስ እናት አንቺ በ እውነት ድንግል ይሆንሽ በ እኔ ላይ ይቅርታ ታደርጊ ዘንድ አለምንሻለሁ። በሐዋርይትም ልመና እጆቹ ተመልሰው እንደቀድሞው ደህና ሆኑ። እመቤታችን በቀብሯት ጊዜ ከዚያ ሶስት ቀን ኖሩ እረፍቷም የነበረው እሁድ ቀን ጥር 21 ነብር። ጌታችንም ብርሃናውይን መላእክትን ልኮ ሥጋዋን ከመቃብር ወስደው በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር አኖሯት። ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ግን ያን ጊዜ አልነበረም በደመና ላይ ተጭኖ እርሱ ሲመጣ መላእክት ሲያሳርጓት እመቤታችንን አገኟት ። መላእክትም ለአምላክ እናት ለ እመቤታችን ድንግል ማርይም ና እጅ ንሳ አሉት እርሱም ሰገደላትና ተሳለማት ከ እርሷም ተባረከ ከዚህም በኋላ ወደ ሐዋርያት ደረሰ። እነርሱም እመቤታችንን ማርያምን እንደ አረፈችና እንደ ቀበሯትም ነገሩት። ቅዱስ ቶማስም ሥጋዋን እስከ ማይ አላምንም አላቸው። ሥጋውንም ይሳዩት ዘንድ ወደ መቃብሯት በአደረሱት ጊዜ ከመቃብሩ ውስጥ ሥጋዋን አላገኙም ደንግጠውም አደነቁ ያን ጊዜ ከመላእክት ጋር ወደ ሰማይ ስታርግ እመቤታችን እንዳገኛት ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ የ እመቤታችንን ዕርገቷን ኡ ስላላዩ እጅግ አዘኑ ሥጋዋን በምድር ውስጥ ይተው ዘንድ እንዳልወደደ መንፈስ ቅዱስ አስገነዘባቸው። ከዚህም በኋላ አንድ ጊዜ ደግሞ እርሷን ያሳያቸው ዘንድ እንዳለው ጌታችን ቃል ኪዳን በማድረግ ተስፋ ሰጣቸው። እነርሱም በተስፋ እስከ ነሐሴ 16 ቀን በተስፋ ኖሩ። የ እመቤታችንም የእድሜዋ ዘመን 64 ዓመት ነው። በአባትና በእናቷ ቤት 3 ዓመት፤ በመቅደስም 12 ዓመት፤ በዮሴፍም ቤት 34 ዓመት ከሦስት ወር ከጌታ ዕርገት በኋላ በወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ቤት 14 ዓመት ነው።
ይቆየን…………….
የሕይወት የድህነት አለኝታ የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
የእመቤታችን በረከቷ ረድ ኤቷ ይደርብን አሜን!!!
Post Top Ad
Wednesday, April 15, 2020
Tags
# ነገረ ማርያም
Share This
About አትሮንስ ሚዲያ
ነገረ ማርያም
Labels:
ነገረ ማርያም
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Post Bottom Ad
Author Details
Templatesyard is a blogger resources site is a provider of high quality blogger template with premium looking layout and robust design. The main mission of templatesyard is to provide the best quality blogger templates which are professionally designed and perfectlly seo optimized to deliver best result for your blog.
No comments:
Post a Comment