ብሂለ አበው (ክፍል አንድ) - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 24, 2020

ብሂለ አበው (ክፍል አንድ)


 ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ›› አባ እንጦንስ · ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል›› ቅዱስ አትናቴዎስ ·

 ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል›› ቅዱስ ሚናስ · 

‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና›› ታላቁ አባ መቃርስ ·

 ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም›› ቅዱስ አርሳንዮስ · 

‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል›› ቅዱስ እንድርያስ · 

‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን›› አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን ·

 ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው›› ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ · 

‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ›› ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ · 

‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር›› ቅዱስ ይስሀቅ ሶርያዊ ·

 ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል›› ቅዱስ እንጦስ 

o ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ጠበቃ መሆን፤መዋጋት ብሎም መሞት አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው ህይወት ነው፡፡

 o የረብዑ ምግብ ለሀሙስ የአርብ ምግብ ለቅዳሜ ይጠቅማል ነገር ግን የማክሰኞ ምግብ ለረብዑ አይጠቅምም የሀሙስ ምግብ ለአርብ አይሆንም የነፍስና የስጋ ነገርም እዲሁ ነው፡፡ 

o የነፍሳችን ነገር ትተን የስጋችንን ብቻ የምናደልብ ከሆነ ነፍስን በስጋ መቃብር እየቀበርናት መሆኑን አንርሳ

 o አንድ በርሜል ወተት በአንድ ጠብታ ኮምጣጤ የበጣጠሳል የብዙ ጊዜ ተጋድሎንም ጠብታ የሀጢያት ኮምጣጤ ያበላሸዋል 

o ራስህን በሀሰት አትውቀስ፡፡ራስህ መክሰስ ትህትና አይደለም፡፡ ታላቅ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው

 o ትዕቢት ሰይጣን ያለመው ጦር ነው 

o ትህትና ህፀፅን የምታስታውቅ መስታወት ናት

 o ክርስትና ማለት የሰውን ሸክም መሸከምና እስከሞት ድረስ መፅናት ማለት ነው

 o በባልንጀራው ላይ ክፋትን የሚያስብ ሰው ያችው የሚያስባት ክፋት ራሱን ትጎዳዋለች፡፡ በየትና ምን ጊዜ እደምትጥለው ግን አያውቅም

 o ስንፍናውን ወደጥበብ፤አላዋቂነቱን ወደእውቀት ፤መጥፎ ጠባዩን ወደበጎነት የሚመልስ ሰው ብርቱ ነው 

o  ፀሎት ገንዘብን ሊያመጣ ይችላል፡፡  ገንዘብ ግን ፀሎትን አያመጣም፡፡ 

ò ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው፡፡ ቅዱስ ስራፕዮን

 ò የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ ፡፡ መጽሐፈ ምክር

 ò አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል፡፡ አረጋዊ መንፈሳዊ

 ò ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ፡፡ ማር ይስሐቅ

 ò ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለየዋል፡፡ አረጋዊ መንፈሳዊ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages