ማቴዎስ ወንጌል 1፤1-19 - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, April 25, 2020

ማቴዎስ ወንጌል 1፤1-19



መጽሐፈ ልደቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ 

v ወንጌላውያን ሲጽፉ ራሳቸውን መሰረት አያደርጉም፤ ሌሎች ግን ራሳቸውን መሰረት ያደርጋሉ
v ምንም የሚገልጽላቸው መንፈስ ቅዱስ ቢሆን የሚጽፉ ከራሳቸው አቅንተው ነውና
v ዳግመኛ ከአንድ ሃገር ሆነው ጽፈው ወደ አንዱ ሃገር ይሰዱታልና ወንጌላውያን ግን የሚጽፉ ጌታ የተናገረውን ነው እንጂ ከራሳቸው አቅንተው አይደለምና፤ በመካከል ሆነው ይጽፋሉና፤ ዳግመኛ ምንም አንዱም አንዱ ወሀሎ አሀዱ ብእሲ ቢል ነገር ለማያያዝ ነው።

 የጌታችን የኢየሱስ የትውልዱ ሐረግ እንዲህ ነው
 v ጸሐፊዮ ለብእሲ ከመ ዘሞተ ወበ ውእቱ መዋዕል ወጽአ ትዕዛዝ እም ኀበ አውግስጦስ ቄሳር ከመ ይጸሐፍ ኩሎ ዓለም እንዲል። አንድም፤
 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ ወግ ታሪክ እንዲህ ነው ስማ ለዳቤር ትካት ሀገረ መጽሐፍ እንዲል የወግ፤ የታሪክ ሃገር ሲል ወግ===› የነ ትእማርን የነራኬብን የነ ሩትን ያመጣል።
  ታሪክ ወለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመዝ ውእቱ ልደቱ ብሎ ያመጣል ልደቱ ለእግዚእነ አለ ብዙ ልደታት አሉና ከዚያ ሲለይ፤ 1) ልደተ አዳም ==== እምድር
2) ልደተ ሔዋን===== እምገቦ
 3) ልደተ አቤል =====እምከርስ
 4) ልደተ በግዕ===== እም ዕፅ
 5) ልደተ ሙታን===== እመቃብር አለ እኒያ አውጭ ይሻሉ፤ እሱ ግን በገዛ ስልጣኑ ነውና፤ የልደቱን ነገር ብቻ ይናገራልና

መጽሐፈ ልደቱ አለ፤ ምን ነው ቢሉ?
 } መጽሐፍ በአንድ መጀመር ኋላ ብዙ ማምጣት ልማድ ነው። ከዚያ ሁሉ ኦሪት ዘልደት ይላል። የሥነ ፍጥረትን ብቻ ተናግሮ ይቀራልን መጽሐፈ ልደቱ ባለው በቁጥር አንድ ይላል የንዑስ ምዕራፍ አሀዝ ነው።
 1) ማቴዎስ====መጽሐፈ ልደቱ
 2) ማርቆስ====አንተ ውእቱ ወልድየ
3) ሉቃስ==== ወይመስሎ ወልደ ዮሴፍ
 4) ዮሐንስ==== ቀዳማዊ ቃል ያለውን ሁሉም የጌትነት ነገር ከሆነ ብሎ አራቱ የተባበሩት ሲል አሐዱ ይላል።
 ሠለስቱ ቢል ማርቆስ አውጥቶ በሦስተኛው ሠንጠረዥ ማርቆስ የለምና
 } ወያዕቆብኒ ወለደ ዮሴፍሃ ፈሃሪሃ ለማርያም እንተ እምኔሃ ተወልደ እግዚእ ኢየሱስ ዘተብህለ ክርስቶስ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስ ከሷ የተወለደ የእምቤታችን እጮኛ የሚሆን አቃቤሃ ተለአኪሃ፤ አገልጋይዋ ጠባቂዋ የሚሆን ዮሴፍ ወለደ።

መገናኛው አንዱ አልአዛር ነው
 v አልአዛር ማትያንንና ቅስራን ይወልዳል
 v ማትያን ያዕቆብን፤ ያዕቆብ ዮሴፍን ይወልዳል
 v ቅስራ ኢያቄምን፤
 ኢያቄምም እመቤታችንን ይወልዳል
በሃገራቸው ሴትና ወንድን አቀላቅሎ መቁጠር የለምና ሥርዓት አፈረሰ ይሉኛል ብሎ በዮሴፍ አንጻር ቆጠረ፤
 እሷንም እንዳትቀር በቅጽል አመጣት።
} እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንድትታጭ ማድረጉ ስለ ምንድን ነው ቢሉ
1) ሃይል አርያማዊት ባሏት ነበርና
2) ወንድ ከወንድ ተገኘ ባሉ ነበርና ከመ በብሂሎቱ ብእሲ ያግህድ ከመ እግዝእትነ ማርያም በአማ ብእሲት ይእቲ እንዲል። አንድም፤
ጽንስን ከአጋንንት ለማሣት አውቀው ቢሆን ብዙ ጽንስ አበላሽተው ነበርና
 አንድም፤
 መስተመይናን ዝሁላነ እ እምሮ አይሁድ ሰብሳብ ርኩስ ይላሉና፤ ንጹሕ እንደሆነ ለማጠየቅ አንድም፤ በመከራዋ ጊዜ ለከተላት፤ ከርስት ገብቶ ሊቆጠርላት፤ ከውግረት ሊያድናት ዮሴፍ ምክንያት ባይሆራት በድንጊያ ወግረው በገደሏት ነበርና፤ በጽእለትም ሊያድናት
} ዘተብህለ ክርስቶስ አለ ይህም
v ስም ብቻ
 v የትስብዕት ብቻ
 v የመለኮት ብቻ አይደለም
 ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢሆን የወጣለት ስም ነው እንጂ ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14 ትውልድ፤ ከዳዊት እስከ ባቢሎን 14 ትውልድ፤ ከባቢሎን እስከ ክርስቶስ 14 ትውልድ፤ ከአብርሃም እስከ ክርስቶስ 42 ትውልድ ነው።

} ወለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመዝ ውእቱ ልደቱ፤ የእነ ትዕማርን፤ የእነ ራኬብን፤ የነሩትን ሲናገር መጥቶ ነበርና፤ የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደቱ እንዲህ ነው። ከጥንት ሲነገር ሲያያዝ መጥቶ ነበር እንጂ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ አይደለም። ወሶበ ተፍህረት ማንሻ። አንድም ወለእግዚእነሰ ይላል፤ በዘር በሩካቤ የሚወለዱ የአበውን ልደት ሲናገር መጥቶ ነበርና፤
 የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ግን ልደቱ እንዲህ ነው አለ፤ እንበለ ዘር ነው ከመዝ ያለውን ያመጣዋል።
} ወሶበ ተፍኅረት እሙ ማርያም ለዮሴፍ፤ እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ፤ እንበለ ይትቃረቡ ተረክበት ጽንሰተ እንዘ ባ ውስተ ማኅጸና እመንፈስ ቅዱስ፤ እንበለ ይትቃረቡ እንበለ ይትራከቡ ይላል፤

እሱ ሴት እንደሆነች ሳያውቃት፤ እሷ ወንድ እንደሆነ ሳታውቀው ዮሴፍ ጠባቂ ሳላት አጋዥ ሳትሻ፤ አንድም ድንጋሌ ስጋ ድንጋሌ ነፍስ ሳላት፤
 አንድም
 ወዘሃባ ሳላት ከባህርይዋ በግብረ መንፈስ ቅድሱ ጸንሳ ተገኘች።
 } ልደቱን በዘር ያላደረገው እንበለ ዘር ያደረገው ስለ ምን ነው ቢሉ
 ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለጽ። ከአምስት ሽህ አምስት መቶ ዓመት በኋላ ያለ አባት ከ እመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ መወለዱን ያስረዳናል።
} ወዮሴፍሰ ፈሃሪሃ እስመ ጻድቅ ውእቱ ኢፈቀደ ይክስታ፤ እጮኛዋ የሚሆን አቃቢሃ ተለአኪሃ አገልጋይዋ ጠባቂዋ የሚሆን ዮሴፍ ደግ ነውና ሊገልጣት ሊገልጥባት አልወደደም።
አላ መከረ ጽሚተ ይኅድጋ፤ በድብቅ ሊተዋት ወደደ እንጂ።
} ወእንዘ ዘንተ ይኄሊ ናሁ አስተርአዮ መልአከ እግዚአብሔር ለዮሴፍ በሕልም
እመቤታችን የብፅዓት ልጅ ናት።
 ሦስት ዓመት ሲሆናት አባት እናቷ ወስደው ለካህናት ሰጡ። ካህናትም ተቀብለው አክብረው ከቤተ መቅደስ ያኖሯታል። አስራ ሁለት ዓመት ትኖራለች። ከዚያ ሦስት ከዚህ አስራ ሁለት፤ አስራ አምስት አመት ይሆናል። አይሁድ ለምቀኝነት አይርፉምና ይህች ብላቴና መጠነ አንስት አደረሰች ቤተ መቅደሳችንን ታሳድፍብናለች ትውጣልን አሉት። ዘካርያስ ሄዶ እንደምን ትሆኝ አላት። ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ አለችው። ቢያመለክት ከነገደ ይሁዳ ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን በትር ሰብስበህ ከቤተ መቅደስ አግብተህ አውጣው ምልክት አሳይሃለሁ አለው። ቢሰበስብ 1985 ተገኙ። ያን ቢያወጣው ከዮሴፍ በትር ኦ ዮሴፍ እቀባ ለማርያም የሚል ተገኘ። ዕጣም ቢያወጡ ለእሱ ወጣ። ርግብም መጥታ በራሱ ላይ አረፈች። እንደ ሦስት ምስክር ያም ሆነ ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ አግኝተን የሰጠኝህን እስክናሰናብትህ ወስደህ ጠብቅ አትንካ ብለው ሰጡት ይዟት ሄደ። ጊዜው አፀባ ነበርና ንግድ ሄዶ ሦስት ወር ቆይቶ ቢመለስ ዮሐንስ የሚባል ፈላስፋ ወዳጅ ነበርውና ለጠይቀው መጣ ተጨዋውተው ሲሄድ ሊሸኘው ወጣ። ይህች ብላቴና ጸንሳለች ካንተ ነውን ከሌላ አለው። እኔስ አንኳን ነቢብ ገቢር ሐልዮም አላውቅባት አለው። እንኪያስ ፀንሳለች ገብተህ ጠይቃት ያለው። በምን አውቆ ቢሉ ፈላስፋ ነውና በመልኳ። ኦ ወለተ እስራኤል መኑ ቀረጸ አክናፈ ድንግልናኪ ወእም ኀበ መኑ ፀነስኪ ብሎ ጠየቃት። እመንፈስ ቅዱስ አለችው ነገሩ ቢረቅበት ከደጁ ወድቆ የሚኖር ደረቅ ግንድ ነበርና ተክላ አለምልማ አሳይታዋለች። በዚያውስ ላይ አእዋፍን ከባህሪያቸው እንዲራቡ አእዋምን እንዲያፈሩ የሚያደርግ ማን ይመስልሃል አለችው። ነገሩን ተረዳው። ከዚህ በኋላ ለበዓል የሚወጡበት ጊዜ ደረሰ ትቻት ብወጣ ያደረገችውን ታውቅ ከደረቷ ትታጠቅ እንዲሉ ያደረገውን አውቆ ትቷት መጣ ይሉኛል። ይዣት ብወጣ ሴሰነሽ ብለው በድንጋይ ወግረው ይገድሉብኛል እያለ ወወድቀ ዮሴፍ ውስተ ጽኑዕ መዋግደ ሕሊና ይላል። ይህንን ሲያወጣ ሲያወርድ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ነገረው። ይቆየን...

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages