የማቴዎስ ወንጌል መግቢያ ክፍል ሁለት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, April 25, 2020

የማቴዎስ ወንጌል መግቢያ ክፍል ሁለት



ቅዱስ ማቴዎስ ማነው ክፍል ሁለት
  የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል የተጻፈበት ዓላማ የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌልን ስናጠና ቅዱስ ማቴዎስ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክና ሥራ በወንጌሉ ውስጥ ለዕብራውያን የጻፈው በሚከተሉት ዓላማዎች መሆኑን እንረዳለን።

· ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዳዊት ትውልድ የተወለደ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማስረዳት ነው።
 ይህንንም ሃሳብ ትውልዱን በመቁጠር ጌታ ራሱን “የሰው ልጅ” መጥራቱንና በሌሎች ሰዎች “የዳዊት ልጅ” ተብሎ መጠራቱን በመመዝገብ ያስረዳል። ማቴ 1፤1-17 8፤20 9፤6 9፤27 12፤27 16፤13 17፤12 18፤11 25፤31 26፤64

 · በሰዎች ዘንድ ጌታ ከነቢያት አንዱ ቢባል እንኳ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዲታወቅ ለማስረዳት ነው። ማቴ 3፤17 8፤29 11፤25-27 14፤33 16፤13-17 17፤5 27፤40 43፤54

 · በሕግና በነቢያት መጽሐፍት በብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስ የተነገሩትን ትንቢታዊ ቃላት እየጠቀሰ ፍጻሜአቸውን ለማሳየት ነው። ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ውስጥ ከ60 ጊዜ በላይ የብሉይ ኪዳን ጥቅሶችን ጠቅሷል።

 ከእነዚህም ብዙዎቹ ሕግና ነቢያት ስለ ክርስቶስ መሲህ ምን እንደተናገሩ የሚገልጹ ናቸው።

 የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በመጀመሪያ የተዘረዘረው የብሉይ ኪዳንን ፍጻሜ አሳይቶ ወደ ሐዲስ ኪዳን የሚያሸጋግር ድልድይ የሆነ ወንጌል በመሆኑ ነው።

 ስለዚህ የማቴዎስ ወንጌል ሕግና ነቢያትን በመጥቀስ ኢየሱስ እርሱ እንደሚመጣ ይጠበቅ የነበረውን መሲህ ክርስቶስ መሆኑን ለዕብራውያን ያስረዳል። ማቴ 1፤22 2፤4 4፤16 11፤2-5 12፤17-21 13፤35 16፤16 21፤522፤41-46 27፤9

 የወንጌሉ ጥናት
 · የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል 28 ም ዕራፎች እና 1061 ቁጥሮች ያሉት መጽሐፍት ነው።
 · ከዚህ ክፍል ውስጥ የ እነዚህን ም ዕራፎች ቁጥሮች ቃል በማንበብ የወንጌሉን ይዞታና አከፋፈል እናጠናለን።

 ይዞታው
 · አራቱም ወንጌላት ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ነገሮችን ይዘዋል እነርሱም
 1. የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርቶስን ታሪክ
2. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረጋቸው ተአምራት
 3. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸው ትምህርቶች ናቸው።
 28ቱን የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ም ዕራፋት በማንበብ እነዚህን ሦስት ይዞታዎች እንደሚከተለው እናጠናለን።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages