#ሰማዕቱ_ጊዮርጊስና_ኢትዮጵያ_ምን_እና_ምን_ናቸው/ዓድዋ/ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, May 19, 2020

#ሰማዕቱ_ጊዮርጊስና_ኢትዮጵያ_ምን_እና_ምን_ናቸው/ዓድዋ/


ዓድዋን ስናከብር እዛው የጦሩ ሜዳ ድረስ አብሮ የዘመተውን የአራዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰራውን ተአምር እንኳን ኢትዮጵያዊ ፋሽሽት ጣሊያኖችም እንኳን በነጭ ፈረስ ሆኖ በእሳት ሰይፍ የፈጀን አለ ብለው በመፅሀፋቸው የመሰከሩለትን የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ወዳጂ መዘንጋት አይገባም።
በአዲስ አበባ እንብርት አራዳ አንድ ለጥቁሮች የነፃነት ትግል ነፀብራቅ የሆነ ቤተ እምነት አለ። የአድዋ ድል መታሰቢያና የነፃነት ጮራ ነው። ቤተ አምልኮቱ መናገሻ
ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይሰኛል። “መናገሻ” መባሉ ደግሞ ሁለት
ቀደምት ነገስታት ስርዓተ ንግስናቸው የተፈፀመው በዚሁ ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን መሆኑ ነው።
በኢትዮጵያ የአድዋ ድል ሲወሳ ተለይቶ የማይነሳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወራሪውን ፋሽስት ድል ለመንሳት አፄ ሚኒሊክና እቴጌ ጣይቱ የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት የጦር አውድማ ድረስ ይዘው በመሄድ ጠላትን ድል ስለ ማድረጋቸው በውጭ እና በአገር ውስጥ የታሪክ ፀሐፊያን የተመሰከረለት ሐቅ ነው።
ድሉም የተገኜው የካቲት 23 በጊዮርጊስ እለተ ቀን ነው ጣሊያነ ኢትዮጰያዊያኖች
ለሀይማኖታቸው ቅን መሆናቸውን ስላወቀ በጊዮርጊስ ቀን ቅዳሴ ይገባሉ በማለት
ጦርነቱን ቢጀምርም በእግዚአብሔር እርዳታ ድሉ የኢትዮጵያውያን ሆነ፡፡
በአድዋው ጦርነት በዘመናዊ መሳሪያ እና በሠለጠነ ወታደር ለወረራ የመጣውን
የጣሊያን ጦር ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለመውጋቱ የጣሊያን ወታደሮች “ከኢትዮጵያ
አርበኞች መኃል አንድ ወጣት በነጭ ፈረስ ተቀምጦ ሰራዊታችንን ፈጀብን” በማለት
በትክክል ስለመናገራቸው በመናገሻ ገ/ጽ/ቅ/ጊ ቤተክርስቲያን ቤተ መዘክር ባገኜሁት መጽሄት ላይ ሰፍሯል።
ለአድዋ ድል መገኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሚና እጅግ የላቀ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ይህች ጥንታዊ ቤተክርስቲያን በአድዋ ጦርነት ወቅት
ከመነሻው እስከመጨረሻው፣ ከዘመቻው እስከ ድሉ፣ ከዋዜማው እስከጦርነቱ
በመሪነትና በተሳታፊነት ነበረች፡፡ ቤተክርስቲያኗ ሕዝቡን በመቀስቀስ፣ አመራር
በመስጠት፣ አብራ በመዝመት፣ የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖር በማድረግ፣ በጦርነቱ
በመሳተፍ፣ መረጃ በመስጠትና በማስቀመጥ ባደረገችው አስተዋጽዖ ተወዳዳሪ
አልነበራትም፡፡ ለረጅም ዘመናት ይዛ በቆየችው ልዩ ልዩ አገራዊ ሓላፊነትና ሚናዋ
ምክንያት፣ አገር ያለ ሃይማኖት ሃይማኖት ያለ አገር የለም በሚለው እሳቤ፣በቀደሙት
የጦርነት ታሪኮች ከሁሉም በላይ ጥቃት የደረሰባት እርሷ በመሆኗ ( ለአብነት ያክል
የአህመድ ግራኝን ጥፋት፣የመቅደላን የቅርስ ዝርፊያ ፣ የደርቡሾች ጥቃት መጥቀስ
ይቻላል) እና በተለይ ደግሞ የወራሪው መንገድ ጠራጊዎች አባ ማስያስን የመሳሰሉ
ሚሲዮናውያን በመሆናቸው ቤተክርስቲንዋ በጦርነቱ የነበራትን ጉልህ ተሳትፎ
ምክንያታዊ ያደርገዋል፡፡
በአደዋ ጦርነት ወቅት ቤተክርስቲያኗ የነበራትን የላቀ ሚና ለመረዳት የአፄ ምኒልክን
የክተት ዐዋጅ ብቻ መመልከት በቂ ነው፡፡ አዋጁ ጦርነቱ ከቤተክርስቲያን፣
ከእግዚአብሔር እና ከወላዲት አምላክ ጠላት ጋር እንደሆነና የመጣው ጠላት አገር
የሚያፈርስ ብቻ ሳየሆን ሃይማኖት የሚለውጥ ጭምር መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡
በመሆኑም የጦርነቱ አዋጅ ሐይማኖታዊ ቅርጽ ነበረው፡፡ አዋጁ እንደሚከተለው ነበር፡፡
"ስማ፣ ስማ፣ተሰማ የማይሰማ የእግዚአብሔር እና የወላዲት አምላክ ጠላት ነው፡፡
ስማ፣ ስማ
ተሰማማ፣የማይሰማ የእግዚአብሔርና የቤተክርስቲያን ጠላት ነው፡፡ ስማ፣ስማ
ተስማማ፣ የማይሰማ የእግዚአብሔርን የንጉሡ ጠላት ነው፡፡
ስማ፣ስማ
ተስማማ፣ የማይሰማ የእግዚአብሔርን የንጉሡ ጠላት ነው፡፡እግዚአብሔር ወሰን
እንዲሆን የሰጠንን ባሕር አልፎ ሃይማኖት የሚለውጥና ሀገር የሚያጠፋ ጠላት
መጥቶአል፡፡ እኔ ምኒልክ በእግዚአብሔር ርዳታ ሀገሬን ለጠላት አሳልፌ አልሰጥም፡፡
ያገሬ ሰው! ከአሁን ቀደመ የበደልሁህ አይመስለኝም፡፡ አንተም እስካሁን
አላስቀየምኸኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ርዳኝ፣ ጉልበት የሌለህ
ለልጅህ፣ለሚስትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በኅዘን ርዳኝ፡፡ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ
ትጣላኛለህ፣ አልተውልህም፡፡ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም፡፡ ዘመቻዬም
በጥቅምት ነው፡፡
አፄ ምኒልክ አዋጅን ካስነገሩ በኋላ በአዲስ አበባ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸሎት ማድረሳቸውና ብፅዓት ማድረጋቸው ወይም ስዕለት
መሳላቸው የጦርነቱ መንፈሳዊ ዝግጅት አካልና ለቤተክርስቲያኗ ልዩ መልእክት
የነበረው ነው፡፡ ስዕለታቸውም “አምላከ ቅ/ጊዮርጊስ ድሉን ቢሰጠኝ ይህን የቅ/
ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሣር ክዳኑን ለውጨ ባማረ ሕንፃ አሠራዋለሁ ” የሚል ነበር፡፡
ይህንም ስእለታቸውን ከድል በኋላ ፈጽመውታል፡፡
እንኳን ለ124ኛው የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁሮች እንዲሁም ለተጨቆኑ ሰወች በሙሉ የድል ቀን ለሆነው የዓድዋ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ የሰማእቱ የቅዱስ የጊዮርጊስ እገዛ አሁንም ወደፊት በኢትዮጵያ ሀገራችን አይራቅብን ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages